Get Mystery Box with random crypto!

'አንድ በሩሲያ የሚተረት ተረት አለ ' አንድ ሽማግሌ ሰው ዛፍ ሲተክል ያዩት ወጣቶች 'ይህ ዛፍ የ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"አንድ በሩሲያ የሚተረት ተረት አለ " አንድ ሽማግሌ ሰው ዛፍ ሲተክል ያዩት ወጣቶች "ይህ ዛፍ የሚያፈራው ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።  አንተ እስከዚያ ልትቆይ አትችልም ለምን በከንቱ ትደክማለህ ?" አሉት። እርግጥ ነው እኔ አርጅቻለሁ። ነገር ግን ሰው የተከለውን በልቻለሁና እኔም ተክዬ ማለፍ ፣ ብድሬን መክፈል አለብኝ" ብሎ መለሰላቸው ይባላል ... አሉ " ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት  ኦቶባዮግራፊ  መግቢያ ግርጌ ማስታዎሻ ላይ ።
   ------------
በተለይ ደግሞ የእኛ  ዘመን ኢትዮጵያውያን  የራሱን ምቾት መስዋእት አድርጎ  የሚቀጥለውን ትውልድ አስቦ ካልሰራ  ምናልባትም የምናስረክባቸው ነገር ላይኖር ሁሉ ይችላል ። ቢያንስ የእኛ አባቶች ሉዓላዊት ሀገር ከነ ሙሉ ክብሯ አስረክበውን ነበር ፤ በቀደሙት አባቶች ደምና አጥንት በተገነባች  ሀገር ላይ ስንኖር እዳ እንዳለብን ተገንዝበን እኛም የተሻለች ሀገር ሰርተን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስረከብ ዛሬ በትብብር  የማንበላው ኬክ ጋግረን ለሚቀጥለው ትውልድ ማቅረብ አለብን !
ከሠለጠኑት ሀገራትም የምንማረው ይኸንን ነው ።

         (~Tesgaw mamo~)