Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.53K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-03-08 09:18:54
በውጤቱ የሚደሰቱበት ከችግረወት የሚወጡበት ሀሳበወትን የሚአሟሉበት ለበሽታወት መፍትሔ የሚአገኙበት

ከአሉበት ሁነው በስመወት እና በናትወት ስም ያለበወትን ችግር ማወቅ ይችላሉ

በየቀኑ  የአባቶቻችን እውቀት
የጥበብ ትምሕርት ለማግኔት ከታች ቻናሎቸን ይቀላቀሉ 

      ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ

መሪጌታ ጥበቡ
ባህላዊ መድሐኒት ምርመራ እና ህክምና መስጫ ማእከል  ከምንሰጣቸው በጥቂቱ
  ለገርጋሪ ለአይነጥላ ለአይን ውጊት
ገብያ ለተዘጋበት ለሚገረግረው (ለገብያ)
አፍቅራ ላጣች ለመስተፋቅር (ላጣ)
ለኪንታሮት ባንድቀን የሚአወጣ መዳኒት
ለእሪህ (በአንድቀን ሕክምና)
ለዲስክ መንሸራተት
ለአስም
ለስንፈተወሲብ ለመቸኮል ለመልፈስፈስ
ለቁራኛ ለመተት መፍትሔ
ትዳር ለሚገረግራት
ለመካን
ለጭንቀት
ለሚጥል በሽታ
ለፊት ማድያት
ሌሊት ለሚሸና
የሕዝብ መስተፋቅር
ለሕገጠብቅ እንዳይሔድ (ወይ እንዳቴድ)
ገንዘብ ለሚበተንበት (ባት)
     
        ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ11 ዲያስፖራ በአዲሱ አስፓልት ዳሽን ባንክ ጀርባ
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ተደራሽ በሁሉም ቦታወች ከአገር ውስጥም ውጭም
የሚፈልጉትን በውስጥ መስመር በቴሌግራም ያስቀምጡ

ለበለጠ መረጃ 0912718883
                           0917040506
   በቲክቶክ መማማሪያ የእውቀት ምንጭ
https://vm.tiktok.com/zMM2kcDUb/
    በቴሌግራም የቴሌግራም ቻናል መማማሪያ
https://t.me/mergatah
13.1K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-07 08:54:40
እንዴት አደራችሁ

ውድ ኢትዮጲያውያን ከተቀረው የሰለጠነ አለም ጋር እኩል ለመራመድ ስለ ኮምፒውተር ሳይንስ ጠለቅ ያለ መሰረታዊ እውቀት በነፃ ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በኦንላይን ይማሩ!

ይህንን ኮርስ መማር ከእውቀት ባሻገር CV ላይ ከበድ ያለ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን፣ በትልልቅ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች እውቅናን ያተረፈ ኮርስ ነው፣ ወጣቶች በሳምንት 2 ቀን ብቻ ኦንላይን ብትማሩ Harvard ነፃ ሰርተፍኬት ይኖራችሗል።

ከዛ በተጨማሪ የፕሮግራሚንግ ቋንቋን በቀላሉ ትማራላችሁ፣ ስለ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ስለ ፓይተን፣ SQL ፣ JavaScript፣ Debugging እና ሌሎችም ድንቅ ድንቅ ሳይንሳዊ እውቀት ምታገኙበት ነው ይጠቅመዋል ለምትሉት ሰው ሁሉ ሼር አድርጉ።

Official Link: https://www.edx.org/learn/python/harvard-university-cs50-s-introduction-to-programming-with-python
12.6K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 15:02:31
የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በፍርድ ቤት ተወሰነ

“ሁከት እና በጥብጥ በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት 13 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ 100 ሺህ ብር የዋስትና ገንዘብ በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው። ለፖለቲከኛው ዋስትናውን የፈቀደው፤ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ነው።

አቶ በቴ ሲቪል በለበሱ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ “አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ለተሰኘው የዜና ድረ ገጽ ዘጋቢ ከሆነው  አንቷን ጋሊንዶ ጋር ሐሙስ የካቲት 14፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በውይይት ላይ በነበሩበት ወቅት ነው። ዛሬን ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኦነጉ ፖለቲከኛ፤ በፖሊስ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠየቅባቸው ቆይቷል።

ዛሬ ረፋዱን በተካሄደው ችሎትም፤ ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም” በሚል ተጨማሪ 11 የምርመራ ቀናትን ጠይቋል። የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በነበረው ችሎት ለፖሊስ ተጨማሪ አምስት የምርመራ ቀናት የፈቀደው፤ ፖሊስ የሚያቀርበውን “የስልክ ምርመራ ውጤትን ለመስማት” ነበር።

በዛሬው ችሎት የተገኙት መርማሪ ፖሊስ፤ የአቶ በቴን የስልክ የምርመራ ውጤት ለመቀበል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) በተደጋጋሚ ጥያቄ ምማቅረባቸውን ሆኖም እስካሁን ውጤቱን አለመቀበላቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልጓቸው አስረድተዋል።

Via Ethiopia Insider
14.6K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 14:35:42
ወላይታ ሶዶ በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያናችን እየፈረሰችብን ነዉ ድምፅ ሁኑን

በወላይታ ሶዶ በአታ ለማርያም ቤተክርስትያን ይዞታ "ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል" በሚል ምክንያት በጸጥታ አካላት በጉልበት እየፈረሰች ነው

በአንድ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ስጦታ ሰጪነት በተገኘ መሬት ላይ የተተከለችው በወላይታ ሶዶ ከተማ የምትገኘው ዋዱ በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
የወላይታ ዞን ስፍራውን ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል በሚል ምክንያት መቃኞ ህንጻ መቅደሱን ለማፍረስ የጸጥታ ኃይል ያሰማራ ሲሆን የጸጥታ አካላት የጦር መሳርያ በመጠቀም ምዕመናንን ከአከባቢው ለማራቅ ቢሞክሩም አሁን ድረስ ህዝቡ ቤተክርስቲያኒቷን ከበ በመያዝ የማፍረስ ተግባሩን ለማስቆም እየሞከረ ይገኛል። ድምፅ ሁኑን

@Yenetube @Fikerassefa
13.9K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 12:00:27
የ 7000 ብር ሽልማት እርስዎን ይጠብቃል!
አሁኑኑ በ7868 ላይ OK ብለው በመመዝገብ የጠቅላላ እውቀት ውድድር ላይ ተሳታፊ ይሁኑ፣ ይወዳደሩ፣ ይሸለሙ!

አሁኑኑ ይመዝገቡ
Click 7868 OK
14.1K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-05 21:59:02
ቴሌግራም በሰዓታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዳዲስ ተጠቃሚዎች አገኘ።

ዓለም ላይ ለሰዓታት ፌስቡክ እና ኢንስታግራም መቋረጣቸውን ተከትሎ " ቴሌግራም "ን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መቀላቀላቸውን የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተቋረጡበት ባለፉት ሰአታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቴሌግራም ላይ ሲመዘገቡ እና ይዘቶችን ሲያጋሩ ቆይተዋል " ብለዋል።

" ቴሌግራም " ከእነዚህ አገልግሎቶች የበለጠ አስተማማኝ ነው ሲሉም አክለዋል።

" ምንም እንኳን ከሜታ አንድ ሺህ ጊዜ ያነሱ ቋሚ የሆኑ ሰራተኞች ቢኖሩንም በመተግበሪያው ላይ አዳዲስ ይዘቶችን ለማሻሻል እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማከል ፈጣኖች ነን " ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በ2023 ሙሉ ከዓመቱ 525,600 ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌግራምን አገልግሎት ማግኘት ያልተቻለው በአጠቃላይ ለ9 ደቂቃ ብቻ ነው " ያሉ ሲሆን " ይህም 99.999983% ቴሌግራም ስራ ላይ እንደነበር አመላካች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
15.5K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 18:09:35
የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን " በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል። " ሲል አሳውቋል።

" ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል " ብሏል።

ቀደም ብሎ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሜክሲኮ የሚገኘውንና የቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ሥፍራ ለመግዛት መስማማታቸውን ከሁለቱም ወገን መገለጹ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
14.0K viewsedited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-03 16:49:09
#ሰበር #BreakingNews
'ዝክረ አድዋ' ዝግጅት እንዳይካሄድ ተከለከለ

እሁድ የካቲት 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)ወደዛሬ የተዘዋወረው ዓመታዊው 'ዝክረ አድዋ' ዝግጅት እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት እንዳይካሄድ ተከለከለ።

ሀሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 በብሔራዊ ቴያትር ሊካሄድ የነበረው የዝክረ አድዋ ዝግጅት ወደ ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016 ተዘዋውሮ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት እንዳይካሄድ ተከልክሏል።

ዝግጅቱ በቅድሚያ ከታሰበበት ብሔራዊ ቴያትር ወደ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ተቀይሮ የነበረ ሲሆን አዲስ ማለዳ በስፍራው ተገኝታ ነበር።

አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው የጸጥታ አካላት በቦታው በመገኘት ዝግጅቱን ለመታደም የተሰበሰቡ ሰዎችን በትነዋል።

በዚህም በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ታዳምያን እንዲመለሱ እየተደረጉ ይገኛል።

እንዲሁም በስፍራው ተዘጋጅተው የነበሩ ባንዲራዎች እንዲወርዱ መደረጉንም አዲስ ማለዳ ተረድታለች።

ሆኖም ግን ዝግጅቱ እንዳይደረግ የተከለከለው "በምን ምክንያት እንደሆነ" ይህ ዘገባ እስከሚወጣ ድረስ የተገለፀ ነገር የለም።

በአብርሃም ግዛው መዝናኛና የሚዲያ ስራዎች ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ የጥበብ ሰዎች፣ የሃይማኖት አስተማሪዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም የተጋበዙበትና ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡቡት መድረክ እንደሚሆን ተጠብቆ ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
17.3K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 10:47:19
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የመከላከያ ሚንስትር ዶ/ር አብረሀም በላይ ፣የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረዳ እና ሌ/ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተገኙበት 128ኛ አመት የዓድዋ ድል በአል በዓድዋ እየተከበረ ነው።

በበአሉ ላይ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የዓድዋ እና አካባቢው ነዋሪዎችም ተገኝተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
14.2K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 09:36:02
መልካም በዓል ይሁንሎ።

በዓሉ የህዝብ ነበር
13.9K viewsedited  06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ