Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ለዘንድሮው ምርጫ 435 የምርጫ ወረዳዎች ማቋቋሙ | YeneTube

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ለዘንድሮው ምርጫ 435 የምርጫ ወረዳዎች ማቋቋሙን ይፋ አደረገ፡፡

ፓርቲው በዘንድሮ አመት ለሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ እያከናወነ ያለውን ተግባር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፓርቲው በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች መዋቅሩን የመዘርጋት ስራ እያከናወነ መሆኑን የተናገሩት የኢዜማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ ፓርቲው በዘንድሮ አመት የሚካሄደው ምርጫም ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲዊ ምዕራፍ ያሸጋግራታል ብሎ እንደሚያምን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ አስፈላጊውን ሁሉ የምርጫ ፓርቲው እያከናወነ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ከ435ቱ የምርጫ ወረዳዎች በ406ቱ የምርጫ ወረዳዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለክልል ምክር ቤት እና ለወረዳ የሚሳተፉ እጩዎች አስመርጦ ማጠናቀቁንም አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡

ለሚካሄደው ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን የገንዝብ ድጋፍ ፓርቲው እያሰባሰበ መሆኑን የሚናገሩት የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዱአለም አራጌ በማዕከል ደረጃ ብቻ 140 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኪራይ ያገኘውንና በ5 ሚሊየን ብር እድሳት የተደረገለትን የፓርቲውን ዋና ጽህፈት ቤት ፓርቲው ይፋ አድርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa