Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Africa
Share
Ethiopia
Scholarship
Austria
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 129.72K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-06-27 13:53:51
ህወሓት “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገብ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ!

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በፓለቲካ ፓርቲነት “በልዩ ሁኔታ” መመዝገብ እንዲችል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ቀረበ። ምርጫ ቦርድ ጥያቄው ከፍትሕ ሚኒስቴር እንደቀረበለት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ፤ ህወሓት “ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን” እንዳረጋገጠ በመጥቀስ የፖለቲካ ፓርቲውን “ህጋዊ ሰውነት” የሰረዘው በጥር 2013 ዓ.ም ነበር።

ቦርዱ በወቅቱ ባስተላለፈው ውሳኔ፤ የህወሓት ኃላፊዎች “በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ” እገዳ መጣሉም ይታወሳል።

የፍትሕ ሚኒስቴር ከሶስት ሳምንት በፊት በፓርላማ የጸደቀን አዋጅ መሰረት በማድረግ፤ ህወሓት “በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ እንዲችል” ምርጫ ቦርድ “አስፈላጊውን ትብብር” እንዲያደርግ በደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።

ከሁለት ቀን በፊት ሰኞ ሰኔ 17፤ 2016 ለምርጫ ቦርድ የተላከው ይህ ደብዳቤ፤ በግልባጭ ለሰላም ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መላኩ ተገልጿል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ መድረሱን የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀረበለትን ጥያቄ “በስራ ላይ ካሉ ህጎች አንጻር በመመርመር ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ” የኮሚዩኒኬሽን ክፍሉ ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
14.0K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-27 10:30:44
የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ ይደረጋል።

@Yenetube @Fikerassefa
14.2K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-27 10:23:01
ለኢንትራንስ ፈተና Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ይዘጋጁ፡፡

አፕሊኬሽኑ ከ2008 - 2015ዓም የኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ እና ከነማብራሪያው የያዘ ሲሆን ፤ እነዚህን ፈተናዎች በቀላሉ መለማመድ የምትችሉበት መንገድ አዘጋጅቷል፡፡

አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric

Telegram channel: t.me/ethiomatric
13.6K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-26 19:54:50
መንግስት በቢራና በትንባሆ ምርቶች ላይ የጣለውን ኤክሳይዝ ታክስ በመከለስ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የክፍያ ምጣኔ ላይ ጭማሪ አደረገ!

የገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ባደረገው ማስተካከያ በቢራ ፣ የትንባሆ እንዲሁም የፕላስቲክ ከረጢት ምርቾች ላይ ጭማሪ አድርጓል።ከአንድ ዓመት በኃላ በተከለሰዉ የኤክሳይዝ ታክስ ላይ ውሃን ሳይጨምር ቢያንስ ከክብደቱ 75% የሚያህለው በአገር ውስጥ ግብዓት የተመረተ ቢራ 30% ወይም 21 ብር በሊትር ከሁለቱ ከበፊቱ 30% ወይም 8 ብር በሊትር ጭማሪ ተደርጎበታል።

የሚፈሉ መጠጦች (ሲዳር፣ ፔሪ፣ ኦፓክ ቢራ፣ የሩዝ አልኮል መጠጥ)፣ የሚፈሉ መጠጦችና የአልኮል አልባ መጠጦች ድብልቅ፣ ስታውት፣ ሌሎች ከቢራ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መጠጦች፣ ዱቄት ቢራ፣ የአልኮል ይዘታቸው ከ7% ያልበለጠ 40% ወይም 28 ብር በሊትር ሲሆን ከበፊቱ 80 በመቶ ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ተመላክቷል። ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ተመርቶ በበቀለ ገብስ የተመረተ ቢራ 35% ወይም 23 ብር በሊትር እንደሆን ሲደረግ ከበፊቱ 35% ወይም 9 ብር በሊትር ብልጫ አሳይቷል።

ከዚህ ቀደም 20 ፍሬ ሲጋራ ሰላሳ በመቶ እና 5 ብር የነበረዉ የክፍያ መጠን በተሻሻለው መመሪያ ሰላሳ በመቶ እና 20 ብር ሲሆን ሌሎች የትንባሆ ምርቶች በኪሎ ግራም ሰላሳ በመቶ እና 250 ብር ከነበነረበት ወደ ሰላሳ በመቶ እና 644 ብር እንዲሆን ተደርጓል።በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) 40 ብር በኪሎግራም የነበረዉ 103 ብር መሆኑን ካፒታል ከመመሪያው መመልከት ችሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
15.7K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-26 18:09:54
"ተሸንፌያለሁ" - ዊልያም ሩቶ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃውሞ ያስነሳባቸውን "የግብር ማሻሻያ" እቅዳቸውን መሰረዛቸውን ለመላው የኬንያ ህዝብ አሳውቀዋል። ህዝብን ልመራ ነው የተመረጥኩት፣ ህዝብ ከተቃወመኝ ማዳመጥ አለብኝ። "ተሸንፌያለሁ።

ሀሳቤን ሰርዢያለሁ" ብለዋል። አዲሱ የግብር ማሻሻያ በኬንያ ፓርላማ በ195 አብላጫ ድምፅ እና 106 ተቃውሞ አድፅቆ ለዊሊያም ሩቶ መላኩ ይታወሳል። በዚህ ምክንያት በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፓርላማው የፀደቀውን የግብር ማሻሻያ ሰርዘናል፣አልፈርምም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
15.5K viewsedited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-26 13:53:35 ውድ ኢትዮጲያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነት ያላቸው እና ዝቅተኛ አመታዊ ክፍያ የሚያስከፍሉ ዘመናዊቷ አውሮፓ ውስጥ ካሉ 10 የኦስትሪያ ሀገር( Austria) ዩኒቨርስቲዎች ከነ ሊንካቸው አስቀምጣለሁ እንደተለመደው የትምህርት ዶክመንታችሁን አሰናድታችሁ እንድትሞክሩ አበረታታለሁ፣ ይህ መረጃ #ነፃ ስለሆነ ለቤተሰብ ወይም ጓደኛ አካፍሏቸው #share

1. University of Vienna
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://studieren.univie.ac.at/en/admission/)

2. Graz University of Technology
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.tugraz.at/en/studying-and-teaching/degree-and-certificate-programmes/admission-and-registration/)

3. University of Graz
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://studienabteilung.uni-graz.at/en/international-students/degree-programmes/)

4. Johannes Kepler University Linz
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.jku.at/en/degree-seeking-students/admissions-office/)

5. University of Innsbruck
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.uibk.ac.at/studium/angebot/aufnahmeverfahren/)

6. University of Klagenfurt
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.aau.at/en/study/studying-at-the-university-of-klagenfurt/)

7. Vienna University of Technology (TU Wien)
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.tuwien.at/en/studies/admission/international-students)

8. University of Salzburg
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.uni-salzburg.at/index.php?id=41830&L=1)

9. University of Applied Arts Vienna
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.dieangewandte.at/en/studies/study_programs/admission_procedure)

10. Medical University of Vienna
- Tuition Fee: Approximately €1,500 per year for non-EU/EEA students
- [Official Registration Link](https://www.meduniwien.ac.at/web/en/studies-further-education/international/)

These links will direct you to the official admission or registration pages of each university, where you can find detailed information on the application process, requirements, and deadlines. Make sure to review each university's specific instructions and requirements for international students.

#austria #ethiopia #africa #scholarship
15.2K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-26 13:38:23
ፖለቲከኛው ጃዋር መሃመድ የመከላከያ ጄነራሎች ለድርድር ለመቀመጥ ለፋኖ ያደረጉትን ጥሪ፣ የፋኖ አመራርና የአማራ አክቲቪስቶች እንደበጎ እርምጃ እንዲመለከቱትና ለጥሪው ምላሽ ቢሰጡ ለሰላም አማራጭ ይሆናል ሲል በግል የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

መከላከያ ሰራዊት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ያለ አንዱ የመንግሥት ተቋም ነው ብሏል።

መከላከያው እየተፈጠረ ያለውን ችግር በቅርበት የሚያውቅ በመሆኑ፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ጥሪ ማቅረቡ መበረታታት አለበት ብሏል። ከኦነግ ሸኔ ጋርም ሰላም ለመፍጠር ለሁለት ጊዜ የተደራደረው መከላከያው ነው ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
12.0K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-26 13:31:03
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ የዛይሴ ማህበረሰብ አባላት ላይ ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘፈቀደ እሥርና ወከባ እየተፈጸመ ይገኛል ሲሉ ነዋሪዎችና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለፁ፡፡

የዞኑና የወረዳው የፀጥታ አባላት ሰሞኑን በሌሊት ቤት ለቤት በመዘዋወር ወጣቶች ፣ ሴቶች እና ቀሳውስትን ጨምሮ 112 የማህበረሰቡ አባላትን ማሠራቸውን ነው ነዋሪዎቹና የምክር ቤቱ አባላት ለዶቼ ቬለ የተናገሩ፡፡የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የዘፈቀደ እሥርና ወከባው እየተፈጸመ የሚገኘው በወረዳው ዛይሴ ደንብሌ ፣ ዛይሴ ኤልጎ እና ዛይሴ ወዘቃ በተባሉ የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው፡፡

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃፌ ቃፊሬ “ እከሌ እንደዚህ ታሠረ እከሌ እንደዚህ ሆነ ብዬ የምሰጠው ምላሽ የለም “ ብለዋል ፡፡ ምላሽ መስጠት ያልፈለጉበትን ምክንያት አሁንም በዶቼ ቬለ የተጠየቁት ዋና አስተዳዳሪው “ ለእኛ ያልቀረበ ጥያቄ እናንተ [ ዶቼ ቬለ ] ጋር ሲመጣ መቀበል አልነበረባችሁም ፡፡ አሁን እኔ መረጃውን የምሰጠው ቅሬታ አቅራቢዎቹ መጀመሪያ እኔ ጋር ቀርበው ካመለከቱ በኋላ ነው “ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ሲል ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
12.3K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 12:29:15
አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ እንደተለያየ አሰልጣኙ ሩላኒ ሞክዌና ተናግረዋል

"ስለ አቡበከር ናስር መናገር አልፈልግም እሱ የሰንዳውንስ ተጫዋች አይደለም።" ብለዋል

ምንጭ : Transfer Market VIA Power Fm
9.9K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 12:05:48 #ሰበር #መረጃ

"የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ፍሰሃ ተሰደዱ"

"ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለደህንነታችን የሰላም ዋስትና እንዲሰጡን እንጠይቃለን" ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ

በጥቂት ግዜ ውስጥ ከፍታኛ ሀብት ማፍራት የቻለው የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮ CEO ለ #ፋኖ ሀይል ድጋፍ ታደርጋላችሁ፣ ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር እንዲሁም በህገወጥ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ በማስመሰል  እና የሀይማኖትና የቤሄር ግጭት ለመፍጠር መንቀሳቀስ የሚሉ ክሶች ቀርቦባቸው ከሀገር መሰደዳቸውን አሳውቀዋል።

ዶክተር ፍሰሃ ዛሬ በአሜሪካ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል
"ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ እየደረሰበት ያለበትን ግፍ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ያውቃሉ ብየ አላምንም" ያሉት ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ በሰላም ሰርተን ለሀገርም ተስፋ እንድንሆን እንዲያግዙን እንጠይቃለን ብለዋል።

የፐርፐዝብላክን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከአሜሪካ መግለጫ የሰጡት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ፤  የቀረበብን ክስ ከእውነት የራቀ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) አውቀው በሰላም እንድንሰራና ለሚሆነው ነገር ምላሽ እንዲሰጡን ሲሉ  ዶ/ር ፍሰሃ ጠይቀዋል።

ለሀገር የምናስገኘውን ኢኮኖሚያዊ እድገት በመረዳት ትክክለኛውንና ተገቢውን ምላሽ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለፐርፐዝብላክ ምላሽ እንደሚሰጡ ተስፋ እንደሚያደርጉም  ዶ/ር ፍሰሃ ተናግረዋል

Via:- አዩ ዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
10.3K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ