Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.53K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 486

2021-02-06 09:42:44
ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join

@giftsoflovee
@giftsoflovee

+251914839754
+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
4.8K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 09:42:15
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

0953707070
62.0K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 21:33:51 በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ ላይ ያለው እክል እንዳልተቃለለ፣ ነገር ግን ወደ ክልሉ የሚገባው ዕርዳታ በየጊዜው እየጨመረ እንደሄደ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። ዕርዳታ በእጅጉ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ግን ዛሬም ተደራሽ አልሆኑም- ብሏል ቢሮው። በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርቶች እንደሚቀርቡ የጠቀሰው ቢሮው፣ ሆኖም ምዕራባዊ፣ ማዕከላዊ፣ ምሥራቃዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡባዊ እና ደቡብ ምሥራቃዊ ትግራይ ተደራሽ ስላልሆኑ ሪፖርቶቹን ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አክሎ ገልጧል።

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 19:19:18 የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ አሠራር ተዘረጋ!

የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ የጋራ አሠራር መዘርጋቱን የግል ድርጅቶች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ።አብዛኞቹ የግል ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በአግባቡ እየከፈሉ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጊዜውን ጠብቀው ያለመክፈል፣ የተወሰኑት ደግሞ ከእነጭራሹ እንደማይከፍሉ ሁኔታ መኖሩን ኤጀንሲው ገልጿል።

የኤጂንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገመቹ ወዩማ፣ ከጡረታ መዋጮ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ድርጅቶች ላይ የሚስተዋለውን መዘግየት እና ለመክፈል አለመፈለግ ችግሮች ለመፍታት በአካል ጭምር በመሄድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል። በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ ድርጅቶች እንዲከፍሉ እና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ኤጀንሲው ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ቅንጅታዊ አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

በዚሁ መሠረት የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች በዓመቱ መጨረሻ የንግድ ፈቃድ እድሳት እንዳይደረግላቸው የሚያደርግ አሠራር ተዘርግቷል ነው ያሉት።ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ ክፍያ 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የገለጹት አቶ ገመቹ፣ ገቢው በስድስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 106 በመቶ መሆኑንም መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.8K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 18:40:05
ከቀበሌ እስከ ዞን ያለውን አደረጃጀት ለውጥ ማምጣት በሚችል መንገድ ማደራጀት ተጀምሯል - ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

በመተከል ዞን የግብረ ሃይሉ መሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ከቀበሌ እስከ ዞን ያለውን አደረጃጀት ለውጥ ማምጣት በሚችል መንገድ ማደራጀት ጀምረናል ብለዋል።

"ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሲመለሱ አስተማማኝ ሠላም እንዲሰፍን የአካባቢውን ህዝብ የሚመስል የሚሊሻ አደረጃጀት ተፈጥሯል፤ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ የሚሊሻ አባላትም ከዛሬ ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ይወስዳሉ" ብለዋል፡፡

ሽፍታው የሚንቀሳቀስባቸውና የጸጥታ ስጋት ያለባቸው 32 ቀበሌዎች በሚቀጥሉት 15 ቀናት ሙሉ በሙሉ ከሽፍታው እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆኑ አመራሩ ታች ድረስ ወርዶ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከመመለሳቸው በፊት የአካባቢው ሠላም አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ተፈናቃዮች በሚቋቋሙበት ጊዜ የሚፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት አስቀድሞ ትክክለኛ ቁጥራቸውን መለየት እንደሚገባ ገልጸው፣ ለዚህ ደግሞ የሠላም ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል ብለዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌም ተፈናቃዮችን ለመመለስ ማወያየት፣ የዕርቀ ሠላም ስራና ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እንደሚሟሉና ያ ሳይሆን የመመለሱ ስራ እንደማይሰራ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
16.8K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 17:21:26 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች ሁኔታ ላይ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች እና ሌሎች እስረኞችንም ሁኔታ ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ በመገኘት እስረኞቹን የጎበኘ ሲሆን፣ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ በተጨማሪም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ አያያዝ ላይ ክትትል አድርጓል። በክትትሉም ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና ከቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ ቤት አስተዳደሮች እንዲሁም ከእስረኞቹ ጋር ተነጋግሯል።

ኢሰመኮ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተገኘበት ወቅት፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ከጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ ነበሩ። የረሃብ አድማው ዓላማ “መንግስት በሕዝብ እና በፓርቲያቸው ላይ እያደረሰ ያለውን አፈና እና የመብት ጥሰት ለመቃወም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያናን አላግባብ የሆነ አያያዝ እና እንግልት እንዲቆም ለመጠየቅ እና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ እና እነሱን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ” መሆኑን እስረኞቹ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ ለረሃብ አድማው በምክንያትነት የተጠቀሱ አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ማረሚያ ቤቱን የማይመለከቱ መሆኑንና እስረኞችን ለመጠየቅ የሚመጡ ሰዎች ላይ ወከባ እንደማይፈጽም ገልጿል። አስተዳደሩ አክሎም የረሃብ አድማው በእስረኞቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል፣ በተለይም ከመካከላቸው ሁለቱ የጤና ችግር ስላለባቸው በቋሚነት መድኃኒት የሚወስዱ በመሆኑ ቅርብ የህክምና ክትትል እንደሚደረግላቸው አስረድቷል። ኢሰመኮ በቦታው በነበረበት ወቅት የተባለው ህክምና ክትትል እንደሚደረግ በምልከታ ለማረጋገጥ ችሏል።

በሌላ በኩል፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ ተቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ ቪዲዮ ፊልም ጋር በተያያዘ ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል የተባሉትን ኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ ደኅንነትና አያያዝ ሁኔታ ኮሚሽኑ አጣርቷል። ሁለቱም ታሳሪዎች በደኅንነት ላይ እንደሚገኙና አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው አረጋግጧል። ሆኖም ግን ኮሎኔል ገመቹ አያና ከዚህ በፊት ከነበረበት የእስር ክፍል (ዞን) እንዲወጣ ተደርጎ ‹‹ለደህንነቱ ምቹ ወዳልሆነ የእስር ክፍል (ዞን) እንዲዛወር መደረጉን›› እና ከዚህም በፊት በተደጋጋሚ ከቦታ ቦታ በመዘዋወሩ የደረሰበትን እንግልት በሚመለከት ቅሬታውን ለኮሚሽኑ አስረድቷል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በበኩሉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የእስረኞች ክፍል (ዞን) ዝውውር ሊደረግ የሚችል መሆኑን ገልጾ፤ ኮሎኔል ገመቹ የተዛወሩበት የእስር ክፍል (ዞን) ሌሎች እስረኞችም የሚገኙበት መሆኑን ይገልጻል። ኮሚሽኑም በጉብኝቱ ወቅት የማረሚያ ቤቱን ደንብ በመተላለፍ ምክንያት ወደዚህ የእስር ክፍል (ዞን) መምጣቱን የገለጸ አንድ ታሳሪ መኖሩን ኢሰመኮ ተመልክቷል፡፡

ኢሰመኮ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የሰጠውን ምክረ ሃሳብ ተከትሎ፣ አስተዳደሩ እስረኛውን ወደ ሌላ ዞን ለማዛወር በዝግጅት ላይ የነበረ ቢሆንም፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት እስረኛው ከቂሊንጦ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዛወሩ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ ወደ ቂሊንጦ እንዲመለስ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት፣ ከጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስረኛው በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት የሚገኝ መሆኑን ኢሰመኮ እስረኛውን በመጎብኘት አረጋግጧል።

በተመሳሳይ መልኩ፣ ኢሰመኮ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥሮ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘውን የአቶ ጥላሁን ያሚን ደኅንነትና አያያዝ አጣርቷል። እስረኛው በሙሉ ደኅንነት የሚገኝ ሲሆን በማሕበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ቪዲዬ ተከትሎ ከማቆያ ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይወጣ ከመደረጉ በስተቀር በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ እያለ ድብደባም ሆነ ሌላ አይነት የመብት ጥሰት ያልተፈጸመበት መሆኑን አስረድቶ፣ ነገር ግን ከዚህ ቀደም በፖሊስ ጣቢያ በምርመራ ወቅት የነበረውን ተገቢ ያልሆነ አያያዝ በተመለከተ ለኢሰመኮ ቅሬታውን አስረድቷል ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞችን አስመልክቶ፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የእስረኞቹ ጤንነትና ሕይወት የከፋ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞችን ጠያቂዎች በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል›› በማለት ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.9K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 16:09:06
ዋልያ ለችግረኛ ወገኖች የተገነቡ ባለ ሰባት ብሎክ 53 ቤቶችን ለባለቤቶቹ አስረከበ

በአዲስ አበባ ከተማ ጎልተው ከሚታዩ ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ደረጃውን የጠበቀ መኖርያ ቤት ችግር ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር በተባለው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ግድግዳው እና ጣሪያው ከቆርቆሮ በተሠራ ቤት ላለፉት 40 ዓመታት ኖረዋል፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ብቻ ሳይሆን ኩሽና እና መጸዳጃ ቤታቸውም ከቆርቆሮ ተሠርቶ ለረጅም ዘመን በማገልገሉ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር፡፡
ሃይንከን ኢትዮጵያ/ዋልያ ቢራ ይህን ችግር በመረዳት እነዚህን ባለሰባት ብሎክ 53 ቤቶች፣ ኩሽና እና መጸዳጃ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ደረጃውን በጠበቀ የብሎኬት ቤት ተክቶታል፡፡ ግንባታው በሁለት ወራት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ 8.4 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.1K viewsedited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:57:52
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ ደረሰ!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።ሚኒስቴሩ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትንና የህዳሴ ግድቡን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።ግድቡ ለተፋሰሱ አገሮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ኢንጂነር ስለሺ፤ “የግድቡ ግንባታ ሰኔ ወር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም የ4 ነጥብ 05 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
11.2K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:55:57
አምቦ ከተማ ተማሪዎች ሰልፍ ወጥተዋል!

አምቦ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ተማሪዎች፤ ፍትህ ለሀጫሉ፣ የታሰሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ፣ እና ሌሎች መፈከሮችን በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የአዲስ ዘይቤ መረጃ ያመለክታል። ሆኖም ሰልፉ ብዙም ሳይቆይ ተማሪዎቹ በፖሊስ ሀይሎች እንደተበተኑ እና አንዳዶችም እንደታፈሱ ከአይን እማኛችን ለማረጋገጥ ተችሏል።አዲስ ዘይቤ አምቦ ያለውን የፖሊስ ቢሮ ለማነጋገር ሙከራ ያደረገ ቢሆንም "ስብሰባ ላይ ነን አሁን ማናገር አንችልም" የሚል ምላሽ አግኝቻለው ብላለች።

@YeneTube @FikerAssefa
10.4K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 15:49:04
ስልሳ ስምንት ዜጎች ከሊባኖስ ቤይሩት ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ስልሳ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ ቤይሩት በፍሪደም ፈንድ እና አጋር ኢትዮጵያ በተባሉ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች አማካኝነት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ