Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ የነበረው ተኩስ ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋ | YeneTube

ቦሌ የነበረው ተኩስ

ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር

የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።

ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ከቦሌ SNAP PLAZA እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa