Get Mystery Box with random crypto!

በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 እንደሚጀመር ተገለጸ! በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበ | YeneTube

በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 እንደሚጀመር ተገለጸ!

በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በኮሮና ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ከፊታችን የካቲት 1 ቀን 203 ዓ.ም አንስቶ እንደሚጀመር የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በመጀመሪያ በኮሮና ምክንያት በኋላም በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሰለምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮኖ መከላከያ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ ትምህርት መስጠት ይጀመራል።

ወላጆች ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም አቶ አታከልቲ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደባኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @Fikerassefa