Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Africa
Share
Ethiopia
Scholarship
Austria
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 129.72K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-06-22 12:00:37 በፓኪስታን ‘ቅዱስ ቁርዓንን አራክሷል’ የተባለ ቱሪስት በደቦ ጥቃት ተገደለ!

በፓኪስታን ቅዱስ ቁርዓንን አራክሷል በሚል የተወነጀለ ጎብኝ ከፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ በደቦ ፍርድ ተገደለ።ድርጊቱ የተፈፀመው በስዋት ወረዳ በምትገኘው ማድያን ከተማ ሲሆን ፖሊስ ጎብኝውን ከተሰባሰበው ቡድን ለመከላከል ሞክሮ ነበር።ሐሙስ ዕለት ነዋሪዎች የተሰባሰቡት ግለሰቡ ቅዱስ ቁርአንን አራክሷል በሚል ከተከሰሰ በኋላ ነበር።ሃይማኖትን ማራከስ በፓኪስታን በሞት የሚያስቀጣ ሲሆን በዚህ ድርጊት የተወነጀሉ ሰዎችን ያለፍርድ በደቦ ጥቃት መግደል የተለመደ ነው።

ባለፈው ወር አንድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቁርዓንን ገጾች አቃጥሏል በሚል ተወንጅሎ ጥቃት ከተፈፀመበት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።ሐሙስ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት የሚያሳይ ቪዲዮ ከወጣ በኋላ በፓኪስታን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።ቪዲዮው የግለሰቡ አስክሬን በመንገድ ላይ ሲጎተት እና በኋላም ላይ ሲቃጠል አሳይቷል።

ፖሊስም የግለሰቡ አስክሬን መቃጠሉን ያረጋገጠ ሲሆን ከክስተቱ ጋር ተያይዞ 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።የማላንካንድ ፖሊስ አዛዥ መሐመድ አሊ ፣ በበጋ ወቅት የሚጎበኘውን የስዋት ሸለቆ ለመጎብኘት ወደ አካባቢው ያመራውን ግለሰብ ፖሊስ ከታደገው በኋላ በአካባቢው የሚገኝ መስጊድ ሰዎች እንዲሰባሰቡ በመቀስቀስ ጥቃቱን አቀጣጥሏል ሲሉ ወንጅለዋል።የፖሊስ አዛዡ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ከተጎዱት መካከል ስምንቱ የፖሊስ መኮንኖች ናቸው።

በስዋት ክልል የፖሊስ መኮንን የሆኑት ዛሂዱላህ በበኩላቸው የኡርዱ ፖሊስ በቁጣ የተሰባሰቡ ሰዎችን ለመበተንና የተዘጉ መንገዶችን ለመክፈት ጥረት ማድረጉን ለቢቢሲ ተናግረዋል።በድርጊቱ ላይ በተሳተፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ክስ መክፈቱንም ፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ እንዳለው በድርጊቱ ከተሳተፉት መካከል እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችም ይገኙበታል።ከክስተቱ በኋላ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል አሰማርተዋል።ቢቢሲ ኡርዱ እንደዘገበው ከሆነ በከተማዋ ያሉ ሆቴሎች በቱሪስቶች ሙሉ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ከተማዋን ለቀው ለመውጣት እየተጣደፉ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
9.0K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 11:15:19
ሁሉም አከራይ በ15 ቀናት ተከራያቸውን ይዘው በመምጣት የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት መፈጸም ይጠበቅባቸዋል!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወ/ ጊዮርጊስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ በከተማው ግልፅና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ አከራይና ተከራይን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህም ቢሮው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እና መመሪያ ቁጥር 7/2016 ከመጋቢት 24 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

እንዲሁም በከተማው በ11 ክፍለከተሞችና በ120 ወረዳዎች ላይ የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ከሰኔ 1 ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ ሰኔ 30 2016 የሚቆይ ይሆናል።

ውሉ ለሁለት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በነዚህ ጊዜያትም ተከራይ ማስወጣት ሆነ የቤት ኪራይ መጨመር የማይቻል መሆኑንም አስታውቀዋል።

ምዝገባውን በተሰጠው ጊዜ ሳይመዘገብ እስከ ሶስት ወራት የቆየ አከራይ የሁለት ወር ኪራይ እንዲሁም ከሶስት ወራት በላይ ካለፈ የሶስት ወር የቤት ኪራይ ቅጣት የሚቀጣ መሆኑም ተገልጿል።

እንዲሁም አዋጁ ከፀደቀበት መጋቢት 24 2016 ጀምሮ የሚደረግ ማንኛውም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ የማይፈቀድ መሆኑን ገልፀዋል።በመሆኑም በተቀመጠው ጊዜና መመሪያ መሰረት ሁሉም አከራይ ተከራይን ይዘው በመምጣት የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት መፈጸም እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
8.5K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 11:08:10
ሮማኒያ የሥራ ቪዛ

           መሥፈርቶች
የ ፋብሪካ ሥራዎች
በ ሹፍርና
በ ሆቴሎች ሥራዎች
ብ ግብርና ሥራዎች
ሌሎችም
    የታደሰ ፖስፖርት
   እድሜ ከ 19_49 በላይ

  የ ፕሮሰስ ግዜ በ 45 የስራ ቀን ዉል ይመጣል
  ፆታ ሁለቱም
ብዛት ከ 40 በላይ
ደሞዝ 800-1200 euro


Contact Us:

@Sabinavisa2ስልክ  ቁጥራችን 9445Website

https://sabina.et/

      ለበለጠ መረጃ

ወደ ቢሮአችን ይምጡ !

አዲስ አበባ

ሃያ ሁለት ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

እንዲሁም

         በ ሀዋሳ

ቱሩፋት ወርቁ ቡቼ ታወር ፊት ለፊት አዲስ የ ገበያ ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://t.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
7.7K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 11:08:10
ከ 0 አመት ጀምሮ
በ የ ቀኑ የሚወጡ አዳዲስ  የ ሰራ ማስታወቂያዎች ይለቀቃሉ
ከጋዜጦች
ከኤጀንሲዎች
ከድርጅቶች በተጨማሪም
በስልክ እና በኮምፒውተር የሚሰሩ ፓርት ታይም
ስራዎች ስንለቅ  በፍጥነት እንዲደርሶ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ


https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
8.1K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 12:59:24 የመንግሥት ሰራተኞች የደረጃ እድገት እና የእርከን ጭማሪ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተፈቅዷል፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

አዲሱ የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የሰራተኞች አዋጅ ሰራተኞች ተመዝነው በአፈጻጸማቸው የሚለዩበት እንደሆነ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።

አዋጁን በተዛባ መንገድ መረዳት አይገባም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አንድ ሰራተኛ ሁለት ጊዜ ተመዝኖ ውጤቱ ከመካከለኛ በታች ከሆነ ከስራው እንደሚሰናበትም ጠቁመዋል።

በዚህ ምዘና በቂ ውጤት ያመጡ ሰራተኞች ደግሞ የደረጃ እድገት እንዲሁም በየሁለት ዓመቱ የሚኖር የእርከን ጭማሪ እንዲያገኙ በአዋጁ ተደንግጓል ብለዋል።

የአዋጁ ዋና ዓላማ ሰራተኛን መቀነስ ሳይሆን ማብቃት ነው ያሉት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)፤ በምዘናው ደረጃ አሟልተው ብቁ የሆኑ፣ የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው እና ሰፋ ያለ ክፍተት የታየባቸው ተለይተው ክፍተቶቹ በስልጠና እየተሟሉ ሶስቱም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
12.0K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 11:30:32 ለአመታት ሳይወገድ ተከማችቶ የነበረ አደገኛ ኬሚካል መወገዱ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢኒስቲትዩት እንዳስታወቀው ተከማችቶ የነበረ 95 በመቶ አደገኛ ኬሚካል ማስወገዱን አመላክቷል::ተቋሙ ያስወገደው አደገኛ ኬሚካል በእንስሳትና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ እንደነበረ ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ጂዮሎጂካል ኢንስታትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጀራ ተስፋዬ እንደተናገሩት ለአመታት ኬሚካሎች ሳይወገዱ ተከማችተው በመቆየታቸው ምክንያት ስጋት ፈጥሮ መቆየቱን ተናግረዋል።ተወገዱ ያሏቸውን የኬሚካል አይነቶች ግን በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

በሌላ በኩል ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አደገኛ ኬሚካሎቹ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እና ለማስወገድ በባለሙያዎች የተዘረጋው የአሰራር ስርዓት እየተተገበረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
11.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 10:57:46 የአል-ሸባብ መልሶ የመደራጀት ስጋትን ተከትሎ ሶማሊያ የሰላም አስከባሪዎች ቆይታ እንዲራዘመ ጠየቀች!

የአል-ሸባብ ዳግም መልሶ የመደራጀት ስጋትን ተከትሎ የሶማሊያ መንግሥት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከአገሪቱ የሚወጡበትን ጊዜ እንዲያራዝሙ ጠየቀች።ሮይተርስ የዜና ወኪል የመንግሥት ሰነዶችን ተመልክቶ እንደዘገበው በቀጠናው ያሉ ጎረቤት አገራት አል-ሸባብ ስልጣን ሊይዝ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትም ሰላም አስከባሪዎችን ያለ በቂ ቅድመ ዝግጅት ከሶማሊያ ማስወጣት “በአገሪቱ የደኅንነት ክፍተት ይፈጥራል” ሲል አስጠንቅቆ ነበር።

በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ተሰማርቶ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ትራንዚሽን ሚሽን ኢን ሶማሊያ (የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ) - አትሚስ እአአ በ2024 መጨረሻ ቆይታው ይጠናቀቃል።በዕቅዱ መሠረት የሰላም አስከባሪ ኃይሎቹ ቀስ በቀስ እየወጡ 2024 ማብቂያ ላይ ሙሉ በሙሉ ጠቅልለው ከሶማሊያ ከወጡ በኋላ የሶማሊያ ጦር ኃላፊነቱን ይረከባል።

ይሁን እንጂ የሶማሊያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ደኅንነት ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ሰኔ 2016 ዓ.ም. መውጣት ያለባቸው የ2000 ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ቆይታ እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም. ድረስ እንዲራዘም ጠይቋል።የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን ከአገሪቱ በማስወጣት ረገድ በተለይ ደግሞ በሶማሊያ ተሰማርቶ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠራዊትን በተመለከተ በባለስልጣናት መካከል የተለያዩ ሃሳቦች ሲንጸባረቁ ቆይተዋል።

የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት የኢትዮጵያን ሠራዊት ከሶማሊያ ለማስወጣት ቢወስንም አንዳንድ የሶማሊያ ግዛት መሪዎች እና የምክር ቤት አባላት ውሳኔውን ሲቃወሙ ቆይተዋል።ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት መፈረሟ በሁለቱ አገራት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን ፈጥሯል።

ይህን ተከትሎ ለሶማሊያ መረጋጋት ትልቅ ኃላፊነት ሲወጣ የቆየው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከሶማሊያ እንዲወጣ ፍላጎታቸው መሆኑን የአገሪቱ ባለስልጣናት በይፋ ሲናገሩ ቆይተዋል።የኢትዮጵያ ሠራዊት ለአካባቢው አደገኛ ነው ተብሎ የነበረውን የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ቡድንን ዛቻ ተከትሎ ወደ ሶማሊያ ዘልቆ በመግባት የቡድኑን መዋቅር በማፈራረስ ለሶማሊያ መንግሥት መጠናከር ድጋፍ አድርጓል።ከዚያም በኋላ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተልዕኮዎች ስር በመሆን አል ሻባብ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ላይ የደቀነውን አደጋ ለመግታት ከፍተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱ ይነገርለታል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
10.8K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 10:37:17
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት አመቱ አስር ወራት 1066 የሰንበት ገበያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ አድርጊያለሁ አለ!

በበጀት ዓመቱ አስር ወራት የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃላል ካከናወንኳቸው ተግባራት መካከል አንዱ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የሰንበት ገብያ ማዕከላት ናቸው ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

በተያዘው በጀት አመት አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ የሚገበያዩበት የግብይት ማዕከላትን ማሳደግ በትኩረት የሰራሁበት ነው ያለው ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት የሰንበት ገበያ ማዕከላትን 818 ለማድረስ አቅጄ ብነሳም ከዕቅዴ በላይ 1066 የሰንበት ገበያ አቋቁሚያለሁ ብሏል።

በሰንበት ገበያው የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ከመደበኛው ገበያ በተሻለና በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረብ መቻላቸውንም ጠቁሟል።በቀጣይ በሰንበት ገበያ ለሚቀርቡ ምርቶች፣ ዓይነት፣ ጥራትና ከቦታ መረጣ አኳያ ደረጃ እየተዘጋጀላቸውም እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
9.2K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 10:34:53
ሮማኒያ የሥራ ቪዛ

           መሥፈርቶች
የ ፋብሪካ ሥራዎች
በ ሹፍርና
በ ሆቴሎች ሥራዎች
ብ ግብርና ሥራዎች
ሌሎችም
    የታደሰ ፖስፖርት
   እድሜ ከ 19_49 በላይ

  የ ፕሮሰስ ግዜ በ 45 የስራ ቀን ዉል ይመጣል
  ፆታ ሁለቱም
ብዛት ከ 40 በላይ
ደሞዝ 800-1200 euro


Contact Us:

@Sabinavisa2ስልክ  ቁጥራችን 9445Website

https://sabina.et/

      ለበለጠ መረጃ

ወደ ቢሮአችን ይምጡ !

አዲስ አበባ

ሃያ ሁለት ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

እንዲሁም

         በ ሀዋሳ

ቱሩፋት ወርቁ ቡቼ ታወር ፊት ለፊት አዲስ የ ገበያ ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://t.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
8.3K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 10:34:53
ከ 0 አመት ጀምሮ
በ የ ቀኑ የሚወጡ አዳዲስ  የ ሰራ ማስታወቂያዎች ይለቀቃሉ
ከጋዜጦች
ከኤጀንሲዎች
ከድርጅቶች በተጨማሪም
በስልክ እና በኮምፒውተር የሚሰሩ ፓርት ታይም
ስራዎች ስንለቅ  በፍጥነት እንዲደርሶ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ


https://t.me/plusjobs
https://t.me/plusjobs
9.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ