Get Mystery Box with random crypto!

ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት ይፋ አደረገ። የባንኩን አዲስ | YeneTube

ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት ይፋ አደረገ።

የባንኩን አዲስ መለያ የተዘጋጀው በአቶ ያየህይራድ ታደሰ እና በስቱዲዮኔት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለስራውም 7 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል። አዲሱ የንግድ ምልክት የዓባይ ወንዝ ዋና መገለጫ ከሆነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ የተነሳ እና በሰባት አራት ማዕዘናዊ ቋሚ መስመሮች የተወከለ መሆኑን ተጠቅሷል።

ባንኩ ነባሩን የንግድ ምልክት እና መገለጫ ወደዚህ የቀየረው በተለየ መልኩ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት እና ለእድገት እና ለፈጠራ ያለውን ትጋት ለማስረዳት በማሰብ ነው ተብሏል። ይህም የባንኩን እድገት፣ ችግሮችን የመቋቋም አቅም፣ አስተማማኘነት እና ታማኘነት ያመለክታል ሲባል ሰምተናል፡፡

Via ሸገር ኤፍ ኤም
@Yenetube @Fikerassefa