Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.53K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-03-16 22:00:37
ጥንቃቄ…

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ራሳችሁን ከችግር ታደጉ ስም ዝርዝር መለቀቅ ተጀምሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
17.1K viewsedited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 20:21:53
የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ንግድ ባንክ አስታወቀ

በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር መግለፃችን ይታወቃል።
በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ያሳወቅን ሲሆን አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን እናሳውቃለን።

ውድ ደንበኞቻችን በትእግስት ስለጠበቃችሁን እያመሰገንን ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።

@Yenetube @Fikerassefa
16.1K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 20:16:19
ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር እንደገጠመው እንዲሁም እንደተስተካከል ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያው አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች የራሳችሁ ያልሆነ ገንዘብ አስተላልፋችኃል ብሩን ለንግድ ባንክ አስተላልፍ የሚሉ ማስታወቂያዎች በመለጠፍ ላይ ናቸው።

" ዩንቨርስቲዎች ጣልቃ ለምን ገብ የሚለው እንለፍው "

እስካሁን ንግድ ባንክ ብር ሳይቆርጥት ወደ አካውንት ያስተላለፉት ሰዎች ያለው ነገር የለም
የሲስተም ችግር እንደገጠምው ከመግለፅ በስተቀር።

@Yenetube @Fikerassefa
13.9K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 19:56:00
ተመድ በአፍሪካ ቀንድ ወደ 64 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አስጠንቅቋል!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (UNOCHA) እንዳስታወቀው  በአፍሪካ ቀንድ በተያዘው ዓመት ወደ 64 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አስጠንቅቋል ።

ተመድ በሰጠው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ በሱዳን 25 ሚሊዮን፣ በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን፣ በደቡብ ሱዳን 9 ሚሊዮን እና በሶማሊያ 8.3 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 14:07:34
ኬና ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል(with ceramic bracket and metal brackets
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት (partial dentures, full denture, zirconia , ceramic crown, Implant
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት


አድራሻ: ፒያሳ ከኢትዬ ሴራሚክስ ወረድ ብሎ ከአንበሳ ፉርማሲ አጠገብ ኢመኤ ህንዓ 4ኛ ፋሎር ላይ
  Tel: 0911892011 / 0930202124
14.4K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-15 20:39:22 ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መገደላቸው ተነገረ!

ለሁለት ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን የፋብሪካውን አንድ ኃላፊ ለቢቢሲ ገለጹ።ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁት የስኳር ፋብሪካው ኃላፊ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።

አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው።ከተገደሉት መካከለ ሦስቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በዛሬው ዕለት መፈጸሙ ተገልጿል።ሌሎቹ ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ሲሆን ቀብሩ ዛሬ የሚፈጽም ሲሆን፣ እንዲሁም ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።

አራቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም እኚሁ የፋብሪካው ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።

አንደ ኃላፊው ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።ኃላፊው፣ ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።ስለ ግድያው እንዴት? እና ስንት ሰዓት? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።

በፋብሪካው እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም ኃላፊው አስረድተዋል።በእገታው ዙሪያ ቢቢሲ የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማናገር እየሞከረ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ስናገኝ እናካትታለን።በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አቅራቢያ ከአዲስ አበባ 110 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946 ዓ.ም. ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የኔዘርላንድስ ተቋም እና በኢትዮጵያ መንግሥት የጋራ ባለቤትነት የተቋቋሙ በአገሪቱ ቀዳሚ የስኳር ፋብሪካ ነው።

ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለቤትነት ስር መግባቱ ይታወሳል።ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 496/2014 ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ከተደረጉት አምስት ስኳር ፋብሪካዎች መካከከል አንደኛው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
15.5K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 18:50:57
ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት ይፋ አደረገ።

የባንኩን አዲስ መለያ የተዘጋጀው በአቶ ያየህይራድ ታደሰ እና በስቱዲዮኔት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለስራውም 7 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል። አዲሱ የንግድ ምልክት የዓባይ ወንዝ ዋና መገለጫ ከሆነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ የተነሳ እና በሰባት አራት ማዕዘናዊ ቋሚ መስመሮች የተወከለ መሆኑን ተጠቅሷል።

ባንኩ ነባሩን የንግድ ምልክት እና መገለጫ ወደዚህ የቀየረው በተለየ መልኩ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት እና ለእድገት እና ለፈጠራ ያለውን ትጋት ለማስረዳት በማሰብ ነው ተብሏል። ይህም የባንኩን እድገት፣ ችግሮችን የመቋቋም አቅም፣ አስተማማኘነት እና ታማኘነት ያመለክታል ሲባል ሰምተናል፡፡

Via ሸገር ኤፍ ኤም
@Yenetube @Fikerassefa
13.0K viewsedited  15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 10:27:59 የሎተሪ አሸናፊ ባለመቅረቡ ስምንት ሚሊዮን ብር ተመላሽ መደረጉ ተገለጸ

እያንዳንዳቸው የአራት ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ስምንት ሚሊዮን ብር ዛሬ የካቲት 29/ 2016 ዓ.ም ተመላሽ መደረጉን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ።

እነዚህ ሁለት ዕጣዎች ብሔራዊ ሎተሪ ከሚያሳትማቸው ከፍተኛ ዕጣ የሆነው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬቶች መሆናቸውን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ዳይሬከተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከቀረቡት አምስት ቲኬቶች ሶስቱ ቀርበው 12 ሚሊዮን ብር ሁለት አሸናፊዎች ቢረከቡም የቀሪዎቹ ሁለት ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ብለዋል።

ጳጉሜ 2015 ዓ.ም የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የሁለቱ ቲኬቶች ወይም የስምንት ሚሊዮን ብር አሸናፊ በቀን ስራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ ሲሆን ዕጣው ከወጣ ከሶስት ወር በኋላም ወስዷል።

ሌላኛው አሸናፊ የቀን ሰራተኛው የሚሰራበት መኪና አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ሲሆን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ መጥቶ የአራት ሚሊዮን ብር ሽልማቱን ወስዷል።

በ2010 ዓ.ም የወጣው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በተመሳሳይ መልኩ ስምንት ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች የያዙ አሸናፊዎች አልቀረቡም።

የዕጣው አሸናፊዎች አለመቅረባቸውን በተመለከተ በሚዲያ ከተነገረ በኋላ ጊዜው ሊያልፍ አምስት ቀን ሲቀረው አንድ ግለሰብ ሶስቱን ቲኬቶች አቅርቦ 12 ሚሊዮን መቀበሉን አስረድተዋል።

የዕጣ አሸናፊዎች መጥተው ገንዘባቸውን አለመውሰድ በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥም የሚገልጹት አቶ ቴዎድሮስ በዚህ አጋጣሚም ገንዘቡን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተመላሽ ያደርገዋል ብለዋል።

“ህብረተሰቡ ሎተሪ የመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት አለው። የዚያን ያህል ደግሞ የማያዩ በርካታ ደንበኞች አሉ” ብለዋል።

በእንቁጣጣሽ የሎተሪ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዕጣ ዓይነቶችም በተደጋጋሚ ይህ እንደሚያጋጥምም ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.2K viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 10:03:50
Biggest Student Event

March 17 Sunday @ Cassiopeia hotel
2:00 Morning until 8:00 Local Time.


Hosted by In Africa Together (IAT)

Licensed company in Michigan, United States and Licensed in Addis Ababa, Ethiopia

Students can start their study abroad applications process

No Pre Payment
No English Proficiency Exam
100% Admission Guarantee

Register only with your documents

USA Italy China

Our Packages will provide you with higher visa chances

66% scholarship in USA the rest 34% with student loan

100% Scholarship in Italy and China with additional pocket money

You can apply for Bachelors Degree,Masters Program  and PHD

To be part of this event
Register in the link below
https://form.jotform.com/240624657131149
13.0K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 09:19:03
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፒያሳ ለሚነሱ የግል አልሚዎች “ካሳ እና ምትክ መሬት” እንደሚሰጥ አስታወቀ!

በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ ከተገነባው የአድዋ ድል መታሰቢያ ጎን በሚገኘው ቦታ ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ ከስፍራው እንደሚነሱ የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አበቤ ማረጋገጫ ሰጡ። ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች የከተማው አስተዳደር “የጋራ መኖሪያ ቤት” አሊያም “አዲስ የሚገነባ የቀበሌ ቤት” እንደ የምርጫቸው እንደሚያቀርብ፤ በአካባቢው በተዘጋጀው ፕላን መሰረት ግንባታ ለማከናወን የገንዘብ አቅም ለሌላቸው የግል አልሚዎች ደግሞ “ካሳ እና ምትክ መሬት” እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

አዳነች ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኙ “የመንገድ ኮሪደር ልማት” ስራዎችን በተመለከተ በሰጡት ገለጻ ነው። በመንግስት እና ለመንግስት ቅርበት ባላቸው የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በትላንትናው ዕለት በተላለፈው በዚህ ገለጻ፤ የኮሪደር ልማቱን የተመለከተ ጥናት ሲከናወን የቆየው ከግንቦት 2015 ጀምሮ መሆኑ ተጠቅሷል።

ይህ የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከጸደቀ ማግስት ጀምሮ “ወደ ስራ እንዲገባ እና ልዩ ክትትል እንዲደረግለት” ውሳኔ ተላልፎ ነበር። ከንቲባ አዳነች በትላንቱ ገለጻቸው ይህንኑ አረጋግጠዋል።

“ይሄንን በምንሰራበት ሰዓት ከመንገድ ላይ የሚነሱ፣ ከመንገድ ላይ ወደ ውስጥ ጠጋ የሚሉ አጥሮች ይኖራሉ። ከተለያየ ቦታ ላይ በእርጅና አሁን ያለንበትን ዘመን የማይመጥኑ ግንባታዎች አሉ። ከከተማው መዋቅራዊ ፕላን ውጪ የተገነቡ አሉ። የተለያዩ ጥፋቶች አሉ...እርሱን ለማስተካከል ሰዎችን ከቦታቸው ልናነሳ እንችላለን” ሲሉም አዳነች ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
13.9K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ