Get Mystery Box with random crypto!

ዋልያ ለችግረኛ ወገኖች የተገነቡ ባለ ሰባት ብሎክ 53 ቤቶችን ለባለቤቶቹ አስረከበ በአዲስ አበ | YeneTube

ዋልያ ለችግረኛ ወገኖች የተገነቡ ባለ ሰባት ብሎክ 53 ቤቶችን ለባለቤቶቹ አስረከበ

በአዲስ አበባ ከተማ ጎልተው ከሚታዩ ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ደረጃውን የጠበቀ መኖርያ ቤት ችግር ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር በተባለው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ግድግዳው እና ጣሪያው ከቆርቆሮ በተሠራ ቤት ላለፉት 40 ዓመታት ኖረዋል፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ብቻ ሳይሆን ኩሽና እና መጸዳጃ ቤታቸውም ከቆርቆሮ ተሠርቶ ለረጅም ዘመን በማገልገሉ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር፡፡
ሃይንከን ኢትዮጵያ/ዋልያ ቢራ ይህን ችግር በመረዳት እነዚህን ባለሰባት ብሎክ 53 ቤቶች፣ ኩሽና እና መጸዳጃ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ደረጃውን በጠበቀ የብሎኬት ቤት ተክቶታል፡፡ ግንባታው በሁለት ወራት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ 8.4 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል።

@YeneTube @FikerAssefa