Get Mystery Box with random crypto!

በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች! ከአ | YeneTube

በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች!

ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 2014 ቦርኖ ከምትባለው ከተማ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች 276 ተማሪ ሴቶችን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው አፍነው መውሰዳቸው ይታወሳል።

እነዚህ የቺቦክ ትምህርት ቤት ሴት ልጆች መታገት መላው ዓለምን አስደንግጦ በወቅቱ የአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት የነበሩትን ሚሼል ኦባማን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የማስለቀቅ ዘመቻ እንዲጀመር ምክንያት ሆኖ ነበር።

ታፍነው ተወስደው ከነበሩት 280 ከሚጠጉት ልጃገረዶች መካከል አስካሁን ድረስ 100 የሚሆኑት በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር ናቸው ወይም የደረሱበት አልታወቀም።ትናንት ሐሙስ ደግሞ የናይጄሪያ ሠራዊት ከአስር ዓመት በፊት ከታፈኑት ተማሪዎች መካከል አንዷን ከሦስት ልጆቿ ጋር ከታጣቂዎቹ ነጻ ማውታቱን አስታውቋል።

ታጋቿ ሦስት ልጆቿ በተጨማሪም የአምስት ወራት ነፍሰ ጡር መሆኗን ሠራዊቱ ገልጿ።በቦኮ ሃራም ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ ሴት ተማሪዎች መካከል አስካሁን ከ180 በላይ የሚሆኑት በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ውስጥ ከምትገኘው ቦርኖ ግዛት የቡድኑ መደበቂያ ሳምቢሳ ጫካ በፀጥታ ኃይሎች ነጻ ወጥተዋል ወይም ከቡድኑ አምልጠዋል።አስካሁን ከቡድኑ ነጻ ከወጡ ልጃገረዶች መካከል አንዳንዶቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ማርገዛቸው ወይም ልጅ መውለዳቸው ተዘግቧል።

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ጠልፈው የሚወስዷቸውን ተማሪዎች በወሲብ ባርነት ስር ያቆይዋቸዋል የሚሉ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲወጡ መቆየታቸው ይታዋል።ወደ ቤታቸው ከተመለሱት መካከልም የተወሰኑት የናይጄሪያ ባለሥልጣናት የሚያስፈልጋቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ እንዳላደረጉላቸው በመግለጽ መንግሥትን ይታቻሉ።በናይጄሪያ ውስጥ አሁንም የጅምላ አፈና ተማሪዎችን እና ወላጆችን የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa