Get Mystery Box with random crypto!

ቴሌግራም በሰዓታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዳዲስ ተጠቃሚዎች አገኘ። ዓለም ላይ ለሰዓታት ፌስቡ | YeneTube

ቴሌግራም በሰዓታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዳዲስ ተጠቃሚዎች አገኘ።

ዓለም ላይ ለሰዓታት ፌስቡክ እና ኢንስታግራም መቋረጣቸውን ተከትሎ " ቴሌግራም "ን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መቀላቀላቸውን የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተቋረጡበት ባለፉት ሰአታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቴሌግራም ላይ ሲመዘገቡ እና ይዘቶችን ሲያጋሩ ቆይተዋል " ብለዋል።

" ቴሌግራም " ከእነዚህ አገልግሎቶች የበለጠ አስተማማኝ ነው ሲሉም አክለዋል።

" ምንም እንኳን ከሜታ አንድ ሺህ ጊዜ ያነሱ ቋሚ የሆኑ ሰራተኞች ቢኖሩንም በመተግበሪያው ላይ አዳዲስ ይዘቶችን ለማሻሻል እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማከል ፈጣኖች ነን " ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በ2023 ሙሉ ከዓመቱ 525,600 ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌግራምን አገልግሎት ማግኘት ያልተቻለው በአጠቃላይ ለ9 ደቂቃ ብቻ ነው " ያሉ ሲሆን " ይህም 99.999983% ቴሌግራም ስራ ላይ እንደነበር አመላካች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።