Get Mystery Box with random crypto!

'ጌታዬ ሆይ ስለ በደሌ፣ ስለ አበሳዬ ከአንተ እለምን ዘንድ ድፍረት የለኝም። በደሌ ከሰው ሁሉ በደ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"ጌታዬ ሆይ ስለ በደሌ፣ ስለ አበሳዬ ከአንተ እለምን ዘንድ ድፍረት የለኝም። በደሌ ከሰው ሁሉ በደል ይበልጣልና፤ ከሁሉ ፍጥረት ይልቅ እኔ በፊትህ በደልሁ። ከቁጥር ያለፈ ብዙ ጊዜ ስምህን ሰማሁ። ከአቅም በላይ ዝሙትን አበዛሁ። ከዘማውያኑ ጋር ሁሉንም አደረግሁ። ለአንተም ፈጽሞ ባለዕዳ ኾንሁ፤ ዲያብሎስ የኃጢአትና የክፋት ወታደር አደረገኝ። ከሽፍታ የሚበልጥ ሞትን አመጣብኝ፤ እኔ ነፍሰ ገዳይና ፍጹም ዘማዊ ነኝ።

እግዚአብሔር በፈጠረውም ከዘማዊቷ ዝሙትን ፈጸምሁ። ከነነዌ ሰዎች ይልቅም ፈጽሞ ኃጢአትን ሠራሁ፥ ያለ ንስሐም ተቀመጥሁ። በደሌም ከምናሴ ይልቅ ፈጽሞ በእኔ ላይ በዛ። ከከነናዊቷ ሴት ይልቅም ኃጢአቴ ፈጽሞ ከበደ። መሰነካከልን ሁሉ ተሰነካከልሁ፤ ቅዱስና ንጹሕ ስምህን አስቆጣሁ፤ መንፈስህንም አሳዘንሁ። ትእዛዝህንም አልተቀበልሁም። መዝገብህንም በማይገባይ አጠፋሁ። የሰጠኸኝን ልጅነትም በወንጀል አጠፋሁ።

መቅደስህንም አረከስሁ። ይህችም ሥጋዬ ናት፤ ነፍሴንም በርኲሰት አረከስኳት። ይህችውም የአንተ አርአያና አምሳል ናት። የሰጠኸኝን ሀብትም ከጠላቶችህ ጋር ኾኜ በተንሁት (አጠፋሁት)። ትእዛዝህንም አልጠበቅሁም። ያለበስኸኝን ልብስም አሳደፍሁት። በእኔ ላይ ያበራኸውን መብራትም በንዝኅላልነቴ ከውስጤ አጠፋሁት። ..."

ውዳሴ አምላክ ዘዓርብ (የአባ ሲኖዳ ጸሎት)