Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የአገልግሎት የግንባታ ማሽኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን አስታወቀ! ድርጅቱ እ | YeneTube

ኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የአገልግሎት የግንባታ ማሽኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዙን አስታወቀ!

ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከጅቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ተጭነው እንዶዴ የባቡር ጣቢያ የደረሱ አምስት ኤክስካቫተሮችን በትላንትናው እለት ለደንበኞች አስረክቧል፡፡

መሰል ጭነት በኢትዮ ጅቡቲ የባቡር አገልግሎት ሲጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ያስታወቀው ድርጅቱ በቅርቡ ተጨማሪ የኮንስትራክሽን ግዙፍ ተሽከርካሪዎች ከጂቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎት እንደሚያስጀምርም ድርጅቱ ቀደም ሲል ለካፒታል ተናግሯል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa