Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.53K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-13 10:17:38
ኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የአገልግሎት የግንባታ ማሽኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን አስታወቀ!

ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከጅቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ተጭነው እንዶዴ የባቡር ጣቢያ የደረሱ አምስት ኤክስካቫተሮችን በትላንትናው እለት ለደንበኞች አስረክቧል፡፡

መሰል ጭነት በኢትዮ ጅቡቲ የባቡር አገልግሎት ሲጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ያስታወቀው ድርጅቱ በቅርቡ ተጨማሪ የኮንስትራክሽን ግዙፍ ተሽከርካሪዎች ከጂቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎት እንደሚያስጀምርም ድርጅቱ ቀደም ሲል ለካፒታል ተናግሯል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
13.1K viewsedited  07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 09:04:39
Yango የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ ሲሆን ከ72 ብር ብቻ የሚጀምሩ እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ጉዞዎችን ይዞሎት መጥቷል! ከመጀመሪያዎ 3 ጉዞዎች ላይ የ30% ቅናሽ ለማግኘት ከGoogle play አሊያም ከApp Store Yangoን ያውርዱ ወይም ወደ 8610 ይደውሉ።
13.6K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 14:05:11
ቦሌ የነበረው ተኩስ

ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር

የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።

ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ከቦሌ SNAP PLAZA እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.1K viewsedited  11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 23:09:49
ኦ ጄ ሲምፕሰን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

ታዋቂው የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋች፣ እንዲሁም የቀድሞ የትዳር አጋሩን ገድሏል በሚል ከ30 ዓመታት በፊት ከቀረበበትና “የክፍለ ዘመኑ የፍርድ ሂደት” በመባል ከሚታወቀው ክስ ነፃ የወጣው ኦ ጄ ሲምፕሰን፣ በ76 ዓመቱ ትላንት ረቡዕ ላስ ቬጋስ ውስጥ ከዚሕ ዓለም በሞት መለየቱን ጠበቃው አስታውቀዋል።ሲምፕሰን የካንሰር ሕመምተኛ እንደነበርም ጠበቃው ቲ ኤም ዚ ለተባለው ቴሌቪዥን አስታውቀዋል።

በአሜሪካ የእግር ኳስ ጨዋታ ከፍተኛ ዝናን አትርፎ የነበረው ሲምፕሰን፣ በእ.አ.አ 1994 የቀድሞ የትዳር አጋሩን፣ ኒኮል ብራውን ሲምፕሰንን እና ጓደኛዋ የነበረን አንድ ሌላ ግለሰብ ገድሏል በሚል የቀረበበት ክስና የፍርድ ቤት ሂደት፣ የአሜሪካውያንንም ሆነ የተቀረውን ዓለም ትኩረት ሰቅዞ የያዘ ነበር።

ሲምፕሰን፣ ጥቁር፤ የቀድሞ ባለቤቱ ደግሞ ነጭ መሆኗ፣ አሜሪካዉያን የፍርድ ሂደቱን በውጥረት ውስጥ ሆነው እንዲከታተሉት አድርጓል።ሲምፕሰን ከመጀመሪያው ክስ ቢያመልጥም፣ ውድ የስፖርት ማስታወሻዎችን የሚሸጡ ደላላዎችን በመሣሪያ አስፍራርቶ ዘርፏል በሚል ከአሥር ዓመታት በኋላ በቀረበበት ክስ፣ የዘጠኝ ዓመታት እሥር ተፈርዶበታል። በእ.አ.አ 2017 ከእሥር የወጣው ሲምፕሰን፣ የስፖርት ማስታወሻዎቹ የራሱ እንደሆኑ ተናግሯል።

በቀድሞ ባለቤቱ ክስ ወቅት ጠበቃው የነበሩት ታዋቂው ጃኒ ካክረን፣ በሲምፕሰን ላይ በማስረጃነት የቀረበውን የእጅ ጓንት ፍ/ቤቱ ሲለካው መጥለቅ ባለመቻሉ፣ “ጓንቱ ልኩ ካልሆነ፣ ደንበኛዬን ልቀቁ” ማለታቸው፣ የፍርድ ሂደቱን የተከታተሉ ሁሉ የሚያስታውሱት ነው።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
12.9K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 15:17:47 ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደሌለና ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት መሆኗን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ተናገሩ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” መሆኗን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር እና ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብም ተናግረዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ሞሐመድ ይህንን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ነው።

“የኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ቀልባቸው መመለስ አለባቸው” ያሉትን ሐሴን ሼህ፤ ግጭት እየፈጠረች ያለችው ኢትዮጵያ እንጂ ሶማሊያ እንዳልሆነች ለዓለም እየተናገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“እኛ የኢትዮጵያን አካል እንፈልጋለን አላልንም። ለኢትዮጵያን መንግሥት እውቅና አንሰጥም [አላልንም]፤ ከክልል መንግሥት ጋር ስምምነት እንፈጽማለንም አላልንም” ሲሉ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት እየፈጠረች አይደለም የሚለውን ሀሳባቸውን አስረድተዋል።

ሁለቱ ጎረቤት አገራት በጋራ ፍላጎቶቻቸው ላይ መሥራት ያላቸው “ብቸኛ አማራጭ” መሆኑን በንግግራቸው ላይ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሉዓላዊነታችንን፣ አንድነት እና ሙሉዕነታችንን ለድርድር የሚያቀርብ የጋራ ፍላጎት ሊኖረን አይችልም” ብለዋል።

ሐሰን ሼክ፤ “ለዓለም እየተናገርን ያለነው፤ እኛ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት እንዳልሆንን ነው። እነሱ ግን ናቸው። እናም ይህ እንዲፈጠር በፍፁም አንፈቅድም” ሲሉ ከኢትዮጵያ ተጋርጦብናል ያሉትን ስጋት ገልጸዋል።

ሶማሊያ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር ልታደርግ እንደማትችል እና ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብ የተናገሩት ሐሴን ሼክ፤ “ንግግርን ወይም ድርድርን እየተቃወምን አይደለም። ነገር ግን መሬታችን እንዲወሰድ ወይም ሉዐላዊነታችን ለድርድር እንዲቀርብ አንፈቅድም” ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ የኢትዮጵያ መሪዎች እየተከተሉት ያለው አካሄድ “እንደማይሠራላቸው” እና “ከዚህ መንገድ እንዲመለሱ እየመከሯቸው” መሆኑንም አንስተዋል።

ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ይህንን ንግግር ያደረጉት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማቋረጥ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ካስተላለፈች ከቀናት በኋላ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኙት የሶማሊያ አምባሳደርም ወደ ሞቃዲሾ እንዲመለሱ መታዘዛቸው ይታወሳል።

ሁለቱ አካላት ጥር ላይ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚነት ወደሚኖረው ስምምነት ተቀይሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ሁለቱ አካላት በተፈራረሙበት ዕለት ተገልጾ ነበር። ይሁንና የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ አራት ወራት ቢያልፍም እስካሁን ድረስ ተፈፃሚነቱ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ በይፋ የተነገረ ነገር የለም።

Via::- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
14.8K viewsedited  12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 15:17:16
ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ቤት ለቤት ይላኩ ይቀበሉ።

በአዲስ ኤክስፕረስ ይላኩ ይቀበሉ።
ዛሬ ከአዲስ አበባ ይላኩ ነገ አርባምንጭ ይቀበሉ።

ፓስታዎች
የመኪና ስፔር ፓርቶች
የጨረታ ሰነዶች

አዲስ ኤክስፕረስ የችግሮ መላ
0980526262 አዲስ አበባ
0988627762 አርባምንጭ
13.7K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 15:16:40
አስደሳች ዜና ለወላጆች

         Ace Tutors
 
  በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል


- ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን
- ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች
- ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል


ለበለጠ መረጃ
በ0943909174 ይደውሉ

@acetutorshr
@acetutorshr
13.7K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:16:03
Did you miss our February edition EdTech Mondays radio show? No worries, all you have to do is click on the below link and access the full show where we highlight Ethiopia's Digital Education Strategy and Implementation Plan. Join our community and explore the innovative pathways transforming education in Ethiopia. Be part of the conversation!

#EdTechMondays #EdTechMondaysEthiopia #Ethiopia #Africa #Education #EdTech #Tech #AddisAbaba #ICT #Infrastructure #Digital #DigitalLiteracy #Shega #mastercardfoundation

Check out the full video at

13.8K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 16:28:38
የኤርትራ ሰራዊት በኢሮብ

ከአድዋ 23 ኪሎሜትር እንዲሁም ከኤርትራ ድንበር በ 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው #ኢሮብ ሰሞኑን በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መሆኗን ምንጮች ገልጸዋል።

የኤርትራ ሃይሎች የኢሮብ ተወላጆችን ማንነታቸውን ኤርትራዊ ብለው እንዲቀይሩ እና በኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሳተፉ እያስገደዱ መሆኑን የአይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል። .

ወደ ብሄራዊ ግዳጅ አንሄድም ያሉ ሰዎችም እንደሚታሰሩ ገልፀዋል።
በስፍራው የስልክ አገልግሎም ተቋርጧል ተብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
16.3K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 16:00:17
Yango የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ ሲሆን ከ72 ብር ብቻ የሚጀምሩ እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ጉዞዎችን ይዞሎት መጥቷል! ከመጀመሪያዎ 3 ጉዞዎች ላይ የ30% ቅናሽ ለማግኘት ከGoogle play አሊያም ከApp Store Yangoን ያውርዱ ወይም ወደ 8610 ይደውሉ።
15.4K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ