Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲሱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስ | YeneTube

ለአዲሱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የስደተኞች ጉዳይ እንዲሁም ከሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ጋር በተገናኘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከአትላንቲክ ካውንስል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በውይይቱም ይነሱ ለነበሩት በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሰጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡በተለይም በምዕራባዊያኑ በኩል ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ከሞላ ጎደል በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት እየተመለሰ እንደሚገኝ ለሰብዓዊ ድጋፍም ክፍት መሆኑን ማስረዳታቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa