Get Mystery Box with random crypto!

የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ አሠራር ተዘረጋ! | YeneTube

የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ አሠራር ተዘረጋ!

የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ የጋራ አሠራር መዘርጋቱን የግል ድርጅቶች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ።አብዛኞቹ የግል ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በአግባቡ እየከፈሉ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጊዜውን ጠብቀው ያለመክፈል፣ የተወሰኑት ደግሞ ከእነጭራሹ እንደማይከፍሉ ሁኔታ መኖሩን ኤጀንሲው ገልጿል።

የኤጂንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገመቹ ወዩማ፣ ከጡረታ መዋጮ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ድርጅቶች ላይ የሚስተዋለውን መዘግየት እና ለመክፈል አለመፈለግ ችግሮች ለመፍታት በአካል ጭምር በመሄድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል። በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ ድርጅቶች እንዲከፍሉ እና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ኤጀንሲው ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ቅንጅታዊ አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

በዚሁ መሠረት የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች በዓመቱ መጨረሻ የንግድ ፈቃድ እድሳት እንዳይደረግላቸው የሚያደርግ አሠራር ተዘርግቷል ነው ያሉት።ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ ክፍያ 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የገለጹት አቶ ገመቹ፣ ገቢው በስድስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 106 በመቶ መሆኑንም መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa