Get Mystery Box with random crypto!

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚወያይ ምክ | YeneTube

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚወያይ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የተመድ ሰብዓዊ ሁኔታዎች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ስላለው ሰብዓዊ ሁኔታ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጉዳዩ ለሦስተኛ ጊዜ ውይይት እንዲደረግበት ሃሳብ ካቀረቡት የምክር ቤቱ አባል ሀገራት መካከል፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ይገኙበታል፡፡ ጉዳዩ እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ “ሌሎች ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ስር የተያዘ ሲሆን፣ በውይይቱ ማብቂያ መግለጫ ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa