Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር #BreakingNews 'ዝክረ አድዋ' ዝግጅት እንዳይካሄድ ተከለከለ እሁድ የካቲት 24 | YeneTube

#ሰበር #BreakingNews
'ዝክረ አድዋ' ዝግጅት እንዳይካሄድ ተከለከለ

እሁድ የካቲት 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)ወደዛሬ የተዘዋወረው ዓመታዊው 'ዝክረ አድዋ' ዝግጅት እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት እንዳይካሄድ ተከለከለ።

ሀሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 በብሔራዊ ቴያትር ሊካሄድ የነበረው የዝክረ አድዋ ዝግጅት ወደ ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016 ተዘዋውሮ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት እንዳይካሄድ ተከልክሏል።

ዝግጅቱ በቅድሚያ ከታሰበበት ብሔራዊ ቴያትር ወደ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ተቀይሮ የነበረ ሲሆን አዲስ ማለዳ በስፍራው ተገኝታ ነበር።

አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው የጸጥታ አካላት በቦታው በመገኘት ዝግጅቱን ለመታደም የተሰበሰቡ ሰዎችን በትነዋል።

በዚህም በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ታዳምያን እንዲመለሱ እየተደረጉ ይገኛል።

እንዲሁም በስፍራው ተዘጋጅተው የነበሩ ባንዲራዎች እንዲወርዱ መደረጉንም አዲስ ማለዳ ተረድታለች።

ሆኖም ግን ዝግጅቱ እንዳይደረግ የተከለከለው "በምን ምክንያት እንደሆነ" ይህ ዘገባ እስከሚወጣ ድረስ የተገለፀ ነገር የለም።

በአብርሃም ግዛው መዝናኛና የሚዲያ ስራዎች ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ የጥበብ ሰዎች፣ የሃይማኖት አስተማሪዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም የተጋበዙበትና ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡቡት መድረክ እንደሚሆን ተጠብቆ ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa