Get Mystery Box with random crypto!

'ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . .' ይህንን ያለው 9,0 | YeneTube

"ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ."

ይህንን ያለው 9,000 ሰው ተሰብስቦ በሚመለከተው የቲክቶክ ሽምግልና ላይ ነው።

ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ የተባለ ታማሚ ግለሰብ የተለያዩ ታዋቂ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" ብሏል።

Via: ስንታየሁ ኃይሉ
@Yenetube @Fikerassefa