Get Mystery Box with random crypto!

ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ! የስዊ | YeneTube

ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ!

የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል።

ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል።

ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa