Get Mystery Box with random crypto!

የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ዜጎችን ማጥቃቱን የዓለም ጤና ድ | YeneTube

የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ዜጎችን ማጥቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡

ከፍተኛ ረሃብ እና በሽታ የብዙ ኢትጵያዊያንን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡የትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ በተከሰተዉ ጦርነት ምክንያት ከባድ ቀዉስን ያስተናገዱ ናቸዉ፡፡

በእነዚህ ክልሎችም የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል መዉደማቸዉንም ነዉ ድርጅቱ የገለጸዉ፡፡በኢትዮጵያ 20ኛወሩን ያስቆጠረዉ የኮሌራ ወረርሺኝ 41ሺህ ዜጎችን ያጠቃ እና በ8ወረዳዎች የተከሰተ መሆኑንም ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡

የአሁኑ የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛዉ መሆኑን ነዉ ዶ/ር ቴዎድሮስ የተናገሩት፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በወባ ወረርሺኝ 1.1 ሚሊየን ዜጎች መያዛቸዉን አንስተዉ ፤ ባለፈዉ ዓመት ከተመዘገበዉ 4 ሚሊየን ቁጥር አሁን ላይ መቀነሱን ነዉ ያስታወቁት፡፡

በዚህኛዉ ዓመት ብቻ ከ1መቶ በላይ በሚሆኑ አከባቢዎች ከ15ሺህ በላይ ሰዎች በኩፍኝ ወረርሺኝ መያዛቸዉንም አንስተዋል፡፡እነዚህ ችግሮች እየተከሰቱ ያሉት ሚሊየኖች መሰረታዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት በሚፈልጉባቸዉ ቦታዎች መሆኑንም ነዉ የገለጹት፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa