Get Mystery Box with random crypto!

ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ። የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ | YeneTube

ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ።

የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይ የበላይ ጠባቂ ሆኖ በዋና ዋና የአማዞን ጉዳዮች ብቻ መሳተፍ ብቻ እንደሚፈልግ ገልጿል።

'የአማዞን ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መሥራት ፋታ የለውም። ጊዜና ጉልበትን ያሟጥጣል። እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ላይ መሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማተኮር ጊዜ አይሰጥም' ይላል ቤዞስ በይፋ በጻፈው የመልቀቂያ ደብዳቤ።

ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ አሁን ትኩረት ሊያደርግበት የፈለጋቸው የሥራ ዘርፎች በህዋ ትራንስፖርት ላይ የሚያተኩረው ብሉ ኦሪጂን እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ህትመት እና ሌሎች የግል ፍላጎቶቹ ላይ ነው።

የአማዞን የበይነ መረብ ገበያን የጀመረው በ1994 ሲሆን ያን ጊዜ መጽሐፍ በበይነ መረብ የሚሸጥ ትንሽ ድርጅት ሆኖ ነበር አማዞን የተመሰረተው። አሁን አማዞን በመላው ዓለም 1.3 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉት።

በ2020 ዓ/ም ብቻ የአማዞን ጠቅላላ ሽያጭ 386 ቢሊዮን ዶላር አልፏል። ይህም የሆነው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የበይነ መረብ ገበያው ስለደራ ነው። ጄፍ ቤዞስ በፎርብስ የሀብት ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰለት ሀብቱ 192 ቢሊዯን ዶላር ደርሷል።

Via - BBC
@Yenetube @FikerAsssefa