Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል፡፡ ም/ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒ | YeneTube

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል፡፡

ም/ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባው የ6ኛ አመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ይጀምራል፡፡ ም/ቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲሁም ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቲዎሮሎጂ ምልከታ መሰረተ ልማት እና የትንበያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን የምርጫ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የሚስተናገዱበት የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ደንብንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa