Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ለተገደሉ ንፁሃን መንግሥት ማዘኑን ገለፀ፡፡ ‹‹የአንድ ንፁ | YeneTube

በትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ለተገደሉ ንፁሃን መንግሥት ማዘኑን ገለፀ፡፡

‹‹የአንድ ንፁህ ሰው ሞት በራሱ ብዙ ነው›› ሲል መግለጫ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ሆኖም በሕግ ማስከበር ዘመቻው በፌደራሉ መንግሥት በኩል በንፁሃን ላይ የደረሰ ጉልህ ጉዳት አለመኖሩንም ያነሳል፡፡ምክንያት ያለው ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ ሙያዊ ስልቱን ተጠቅሞና ጥንቃቄ በተሞላበት እቅድ ስለተመራ ነው የሚል ነው፡፡የመረጃ ማጣሪያው በትግራይ ሕግ የማስከበር ወቅት በንፁሃን ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ በዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩት መረጃዎች በመረጃ ያልተደገፉና ያልተረጋገጡ ናቸው ሲልም አጣጥሏቸዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን መረጃዎቹ ከፖለቲካ ፍላጎት የመነጩ ስለመሆናቸውም ተከራክሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa