Get Mystery Box with random crypto!

በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር ውሏል ተባለ! የተባሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የአልቃይ | YeneTube

በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር ውሏል ተባለ!

የተባሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ፡፡የድርጅቱ የክትትል ቡድን ትናንት ሃሙስ ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ካሊድ ባታርፊ በቁጥጥር ስር ከዋለ መቆየቱን ጠቁሟል፡፡ባታርፊ ከዓመት በፊት ነበር የሽብር ቡድኑን እንዲመራ የተመረጠው እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ፡፡ምክትሉ ሰዓድ አቲፍ አል-አውላቂ አል ማህራህ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ጋይዳ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ዘመቻ መገደሉንም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በኦሳማ ቢን ላደን እና አጋሮቹ መመስረቱ የሚነገርለት አልቃይዳ የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ በአሜሪካ እና በሌሎችም ሃገራት በሽብርተኝነት መፈረጁ የሚታወስ ነው፡፡ቢንላደን አሜሪካ በባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ባካሄደችው ዘመቻ በፓኪስታን አቦታባድ መገደሉም አይዘነጋም፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa