Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube Y
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.12K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 487

2021-02-05 17:21:26 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች ሁኔታ ላይ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች እና ሌሎች እስረኞችንም ሁኔታ ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ በመገኘት እስረኞቹን የጎበኘ ሲሆን፣ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ በተጨማሪም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ አያያዝ ላይ ክትትል አድርጓል። በክትትሉም ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና ከቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ ቤት አስተዳደሮች እንዲሁም ከእስረኞቹ ጋር ተነጋግሯል።

ኢሰመኮ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተገኘበት ወቅት፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ከጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ ነበሩ። የረሃብ አድማው ዓላማ “መንግስት በሕዝብ እና በፓርቲያቸው ላይ እያደረሰ ያለውን አፈና እና የመብት ጥሰት ለመቃወም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያናን አላግባብ የሆነ አያያዝ እና እንግልት እንዲቆም ለመጠየቅ እና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ እና እነሱን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ” መሆኑን እስረኞቹ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ ለረሃብ አድማው በምክንያትነት የተጠቀሱ አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ማረሚያ ቤቱን የማይመለከቱ መሆኑንና እስረኞችን ለመጠየቅ የሚመጡ ሰዎች ላይ ወከባ እንደማይፈጽም ገልጿል። አስተዳደሩ አክሎም የረሃብ አድማው በእስረኞቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል፣ በተለይም ከመካከላቸው ሁለቱ የጤና ችግር ስላለባቸው በቋሚነት መድኃኒት የሚወስዱ በመሆኑ ቅርብ የህክምና ክትትል እንደሚደረግላቸው አስረድቷል። ኢሰመኮ በቦታው በነበረበት ወቅት የተባለው ህክምና ክትትል እንደሚደረግ በምልከታ ለማረጋገጥ ችሏል።

በሌላ በኩል፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ ተቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ ቪዲዮ ፊልም ጋር በተያያዘ ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል የተባሉትን ኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ ደኅንነትና አያያዝ ሁኔታ ኮሚሽኑ አጣርቷል። ሁለቱም ታሳሪዎች በደኅንነት ላይ እንደሚገኙና አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው አረጋግጧል። ሆኖም ግን ኮሎኔል ገመቹ አያና ከዚህ በፊት ከነበረበት የእስር ክፍል (ዞን) እንዲወጣ ተደርጎ ‹‹ለደህንነቱ ምቹ ወዳልሆነ የእስር ክፍል (ዞን) እንዲዛወር መደረጉን›› እና ከዚህም በፊት በተደጋጋሚ ከቦታ ቦታ በመዘዋወሩ የደረሰበትን እንግልት በሚመለከት ቅሬታውን ለኮሚሽኑ አስረድቷል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በበኩሉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የእስረኞች ክፍል (ዞን) ዝውውር ሊደረግ የሚችል መሆኑን ገልጾ፤ ኮሎኔል ገመቹ የተዛወሩበት የእስር ክፍል (ዞን) ሌሎች እስረኞችም የሚገኙበት መሆኑን ይገልጻል። ኮሚሽኑም በጉብኝቱ ወቅት የማረሚያ ቤቱን ደንብ በመተላለፍ ምክንያት ወደዚህ የእስር ክፍል (ዞን) መምጣቱን የገለጸ አንድ ታሳሪ መኖሩን ኢሰመኮ ተመልክቷል፡፡

ኢሰመኮ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የሰጠውን ምክረ ሃሳብ ተከትሎ፣ አስተዳደሩ እስረኛውን ወደ ሌላ ዞን ለማዛወር በዝግጅት ላይ የነበረ ቢሆንም፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት እስረኛው ከቂሊንጦ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዛወሩ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ ወደ ቂሊንጦ እንዲመለስ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት፣ ከጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስረኛው በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት የሚገኝ መሆኑን ኢሰመኮ እስረኛውን በመጎብኘት አረጋግጧል።

በተመሳሳይ መልኩ፣ ኢሰመኮ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥሮ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘውን የአቶ ጥላሁን ያሚን ደኅንነትና አያያዝ አጣርቷል። እስረኛው በሙሉ ደኅንነት የሚገኝ ሲሆን በማሕበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ቪዲዬ ተከትሎ ከማቆያ ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይወጣ ከመደረጉ በስተቀር በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ እያለ ድብደባም ሆነ ሌላ አይነት የመብት ጥሰት ያልተፈጸመበት መሆኑን አስረድቶ፣ ነገር ግን ከዚህ ቀደም በፖሊስ ጣቢያ በምርመራ ወቅት የነበረውን ተገቢ ያልሆነ አያያዝ በተመለከተ ለኢሰመኮ ቅሬታውን አስረድቷል ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞችን አስመልክቶ፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የእስረኞቹ ጤንነትና ሕይወት የከፋ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞችን ጠያቂዎች በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል›› በማለት ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.9K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 16:09:06
ዋልያ ለችግረኛ ወገኖች የተገነቡ ባለ ሰባት ብሎክ 53 ቤቶችን ለባለቤቶቹ አስረከበ

በአዲስ አበባ ከተማ ጎልተው ከሚታዩ ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ደረጃውን የጠበቀ መኖርያ ቤት ችግር ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር በተባለው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ግድግዳው እና ጣሪያው ከቆርቆሮ በተሠራ ቤት ላለፉት 40 ዓመታት ኖረዋል፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ብቻ ሳይሆን ኩሽና እና መጸዳጃ ቤታቸውም ከቆርቆሮ ተሠርቶ ለረጅም ዘመን በማገልገሉ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር፡፡
ሃይንከን ኢትዮጵያ/ዋልያ ቢራ ይህን ችግር በመረዳት እነዚህን ባለሰባት ብሎክ 53 ቤቶች፣ ኩሽና እና መጸዳጃ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ደረጃውን በጠበቀ የብሎኬት ቤት ተክቶታል፡፡ ግንባታው በሁለት ወራት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ 8.4 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.1K viewsedited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:57:52
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ ደረሰ!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።ሚኒስቴሩ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትንና የህዳሴ ግድቡን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።ግድቡ ለተፋሰሱ አገሮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ኢንጂነር ስለሺ፤ “የግድቡ ግንባታ ሰኔ ወር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም የ4 ነጥብ 05 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
11.2K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:55:57
አምቦ ከተማ ተማሪዎች ሰልፍ ወጥተዋል!

አምቦ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ተማሪዎች፤ ፍትህ ለሀጫሉ፣ የታሰሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ፣ እና ሌሎች መፈከሮችን በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የአዲስ ዘይቤ መረጃ ያመለክታል። ሆኖም ሰልፉ ብዙም ሳይቆይ ተማሪዎቹ በፖሊስ ሀይሎች እንደተበተኑ እና አንዳዶችም እንደታፈሱ ከአይን እማኛችን ለማረጋገጥ ተችሏል።አዲስ ዘይቤ አምቦ ያለውን የፖሊስ ቢሮ ለማነጋገር ሙከራ ያደረገ ቢሆንም "ስብሰባ ላይ ነን አሁን ማናገር አንችልም" የሚል ምላሽ አግኝቻለው ብላለች።

@YeneTube @FikerAssefa
10.4K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:49:04
ስልሳ ስምንት ዜጎች ከሊባኖስ ቤይሩት ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ስልሳ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ ቤይሩት በፍሪደም ፈንድ እና አጋር ኢትዮጵያ በተባሉ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች አማካኝነት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:01:45
የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ”ይጠይቁ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የማህበራዊ ሚዲያ የተሳትፎ መድረክ ለቀረቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገጽ በቀጥታ ምላሽ ሰጥተዋል።

የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው በምን አይነት መልኩ ይሳተፋሉ? በሚል ከተሳታፊ ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው ላይ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ቦርዱ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል። ዜጎቹ ባሉበት ቦታ ሆነው የሚመዘገቡበትና ከመጡበት አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ምርጫውን የሚያደርጉበት ሁኔታ መመቻቸቱን አመልክተዋል።

ምርጫ ቦርድ የተፈናቀሉት ዜጎች የሰጡትን ድምጽ ከመጡበት አካባቢ ሰዎች ከሚሰጡት ድምጽ ጋር የሚደመርበት የውጤት ማስላት ዘዴ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። በአዲስ መልክ ዜጎች የተፈናቀሉባቸው ቦታዎች በመኖራቸው የወቅቱን መረጃዎች ማወቅ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ የሰላም ሚኒስቴርና የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) የሚያወጧቸውን መረጃዎች መሰረት በማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የተፈናቀሉ ዜጎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላና ሌሎች በተጓዳኝ የሚከናወኑ ስራዎች የሚመሩበት እቅድ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

[Arts TV]
@Yenetube @FikerAssefa
13.8K viewsedited  12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 14:52:27
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 117 ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 5 ሺህ 117 ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ጥር 29/2013 ዓ.ም በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና ፖስት ግራጁዬት ዲፕሎማ ያስመርቃል፡፡በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ብቻ ጠርቶ በ15 አካዳሚክ ክፍሎች ማካካሻ ትምህርት ሲሰጥ እንደቆየ ነው የዩቨርሲቲው የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮምዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውዱ እምሩ (ዶክተር) የተናገሩት፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
10.3K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 13:23:51
በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር ውሏል ተባለ!

የተባሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ፡፡የድርጅቱ የክትትል ቡድን ትናንት ሃሙስ ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ካሊድ ባታርፊ በቁጥጥር ስር ከዋለ መቆየቱን ጠቁሟል፡፡ባታርፊ ከዓመት በፊት ነበር የሽብር ቡድኑን እንዲመራ የተመረጠው እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ፡፡ምክትሉ ሰዓድ አቲፍ አል-አውላቂ አል ማህራህ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ጋይዳ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ዘመቻ መገደሉንም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በኦሳማ ቢን ላደን እና አጋሮቹ መመስረቱ የሚነገርለት አልቃይዳ የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ በአሜሪካ እና በሌሎችም ሃገራት በሽብርተኝነት መፈረጁ የሚታወስ ነው፡፡ቢንላደን አሜሪካ በባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ባካሄደችው ዘመቻ በፓኪስታን አቦታባድ መገደሉም አይዘነጋም፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
10.6K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 13:20:18
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳዳር ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ጠንካራ ትስስርን እንደገና ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡

በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ገለፃ ካደረጉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ባይደን ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያለውን ትስስር እንደገና እንደሚገነቡት ቃል ገብተዋል፡፡ቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ ከ2 ዓማት በፊት ‹‹አፍሪካዊያንን የማይረቡ አገራት ያሉበት አኅጉር›› ሲሉ መግለፃቸው ቁጣን ቀስቅሶ እንደነበርና ኅብረቱን ከዩናይትድ ስቴትስ ማራራቁ ይታወቃል፡፡ምንም እንኳን ትራምፕ ‹‹እኔ ዘረኛ አይደለሁም›› ሲሉ ሊያስተባብሉ ቢሞክሩም በተግባር ግን ለጥቁር ቆዳ ቀለም ሕዝቦች ያላቸው ጥላቻ በተለያየ ጊዜ ሲገለጥ ኖሯል፡፡ነጩን ቤተ መንግሥት የተረከቡት ባይደን ግን ከኅብረቱ ጋር የነበረውን ጠንካራ ትስስር እንደሚመልሱት ነው የገለፁት፡፡ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኅብረቱ በአኅጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን በመፍታት ጠንካራ እንዲሆን እገዛ እንደሚያደርጉ ነው ያሳወቁት፡፡ዩናይትድ ስቴትስና አፍሪካ በባራክ ኦባማ ዘመንም ጠንካራ ትስስር ነበራቸው፡፡

Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
10.1K viewsedited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 13:13:45
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ለዘንድሮው ምርጫ 435 የምርጫ ወረዳዎች ማቋቋሙን ይፋ አደረገ፡፡

ፓርቲው በዘንድሮ አመት ለሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ እያከናወነ ያለውን ተግባር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፓርቲው በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች መዋቅሩን የመዘርጋት ስራ እያከናወነ መሆኑን የተናገሩት የኢዜማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ ፓርቲው በዘንድሮ አመት የሚካሄደው ምርጫም ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲዊ ምዕራፍ ያሸጋግራታል ብሎ እንደሚያምን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ አስፈላጊውን ሁሉ የምርጫ ፓርቲው እያከናወነ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ከ435ቱ የምርጫ ወረዳዎች በ406ቱ የምርጫ ወረዳዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለክልል ምክር ቤት እና ለወረዳ የሚሳተፉ እጩዎች አስመርጦ ማጠናቀቁንም አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡

ለሚካሄደው ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን የገንዝብ ድጋፍ ፓርቲው እያሰባሰበ መሆኑን የሚናገሩት የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዱአለም አራጌ በማዕከል ደረጃ ብቻ 140 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኪራይ ያገኘውንና በ5 ሚሊየን ብር እድሳት የተደረገለትን የፓርቲውን ዋና ጽህፈት ቤት ፓርቲው ይፋ አድርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
13.3K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ