Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ 32 ሺህ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተባለ፡፡ የክረምት ወር መግባቱን | YeneTube

በአዲስ አበባ 32 ሺህ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተባለ፡፡

የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎችና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በአሁኑ ሰዓት በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተው ታውቀዋልም ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወ/መስቀል እንደተናገሩት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በመዲናዋ በወንዝ ዳር የሚኖሩ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ዜጎችን ከአካባቢው በማንሳት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማዛወር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡መሥሪያ ቤታቸው ሰባት ከሚሆኑ ባለድርሻ መስራቤቶች አካላት ጋር በመሆን ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ለጎርፍ አደጋ መባባስ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ችግሮች ሲገልጹ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተቆፋፍረው ክፍት የተተዉ ጉድጓዶች፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችና ወንዞች ላይ ተረፈ ምርቶችንና ቆሻሻዎችን መጣል በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡እነዚህ ችግሮች በሁሉም አካባቢ በመለየት አሁን ላይ የስራ ክፍፍል ተደርጎ ቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa