Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 738.19 ኪ.ሜ ርዝማኔው ያላቸውን 8 መ | YeneTube

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 738.19 ኪ.ሜ ርዝማኔው ያላቸውን 8 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት ከተለያዩ ስራ ተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል።

በአጠቃላይ ባለስልጣን መስሪያቤቱባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በ43.3 ቢሊየን ብር ወጪ 21 መንገድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ከተለያዩ የሐገር ውስጥና ከውጭ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል።

ከመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ወደ ጎረቤት ሐገር ከሚያስተሳስሩ ፕሮጀክቶች; አንደስላሴ-ራማ ገረሁ ሰናይ ከኤርትራ፣ ዱርቤቴ -ቁንዝላ-መተማ ከሱዳን አንዲሁም ነጌሌ ቦረና-መልካሱፍቱ ከኬንያ አና ከሶማሊያ ይገኙበታል።

@YeneTube @FikerAssefa