Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube Y
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 128.55K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 491

2021-02-04 11:26:51 አልማ በዚህ አመት መጨረሻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርቼ አስረክባለው አለ።

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከተመሰረተ ጀምሮ የአባላቱን ቁጥር እየጨመረ የተለያዩ ስራዎችን እንደሰራ ይገለጻል።

በተለይም በትምህርት በጤና እና ስራ ፈጠራ ዘርፎች የሰራው ስራ ተጠቃሽ ነው።

የአማራ ልማት ማህበር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች 84 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና ደረጃቸውን ጥሩ ለማድረግ በዘንድሮው አመት ብቻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርተን እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የሚሰሩትም በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ሲሆን መማሪያ ክፍሎቹም ከመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እስከ መሰናዶ ላሉት አገልግሎት ይሰጣል ስለመባሉ ተሰምቷል።

የአማራ ልማት ማህበር በአሁኑ ሰአት 4.7 ሚሊየን አባላት እንዳሉት ገልጿል።

የአባላቱ ቁጥር ሲጨምርና የሀብት መጠኑ ሲያድግ በማህበራዊ ሀላፊነቶችም የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ በተሰራው ስራና በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
12.3K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 10:05:48 የአውስትራሊያ መንግስት በኮቪድ የተያያዘ አንድ ግለሰብ ማግኘቱን ተከትሎ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ እገዳ መጣሉ ተሰምቷል ።

ባለፈው ሰኞ በምዕራባዊው አውስትራሊያ ፔርዝ ከተማ ሪፖርቱ ይፋ የተደረገ ሲሆን መንግስት ለ5 ቀን የሚቆይ ጥብቅ እገዳ ማስተላለፉን ሮይተርስ ዘግቧል ።

በቫይረሱ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ቀረቤታ ነባራቸው የተባሉ 13 ሰዎችም በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
አውስትራሊያ ኮቪድ 19 በመከላከል ውጤታማ ስራዎችን የሠራች አገር ስትሆን እስካሁን 29 ሺህ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ 909 ሰዎች ደግሞ ህይዎታቸውን አጥተዋል ።

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሁሉም ዜጎች ክትባት እንዲያገኙ እየሠራን ነው ብለዋል።

አሁን ላይ አውስትራሊያ 4.4 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ 26 ሚሊየን ዜጎቿን ለመከተብ እየሠራች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ተጨማሪ 1.9 ቢሊዬን ዶላር ያስፈልገናል እያሉ ይገኛሉ።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
11.8K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 09:26:54 የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ ተዳርጓል!

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ሕገወጥ ተግባራትና በአመራር ዝርክርክነት ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ መዳረጉ ተገለፀ። ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኦዲት አለመደረጉም ተጠቆመ።በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት መምህርና በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ጥናት ያደረገው ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ቱሉ ቶላ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል።በዚህ ጊዜ ውስጥም ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።

ግንባታው ከፍተኛ የሀገሪቱ ሀብት የፈሰሰበት ቢሆንም በሕግና በሥራት የሚመራ አልነበረም የሚሉት ዶክተር ቶላ፤ በዚህ የተነሳ ለከፍተኛ የአሠራር ብልሹነትና የገንዘብ ዕዳ መዳረጉን አመልክተዋል።ቡድኑ ባደረገው የማጣራት ሂደት ለግለሰቦች የተላለፈበት መንገድ ያልታወቀ፣ መረጃ ያላቀረቡ፣ ዝግ የሆኑ፣ ባዶ ቤቶችና መሰል ችግሮች መለየታቸውን ጠቁመው፣ በከተማዋ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት እያለ ለ11 ዓመታት ዝግ ሆነው የቆዩ ቤቶች እንደነበሩም ጠቁመዋል። ከዚህም ባሻገር 21 ሺህ የሚሆኑ ቤቶች በማን እንደተያዙ ምን አይነት መረጃ ያልቀረበባቸው እንደነበሩም አስታውቀዋል።ቤቶቹ በዚህ መልኩ እንዲባክኑና ለሙስና እንዲዳረጉ የተደረገው ሆን ተብሎ ነው የሚሉት ዶክተር ቱሉ፣ ለዚህም ቤቶቹ መረጃ እንዳይኖራቸው ማድረግ አንዱ የሌብነት ስልት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት 85 ከመቶ የሚሆኑ ቤቶች ምንም አይነት የቤት መግለጫ የሌላቸው እንደሆኑ አመልክተዋል።በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከህብረተሰቡ የሚሰሙ ሮሮዎች የቆዩ መሆናቸውን የሚናገሩት ዶክተር ቱሉ፣ ሆኖም በዚህ ደረጃ ችግሩ ሥር የሰደደ ስለመሆኑ ግንዛቤ አልነበረንም።ጥናት በምናደርግበት ወቅትም ሀገሪቷ በምን አይነት ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደነበረች ማየት ችለናል ብለዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
15.0K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 09:00:24 ወደ መቀሌ ተልኮ መደረሻው ሳይታወቅ የቆየው 1.3 ቢሊየን አዲሱ ብር ተገኘ!

አሁን በምርጫ ቦርድ ተዘርዞ ህልውናው እንዲከስም የተደረገው ቀድሞ የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እና በማዕከላዊው መንግስት መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰ ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2013 አ.ም ምሽት ወደ ትግራይ መቀሌ በአሮጌው ብር እንዲቀየር በብሄራዊ ባንክ በአውሮፕላን የተላከው አዲሱ 1.3 ቢሊየን ብር መዳረሻው መታወቁን ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።

ከምንጫችን እንደሰማነው በአሮጌው ብር እንዲቀየር የተላከው 1.3 ቢሊየን ብር መቀሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ክፍል ውስጥ ታሽጎ ነው የተገኘው።

ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል በተባለበትና ግጭቱ ወደለየለት ጦርነት በተሸጋገረበት በዚያ ዕለት አሮጌውን የብር ኖት እንዲተካ የተላከው ብር መዳረሻ አልታወቀም ነበር።

በወቅቱም መንግስት ገንዘቡን በትግራይ ክልል ላሉ የተለያዩ ባንኮች አከፋፍያለሁ ብሎ በብሄራዊው የቴሌቭዥን ጣብያ ማስነገሩ ይታወሳል። ማይጨው ፣ አደዋ ፣ሽሬ እንዳስላሴ እና አዲግራት ላሉ የተለያዩ ንግድ ባንኮች ብሩ ተከፋፍሏል ተብሎም ነበር። ሆኖም በወቅቱ በክልሉ ከነበረው ሁኔታ አንጻርና እንደተባለውም ብሩ በክልሉ ላሉ የባንክ ቅርንጫፎች እንዳልተከፋፈለ ዋዜማ ራዲዮ ከታማኝ ምንጮቿ አረጋግጣ መዘገቧ ይታወሳል።

የ1.3 ቢሊየን አዲሱን ብር እጣ ፈንታም የፌዴራል መንግስት የመቀሌ ከተማን ከተቆጣጠረም በሁዋላ በመቀሌ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ አዲስ ስራ እንኪጀምር አላወቀም ነበር ብለውናል ምንጫችን። ሆኖም ከሳምንታት ወዲህ በመቀሌ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫ እንደገና ስራ ሲጀምር ነው የቅርንጫፉ ሰራተኞች ብሩን በአንድ ክፍል ታሽጎ ያገኙት። ገንዘቡ ሲገኝም የመጠን ቅናሽ እንዳልነበረው ከምንጫችን መረዳት ችለናል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በክልሎች ብርን ለማሰራጨት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን በማእከልነት እንደሚጠቀም ይታወቃል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @Fikerassefa
14.5K viewsedited  06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 08:59:59
ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join

@giftsoflovee
@giftsoflovee

+251914839754
+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
4.1K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 08:59:59
የዋሪት የውሀ ማጣሪያ ከ15% ልዩ ቅናሽ ጋር

ሰብስቤ www.sebsibie.com በመግባት መገበየት ይችላሉ።

ሰብስቤ ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

0953707070

Dedicated online shopping platform
5.9K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 20:18:40 በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገጽታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩት ቡድኖችን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣አሸባሪዎች ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እና ለፍንዳታ ሥራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል እና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ ዓሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለዓሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረው እና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲያሴር የቆየው መሐሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች እና ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል።

ሌላ ተመሳሳይ ተልእኮ የተሰጠው ቡድን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ነው።

የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣት እና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል።

ከአውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስዊዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
17.2K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 19:56:32 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ለማሳየት የተለያዩ ሰልፎች መካሄዳቸው ይታወቃል። እነዚህን ሰልፎች ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) “ፓርቲያችን ያለአግባብ ተወንጅሏል፣ ይህም ፓርቲዎች የፈረሙትን የጋራ የስነምግባር ደንብ የጣሰ ነው” ሲል አቤቱታውን ለቦርዱ አቅርቧል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከአቤቱታው በተጨማሪ በእለቱ የተደረጉ የተለያዩ ሰልፎችን በሚዲያ ክትትል ክፍሉ አማካኝነት ክትትል በማድረግ በአሜሪካ ድምጽ፣ በዋልታ፣ በፋና፣ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ እንዲሁም በነዚሁ ሚዲያዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ የተላለፉ መልእክቶችን በማየት
- ሠልፎቹ በዋልታ ቴሌቪዥን እና በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በቀጥታ መተላለፋቸውን እንዲሁም የመንግስት አመራር አካላት፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች መሳተፋቸውን ተረድቷል።
- ከሚዲያዎቹ በቀጥታ ከመተላለፉም በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት አመራር አባላት በሰልፎቹ ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች ተመልክቷል።
- በሰልፎቹ የተለያዩ መፈክሮች፣ በተወሰኑ የመንግስት የዞን፣ የከተማ አስተዳድር አመራር አካላት እና ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊዎች ንግግሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ እና የምርጫ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ፓርቲዎች በአሉታዊ መልኩ መነሳታቸውን ተገንዝቧል።

እነዚህ ሰልፎቹ ላይ የተነሱ ንግግሮች እና መፈክሮች በህጋዊነት ተመዝግበው፣ በፖለቲካ ፓርቲነት የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን ማለትም አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በአመፃ ተግባር በመሳተፍ ከምርጫ ቦርድ ከተሰረዘው ጁንታ በማለት ከሚጠሩ ህወሃት ፓርቲ ጋር አንድ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብሎ በመፈረጅ እና ህገወጥ ናቸው በማለት የምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 ላይ ያሉ ድንጋጌዎችን ጥሰዋል።

ቦርዱ ሰልፎቹ ላይ የተንጸባረቁት ንግግሮች እና መፈክሮች በአዋጁ አንቀጽ 132 ንኡስ 2(ሀ) ላይ የተጠቀሰውን ስም የሚያጠፋ ንግግርን ክልከላ ድንጋጌ አንዲሁም በዚሁ ህግ አንቀጽ 143 (2) ላይ የተጠቀሰውን ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳያሰራጩ ስጋት እና ፍርሀት የመፍጠር የስነምግባር ጥሰት ፈጽሞ አግኝቶታል። ከዚህም በተጨማሪ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ገዥው ፓርቲ በጋራ ተስማምተው በፈረሙት የቃልኪዳን ሰነድ አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሰውን “የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በየትኛውም ጉዳይ ላይ ሊኖር የሚችል የዓላማ፣ የሃሳብ ወይም የዘር ልዩነትን፣ ወይም ሌላ ምክንያት መሰረት በማድረግ የሌሎች ፓርቲዎችን መብቶች የሚፃረሩ ወይም የሚያጣብቡ ድርጊቶችን ከመፈፀም የመቆጠብ ግዴታ አለባቸው” የሚለውን አንቀጽ የሚጥስ ተግባር ነው።

ይህ ተግባር በተለይ ቦርዱ የመጨረሻ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ የምርጫ ተግባራት በይፋ መፈጸም ከጀመረ በኋላ በምንገኝበት የምርጫ ወቅት መከሰቱ በምርጫ ውድድር ላይ ፓርቲዎች በእኩልነት የመወዳደር መብታቸውን ችግር ላይ የሚጥል በመሆኑ ቦርዱን በእጅጉ አሳስቦታል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ያሉ የገዥው ፓርቲ አመራሮች እና በየአስተዳደር እርከኑ ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች በተመሳሳይ ተግባራት ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ያሳውቃል።

ለወደፊትም በተመሳሳይ በምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 እና ተያያዥ መመሪያዎች መሰረት የፓርቲዎች የቅስቀሳ የንግግር እና ሌሎች ለህዝብ የሚያሰራጯቸውን መልእክቶች ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እስከእጩ መሰረዝ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
13.3K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 19:00:56 የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚወያይ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የተመድ ሰብዓዊ ሁኔታዎች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ስላለው ሰብዓዊ ሁኔታ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጉዳዩ ለሦስተኛ ጊዜ ውይይት እንዲደረግበት ሃሳብ ካቀረቡት የምክር ቤቱ አባል ሀገራት መካከል፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ይገኙበታል፡፡ ጉዳዩ እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ “ሌሎች ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ስር የተያዘ ሲሆን፣ በውይይቱ ማብቂያ መግለጫ ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
12.8K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 18:05:10
ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ።

የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይ የበላይ ጠባቂ ሆኖ በዋና ዋና የአማዞን ጉዳዮች ብቻ መሳተፍ ብቻ እንደሚፈልግ ገልጿል።

'የአማዞን ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መሥራት ፋታ የለውም። ጊዜና ጉልበትን ያሟጥጣል። እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ላይ መሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማተኮር ጊዜ አይሰጥም' ይላል ቤዞስ በይፋ በጻፈው የመልቀቂያ ደብዳቤ።

ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ አሁን ትኩረት ሊያደርግበት የፈለጋቸው የሥራ ዘርፎች በህዋ ትራንስፖርት ላይ የሚያተኩረው ብሉ ኦሪጂን እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ህትመት እና ሌሎች የግል ፍላጎቶቹ ላይ ነው።

የአማዞን የበይነ መረብ ገበያን የጀመረው በ1994 ሲሆን ያን ጊዜ መጽሐፍ በበይነ መረብ የሚሸጥ ትንሽ ድርጅት ሆኖ ነበር አማዞን የተመሰረተው። አሁን አማዞን በመላው ዓለም 1.3 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉት።

በ2020 ዓ/ም ብቻ የአማዞን ጠቅላላ ሽያጭ 386 ቢሊዮን ዶላር አልፏል። ይህም የሆነው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የበይነ መረብ ገበያው ስለደራ ነው። ጄፍ ቤዞስ በፎርብስ የሀብት ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰለት ሀብቱ 192 ቢሊዯን ዶላር ደርሷል።

Via - BBC
@Yenetube @FikerAsssefa
15.9K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ