Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል! | YeneTube

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል!

የፀጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ላይ ድምጽ ለመስጠት ለመጭው አርብ ቀጠሮ ይዟል።በአሁኑ ጊዜ ከ10 ተዘዋዋሪ አባላት አንዷ የሆነችው አልጄሪያ «የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል እንድትሆን» የሚል ጥያቄ አቅርባለች።የአልጄሪያን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ በነገው ዕለት ድምፅ እንደሚሰጥ ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዓርብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ፤«የፍልስጤም ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሆና እንድትገባ”በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣል ሲል ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ የምክር ቤቱ ውሳኔ ቢያንስ ዘጠኝ የድጋፍ ድምጽ የሚያስፈልገው ሲሆን ፤እርምጃው እስከ 13 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።ይህም ሀሳቡን በመቃወም ዩኤስ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንድትጠቀም ያስገድዳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa