Get Mystery Box with random crypto!

ውሻ ምን አገባት ከሰው እርሻ!? -- በአውደልዳይ (ይቅርታ) በአገልጋይ ዮናታን አክ-ሊሉ ድርጊት | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

ውሻ ምን አገባት ከሰው እርሻ!?
--
በአውደልዳይ (ይቅርታ) በአገልጋይ ዮናታን አክ-ሊሉ ድርጊት ዘሪያ፥ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠበቅ ያለ የቅሬታ ደብዳቤ፣ ከብሮድካስት ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ ጠንካራ ተግሣጽ እንጠብቃለን። ሰውየው በቁርዓን ላይ ቢያደርገው ምን እንደሚጠብቀው ያውቃል። በካህን ደረጃ የሚነበብን፣ በትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለን መጽሐፍ፣ አማኞች በሌሉበት፣ ዐይን ላወጣ ሳቅና ስላቅ ማዋል በእርግጥ የአስተዳደግ በደል ማሳያ ነው። ውርጋጥ! ውሻ ምን አገባት ከሰው እርሻ! ድርጊቱ በወንጀልም በፍትሐ ብሔርም ያስጠይቃል።
--
ምሥጢረ ሥጋዌን በክሮሞዘም X እና Y ሊተነተን ሲጋጋጥ የነበረ አውደልዳይ በሚመጥነው ቦታ ሊቀመጥ ይገባል። "አትርሱኝ ነው" እየተባለ ቢታለፍም ሰውዬው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማነወሩን እንጀራ ማብሰያ አድርጎታል።
--
(እናክርረው ካልን) ቴክኒካሊ፥ እነ ዮናታንና ተዛማጅ የብልፅግና ወንጌል ሰባቂዎች የሚሰብኩት ኢየሱስ ለእኔ የቀራንዮው ወይም የናዝሬቱ ወይም የቆሮንቶሱ ኢየሱስ አይደለም። ጣዖት ነው! በእነርሱ ሥጋዊ ምኞትና ፍትወት ልክ የሚገለገሉበት ጣዖት። ተከባብሮ የመኖር ቀይ መስመር በአጉራ ዘለሎች እየተጣሰ ነው! የፍትሕ ጎማ ትሽከርከር!!!

~በአማን ነጸረ~