Get Mystery Box with random crypto!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስ | YeneTube

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው በወረዳው በዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ላይ ነው።ከወረዳው ዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ጨለንቆ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 73876 አአ የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።በአደጋው በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ የ36 ሰዎች ህይወት ወድያው አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደደር፣ ጨለንቆና ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ መሆኑን አሳውቋል።የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፖሊስ መምሪያው ለኢዜአ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa