Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ። የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን | YeneTube

የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ።

የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል::

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል::

ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው::

የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል::

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

@Yenetube @Fikerassefa