Get Mystery Box with random crypto!

ማስጠንቀቂያ! ቪዲዮውን ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች እንዲያዩት አንመክርም። በሲድኒ፣ አ | YeneTube

ማስጠንቀቂያ! ቪዲዮውን ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች እንዲያዩት አንመክርም።

በሲድኒ፣ አውስትራሊያ የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያለ አንድ ቢላዋ የያዘ ሰው በአንድ ቄስ ላይ በትናንትናው ዕለት ጥቃት ሰነዘረ።

ይሄ ሰው በዋኪሊ በሚገኘው የደጉ እረኛ ቤተክርስቲያን ቀርቦ ጳጳስ ማሪ ኢማኑኤልን ደጋግሞ በስለት ወግቷቸዋል።

ጥቃት አድራሹ ቄሱን ለመዳን የሞከሩ አራት ምእመናን ላይም ጥቃት ፈፅሟል። ቄስ ማሪ ኢማኑኤል ጉዳት ቢያጋጥማቸውም ከመሞት ተርፈዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይሄ ሰው ከአንድ ቀን አስቀድሞ አንድ ሰው በሲድኒ የገበያ ማእከል ውስጥ ገሎ መሰወሩም ተነግሯል።