Get Mystery Box with random crypto!

የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማ | YeneTube

የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ።

በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ፤ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር )
@YeneTube @FikerAssefa