Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 128.01K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 492

2021-02-03 20:18:40 በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገጽታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩት ቡድኖችን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣አሸባሪዎች ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እና ለፍንዳታ ሥራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል እና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ ዓሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለዓሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረው እና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲያሴር የቆየው መሐሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች እና ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል።

ሌላ ተመሳሳይ ተልእኮ የተሰጠው ቡድን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ነው።

የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣት እና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል።

ከአውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስዊዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
17.2K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 19:56:32 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ለማሳየት የተለያዩ ሰልፎች መካሄዳቸው ይታወቃል። እነዚህን ሰልፎች ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) “ፓርቲያችን ያለአግባብ ተወንጅሏል፣ ይህም ፓርቲዎች የፈረሙትን የጋራ የስነምግባር ደንብ የጣሰ ነው” ሲል አቤቱታውን ለቦርዱ አቅርቧል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከአቤቱታው በተጨማሪ በእለቱ የተደረጉ የተለያዩ ሰልፎችን በሚዲያ ክትትል ክፍሉ አማካኝነት ክትትል በማድረግ በአሜሪካ ድምጽ፣ በዋልታ፣ በፋና፣ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ እንዲሁም በነዚሁ ሚዲያዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ የተላለፉ መልእክቶችን በማየት
- ሠልፎቹ በዋልታ ቴሌቪዥን እና በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በቀጥታ መተላለፋቸውን እንዲሁም የመንግስት አመራር አካላት፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች መሳተፋቸውን ተረድቷል።
- ከሚዲያዎቹ በቀጥታ ከመተላለፉም በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት አመራር አባላት በሰልፎቹ ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች ተመልክቷል።
- በሰልፎቹ የተለያዩ መፈክሮች፣ በተወሰኑ የመንግስት የዞን፣ የከተማ አስተዳድር አመራር አካላት እና ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊዎች ንግግሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ እና የምርጫ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ፓርቲዎች በአሉታዊ መልኩ መነሳታቸውን ተገንዝቧል።

እነዚህ ሰልፎቹ ላይ የተነሱ ንግግሮች እና መፈክሮች በህጋዊነት ተመዝግበው፣ በፖለቲካ ፓርቲነት የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን ማለትም አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በአመፃ ተግባር በመሳተፍ ከምርጫ ቦርድ ከተሰረዘው ጁንታ በማለት ከሚጠሩ ህወሃት ፓርቲ ጋር አንድ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብሎ በመፈረጅ እና ህገወጥ ናቸው በማለት የምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 ላይ ያሉ ድንጋጌዎችን ጥሰዋል።

ቦርዱ ሰልፎቹ ላይ የተንጸባረቁት ንግግሮች እና መፈክሮች በአዋጁ አንቀጽ 132 ንኡስ 2(ሀ) ላይ የተጠቀሰውን ስም የሚያጠፋ ንግግርን ክልከላ ድንጋጌ አንዲሁም በዚሁ ህግ አንቀጽ 143 (2) ላይ የተጠቀሰውን ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳያሰራጩ ስጋት እና ፍርሀት የመፍጠር የስነምግባር ጥሰት ፈጽሞ አግኝቶታል። ከዚህም በተጨማሪ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ገዥው ፓርቲ በጋራ ተስማምተው በፈረሙት የቃልኪዳን ሰነድ አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሰውን “የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በየትኛውም ጉዳይ ላይ ሊኖር የሚችል የዓላማ፣ የሃሳብ ወይም የዘር ልዩነትን፣ ወይም ሌላ ምክንያት መሰረት በማድረግ የሌሎች ፓርቲዎችን መብቶች የሚፃረሩ ወይም የሚያጣብቡ ድርጊቶችን ከመፈፀም የመቆጠብ ግዴታ አለባቸው” የሚለውን አንቀጽ የሚጥስ ተግባር ነው።

ይህ ተግባር በተለይ ቦርዱ የመጨረሻ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ የምርጫ ተግባራት በይፋ መፈጸም ከጀመረ በኋላ በምንገኝበት የምርጫ ወቅት መከሰቱ በምርጫ ውድድር ላይ ፓርቲዎች በእኩልነት የመወዳደር መብታቸውን ችግር ላይ የሚጥል በመሆኑ ቦርዱን በእጅጉ አሳስቦታል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ያሉ የገዥው ፓርቲ አመራሮች እና በየአስተዳደር እርከኑ ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች በተመሳሳይ ተግባራት ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ያሳውቃል።

ለወደፊትም በተመሳሳይ በምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 እና ተያያዥ መመሪያዎች መሰረት የፓርቲዎች የቅስቀሳ የንግግር እና ሌሎች ለህዝብ የሚያሰራጯቸውን መልእክቶች ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እስከእጩ መሰረዝ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
13.3K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 19:00:56 የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚወያይ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የተመድ ሰብዓዊ ሁኔታዎች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ስላለው ሰብዓዊ ሁኔታ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጉዳዩ ለሦስተኛ ጊዜ ውይይት እንዲደረግበት ሃሳብ ካቀረቡት የምክር ቤቱ አባል ሀገራት መካከል፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ይገኙበታል፡፡ ጉዳዩ እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ “ሌሎች ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ስር የተያዘ ሲሆን፣ በውይይቱ ማብቂያ መግለጫ ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
12.8K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 18:05:10
ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ።

የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይ የበላይ ጠባቂ ሆኖ በዋና ዋና የአማዞን ጉዳዮች ብቻ መሳተፍ ብቻ እንደሚፈልግ ገልጿል።

'የአማዞን ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መሥራት ፋታ የለውም። ጊዜና ጉልበትን ያሟጥጣል። እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ላይ መሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማተኮር ጊዜ አይሰጥም' ይላል ቤዞስ በይፋ በጻፈው የመልቀቂያ ደብዳቤ።

ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ አሁን ትኩረት ሊያደርግበት የፈለጋቸው የሥራ ዘርፎች በህዋ ትራንስፖርት ላይ የሚያተኩረው ብሉ ኦሪጂን እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ህትመት እና ሌሎች የግል ፍላጎቶቹ ላይ ነው።

የአማዞን የበይነ መረብ ገበያን የጀመረው በ1994 ሲሆን ያን ጊዜ መጽሐፍ በበይነ መረብ የሚሸጥ ትንሽ ድርጅት ሆኖ ነበር አማዞን የተመሰረተው። አሁን አማዞን በመላው ዓለም 1.3 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉት።

በ2020 ዓ/ም ብቻ የአማዞን ጠቅላላ ሽያጭ 386 ቢሊዮን ዶላር አልፏል። ይህም የሆነው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የበይነ መረብ ገበያው ስለደራ ነው። ጄፍ ቤዞስ በፎርብስ የሀብት ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰለት ሀብቱ 192 ቢሊዯን ዶላር ደርሷል።

Via - BBC
@Yenetube @FikerAsssefa
15.9K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 17:35:42
የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል፡፡

ም/ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባው የ6ኛ አመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ይጀምራል፡፡ ም/ቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲሁም ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቲዎሮሎጂ ምልከታ መሰረተ ልማት እና የትንበያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን የምርጫ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የሚስተናገዱበት የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ደንብንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.0K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 17:33:48
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው በወረዳው በዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ላይ ነው።ከወረዳው ዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ጨለንቆ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 73876 አአ የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።በአደጋው በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ የ36 ሰዎች ህይወት ወድያው አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደደር፣ ጨለንቆና ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ መሆኑን አሳውቋል።የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፖሊስ መምሪያው ለኢዜአ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.4K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 12:07:40
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 738.19 ኪ.ሜ ርዝማኔው ያላቸውን 8 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት ከተለያዩ ስራ ተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል።

በአጠቃላይ ባለስልጣን መስሪያቤቱባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በ43.3 ቢሊየን ብር ወጪ 21 መንገድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ከተለያዩ የሐገር ውስጥና ከውጭ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል።

ከመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ወደ ጎረቤት ሐገር ከሚያስተሳስሩ ፕሮጀክቶች; አንደስላሴ-ራማ ገረሁ ሰናይ ከኤርትራ፣ ዱርቤቴ -ቁንዝላ-መተማ ከሱዳን አንዲሁም ነጌሌ ቦረና-መልካሱፍቱ ከኬንያ አና ከሶማሊያ ይገኙበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
12.7K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 12:04:39 በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 እንደሚጀመር ተገለጸ!

በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በኮሮና ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ከፊታችን የካቲት 1 ቀን 203 ዓ.ም አንስቶ እንደሚጀመር የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በመጀመሪያ በኮሮና ምክንያት በኋላም በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሰለምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮኖ መከላከያ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ ትምህርት መስጠት ይጀመራል።

ወላጆች ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም አቶ አታከልቲ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደባኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @Fikerassefa
12.0K viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 11:45:14
በትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ለተገደሉ ንፁሃን መንግሥት ማዘኑን ገለፀ፡፡

‹‹የአንድ ንፁህ ሰው ሞት በራሱ ብዙ ነው›› ሲል መግለጫ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ሆኖም በሕግ ማስከበር ዘመቻው በፌደራሉ መንግሥት በኩል በንፁሃን ላይ የደረሰ ጉልህ ጉዳት አለመኖሩንም ያነሳል፡፡ምክንያት ያለው ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ ሙያዊ ስልቱን ተጠቅሞና ጥንቃቄ በተሞላበት እቅድ ስለተመራ ነው የሚል ነው፡፡የመረጃ ማጣሪያው በትግራይ ሕግ የማስከበር ወቅት በንፁሃን ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ በዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩት መረጃዎች በመረጃ ያልተደገፉና ያልተረጋገጡ ናቸው ሲልም አጣጥሏቸዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን መረጃዎቹ ከፖለቲካ ፍላጎት የመነጩ ስለመሆናቸውም ተከራክሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
11.5K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 10:53:58 ለአዲሱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የስደተኞች ጉዳይ እንዲሁም ከሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ጋር በተገናኘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከአትላንቲክ ካውንስል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በውይይቱም ይነሱ ለነበሩት በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሰጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡በተለይም በምዕራባዊያኑ በኩል ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ከሞላ ጎደል በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት እየተመለሰ እንደሚገኝ ለሰብዓዊ ድጋፍም ክፍት መሆኑን ማስረዳታቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
14.3K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ