Get Mystery Box with random crypto!

የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ። ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢ | YeneTube

የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን " በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል። " ሲል አሳውቋል።

" ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል " ብሏል።

ቀደም ብሎ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሜክሲኮ የሚገኘውንና የቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ሥፍራ ለመግዛት መስማማታቸውን ከሁለቱም ወገን መገለጹ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa