Get Mystery Box with random crypto!

'ለጽርሐ ጽዮን እሮጣለሁ' የሚል መንፈሳዊ መሪ ሀሳብን ያነገበ ሩጫ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው ። | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"ለጽርሐ ጽዮን እሮጣለሁ" የሚል መንፈሳዊ መሪ ሀሳብን ያነገበ ሩጫ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው ።

መነሻው ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን መድረሻውን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማሪያም አንድነት ገዳም በማድረግ ነው መንፈሳዊ ሩጫው እየተካሄደ የሚገኘው።

በመንፈሳዊ ሩጫው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያኗ አባቶች፣ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ በነቂስ እየተሳተፉበት ነው።