Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-02 15:12:08
በጎንደር በኩል 50 ኪ.ሜ ሱዳን ስትወረን ለመሬት ብለን አንጣላም ያለው መንግስት፣ በጋምቤላ በኩል ደቡብ ሱዳን ከ19 ወረዳዎች ውስጥ 15ቱን ወረዳዎች ወረራ ስትፈፅም እጁን አጣጥፎ የተቀመጠው መንግስት ቀይ ባህርን ለማስመለስ ውጊያ ልገጥም ነው እያለን ነው። የአማራ ህዝብ በእንደዚህ አይነቱ ቀሽም ድራማ ድጋሚ እንደማይሸወድ ተስፋ አለኝ!

ከላይ ባያያዝኩት ቪዲዮ የጋምቤላ ነዋሪዎች የኦሮሞ ብልፅግና መሬታችንን ለደቡብ ሱዳን ስለሰጠብን የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደን ብለዋል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.0K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 18:25:01
በፓስተር ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገቡ ንብረቶች ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ወጣ!

በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገበ ንብረት ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ያወጣው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው፡፡*ባንኩ ሰኔ 13 ቀን 2015 አመት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የሃራጅ ማስታወቂያ፣ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም የተመዘገቡ ንብረቶች በሃራጅ እንደሚሸጡ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በዮናታን ስም የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ላይ የሚገኝ 400ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያለው ባለ ሶስት ወለል መኖሪያ ቤት አንደኛው ሲሆን፣ በ22 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ መሸጫ ዋጋ ተቀምጦለታል፡፡ እንዲሁም በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1ሺህ 271 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንጻ ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጫረታ የወጣበት ሲሆን 30 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ ብር ተቀምጦለታል፡፡

ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጨረታ የወጣበት ደግሞ በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ በካርታ ቁጥር የተመዘገበ 500 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤትም ይገኝበታል፡፡

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
2.5K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 06:29:35
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ትናንት በወለጋ ሆሮ ጉደሩ በኦነግ ሸኔ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም በርካታc የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ብሬን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያ ተሰብስቧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 05:52:54 አጫጭር መረጃዎች በሩሲያ ዉስጥ የተፈጠረዉ ዉጊያ በተመለከተ

የዋግነር አለቃ ፕሪጎዝሂን ወደ ሞስኮ እየገሰገሱ የነበሩትን ተዋጊዎቻቸው ደም መፋሰስን ለማስወገድ ወደ ኃላ በመመለስ ወደ ጦር ሰፈራቸው እንዲገተቡ ማዘዛቸዉ ተሰምቷል፡፡ፕሪጎዝሂን እንዳሉት ተዋጊዎቹ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 200 ኪ.ሜ ወደ ሞስኮ ተጉዘዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ  የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "በጣም ፈርተዋል" ቅጥረኛ ወታደሮ ወደ ሞስኮ ሲገፉ የሆነ ቦታ ተደብቀዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምዕራባውያን ሀገራት የዋግነር ቅጥረኛ ቡድንን "የሩሶፎቢክ(የሩሲያ ጥላቻ) ግባቸውን ለማሳካት" እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቋል።

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ፅህፈት ቤት ሁኔታውን ለማስታገስ ከዋግነር መሪ ፕሪጎዝሂን ጋር ስምምነት እንደፈፀሙ ተናግረዋል ።በቤላሩስ ፕሬዝዳንት ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ላይ በተሰራጨው መረጃ ፕሪጎዝሂን በመላው ሩሲያ የሚያደርጉትን የዋግነር ተዋጊዎች እንቅስቃሴ ለማስቆም ተስማምተዋል፡፡

እስራኤል ዜጎቿ በሩሲያ የሚኖራቸውን ቆይታ ወይም የጉዞ እቅዳቸውን እንደገና እንዲያጤኑበት አሳስባለች።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የጸጥታ ሃላፊዎችን በነገው እለት ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣዉ  መግለጫ አስታውቋል።

የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን ኃይሎች የሩሲያን ወታደራዊ አመራር ለማስወገድ ወደ ከተማዋ ሲንቀሳቀሱ በዋና ከተማው ውስጥ ያለው ሁኔታ "አስቸጋሪ" እንደሆነ አስጠንቅቀዋል፡፡“ሁኔታው አስቸጋሪ ነው። በተቻለ መጠን በከተማው ዙሪያ ከመጓዝ እንድትቆጠብ እጠይቃለሁ ፣ የመንገድ መዘጋት ሊኖር እንደሚችል በማስጠንቀቅ ሰኞ ስራ እንደማይኖር“ አስታውቀዋል ።

ኢራን በሩሲያ ፌደሬሽን የህግ የበላይነትን እንደምትደግፍ በመግለጽ የተፈጠረወቁን ችግር እንደ ውስጣዊ የሩሲያ ጉዳይ ትቆጥራለች ሲሉ የኢራን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ገልፀዋል ።

ፈረንሣይ በሩሲያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ "ከፍተኛ ተለዋዋጭነት" ያለዉ በመሆኑነ ወደ ሩሲያ ዜጎቿ ከሚደርጉት  ጉዞ እንዲቆጠቡ መክራለች፡፡

ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ቱርክ በሩሲያ ውስጥ ለተፈጠረዉ አመጽ “ሰላማዊ መፍትሄ” ለመፈለግ ዝግጁ መሆኗን ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ንግግር መግለጻቸዉን የቱርክ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የሩስያ የቅርብ አጋር የሆነችው ቤላሩስ በዋግነር ቅጥረኛ ቡድን እየተካሄደ ያለው የትጥቅ አመጽ ለምዕራባውያን ሀገራት "ስጦታ" እንደሆነ በመግለጽ አመፁ "አደጋ" ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
5.2K views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 22:00:12 በዕለተ አርብ አጫጭር መረጃዎች

በታላቁ አንዋር መስጂድና አካባቢው በሙስሊም ምዕመናን እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ  አለመግባባት የሰው ነፍስ መጥፋቱ ተሰምቷል። ባለፈው ሳምንት እንዳጋጠመው ሁሉ ዛሬም ዐርብ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም. ከተካሄደው የጁመዓ ሶላት በኋላ በአንዋር መስጂድ አካባቢው የተኩስ ድምጽ መሰማቱን እና የሞቱ እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸው ተነግሯል። ተመሳሳይ ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ውጪ በአንዳንድ አካባቢዎች መከሰቱ የተሰማ ሲሆን፣ ከእስልምና ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ወይም ከፖሊስ ስለተከሰተው ችግር እና ስለደረሰ ጉዳት አስካሁን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ዘመነ ካሴ በመስከረም ወር በቁጥጥር ሥር ውሎ  በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶት እንደነበር ይታወሳል። በከባድ የሰው መግደል ወንጀል  ተከሶ የነበረው፤ የአቶ ዘመነ ካሴ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ ዐቃቤ ሕግ መልስ ለመስጠት የክስ ችሎት ለማሰማት ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ ተዘግቦ ቆይቷል። በመጨረሻም ዛሬ ግንቦት 25 /2015 ቀን በዋለው ችሎት፤ አቶ  ዘመነ ካሴ ከወንጀል ነፃ ነህ መባሉ ተሰምቷል።

  በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚመራ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ልዑካን ለጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ለጉብኝት ወደ ሸራሮ ከተማ ያመራ ሲሆን፤ በኤርትራ ወታደሮች ክልከላ እንደገጠመው ተገልጿል። ቡድኑ ወደ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ለጉብኝት ተንቀሳቅሶ እንደነበረ እና የእርዳታ ተደራሽነት ለመታዘብ እንደሞከረ ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ  ኤርትራዊያን ስደተኞች ለእስር መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል። ኢሰመኮ በመግለጫው ስደተኞቹ “የማስረጃ ሰነድ የላችሁም” በሚል ምክንያት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቁሟል። እንዲሁም ክስ ሳይመሠረትባቸው በእስር የቆዩ መኖራቸውን እና በተለያየ ጊዜ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ከእስር የተለቀቁ መኖራቸውንም ኮሚሽኑ አመላክቷል።

የዩክሬን ባለሥልጣናት በዋና ከተማዋ  ኪየቭ ላይ የተነጣጠሩ፣ ከ30 በላይ የሩስያ ሚሳኤሎችንና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል። የዩክሬን አየር ኃይል፣ ዛሬ ዐርብ በሰጠው መግለጫ፣ በሩስያ የተተኮሱ 15 ክሩዝ ሚሳኤሎች እና ለጥቃት የተሠማሩ 21 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በአየር መከላከያ ሥርዐታቸው ተመትተው መክሸፋቸውንና መውደቃቸውን አስታውቋል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
2.4K views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 20:54:33
#Update

" በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ም/ቤቱ አሳውቋል።

የጁመዓ ሰላት ለመስገድ በአንዋር መስጂድ የተገኙና በተፈጠረው ችግር ምክንያት በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታግተው የቆዩ ምእመናንም ወደየቤታቸው #በሰላም ሸኝተዋል።

አንድም ሰው እንዳልቀረ ካረጋገጡ በኃላ አመራሮቹ የመስጂዱን ቅጥር ጊቢ ለቀው መውጣታቸው ተገልጿል።

ከፍተኛ ም/ቤቱ ፤ " ለሞቱት ጀነት እንዲወፍቃቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለተጎዱትም ቶሎ ማገገምን ይቸር ዘንድ አላህን እንጠይቃለን " ብሏል።

በቀጣይ ህዝበ ሙስሊሙ እየተፈፀሙበት ያለውን አላግባብ የመብት ጥሰቶች በተገቢው መልኩ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉበኤ ውሳኔ መሰረት የተቋቋመውን ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴን እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚሰጠውን አቅጣጫ እንደ መሪ ተቋም በማክበር ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ነው።

https://t.me/wektawi1mereja
2.4K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 15:03:32
አስቸኳይ መልዕክት ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከኡስታዝ አቡበከር አህመድ

በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው::

ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ።

በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.5K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 11:49:35 ​​የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፤ " የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " አለ

ዛሬ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ  አቶ ሃይሉ አዱኛ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት እየተካሄደ ስላለው የቤቶች ፈረሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ፤  ምንም እንኳን እነማን እንደሆኑ በግልፅ ያልተናገሩት " አንዳንድ አካላት " ሲሉ የጠሯቸው በኦሮሚያ ክልል ህገ ወጥ ግንባታዎችን የማፍረሱን ሥራ በአንድ ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ማስመሰላቸው ፈጽሞ ትክክል አይደለም ብለዋል።

" የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " ያሉት ኃላፊው " በክልሉ 600 በሚሆኑ ከተሞች በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን የማፍረስ ሒደት እንደሚከናወን ገልፀዋል።

ሕግ የማስከበር ስራው በዋናነት ህገ-ወጥነትን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ኃላፊው ይህ ስራ በሚሰራበት ወቅት የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ፤ አካላት የአንድ ብሔርና ሃይማኖት እንደተጠቃ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን የሚያራግቡት ትክክል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ህገወጥ ግንባታ ሲካሄድ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፤ " መንግስት ኃላፊዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ኃይሉ አዱኛ ፤ " የሃይማኖት ተቋማት እና የእምነቱ ተከታዮች እምነትን ተገን አድርገው ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን በጋራ ሊከላከሉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በርካታ መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በተደጋጋሚ ማሳወቁ እንዲሁም መፍትሄ እንዲፈለግ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉ የሚዘነጋ አይደለም።

ምክር ቤቱ ከቀናት በፊት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይም በ " ሸገር ከተማ " ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት ምትክ ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ በሸገር ከተማ አስተዳደር እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል ሲል መግለጫ መስጠቱ የሚዘነጋ አይደለም።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.9K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 07:37:44
ይሁኔ በላይ የብልፅግና እና ወያኔ አጀንዳ ተቀበለ..

አማራ መቼም አፈግፍጐ በወያኔ ካርታ ተወስኖ አይጠብም

ይሁኔ ይህን ነጠላ ሙዚቃ መልቀቅ አለበት ከራሱ አሳማኝ የግል ምክንያት እና ገጠመኝ  ካልሰማን በቀር። መጀመሪያውኑ የራሱን ውሳኔ ከሶሻል ሚዲያ የሚሰበሰብ አቀንቃኝ መሆኑ እራሱ ዘፋኙ በራሱ ላይ ያልቆመ እና ያለደጋፊ ባላ በራሱ መተማመን የጎደለው መሆኑን ግልፅ ያደርጋል።

ወያኔ ለዘመናት ስትመኝ የኖረችው ተሳካላት።እሷ በ1987 ዓ.ም ህገመንግስት  መተከልን ቆርሳ፣ ወንድሙ አፋርን አውጥታ ፣ ሸዋን ቆራርሳ ፣ ቤነሻጉልን ሸርፉ፣ ሪያ እና ወልቃይትን ጐርዳ አማራነትን አጥብባ እሷ በወሰነችለት ጠባብ ቦታ ላይ ብቻ ሰፍሮ ድንበሩ እንደሆነ እዲያስብ እና ከኢትዮጵያዊ ማዕቀፍ እንዲወጣ ነበር ለዘመናት ስትሰራ እና ስትመኝ የኖረችው። ይህ የአማራ ታጋይ መስለው የወያኔን አጀነዳ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚያቀነቅኑ ይኖራሉ ማረም አለባቸው። አዲስ አበባ ድሮ በረራ የነበረች የጥንቷ የአፄ ዳዊት ከተማን መካድ ነው። በአማራ አገር መስራች ነው :: አማራ ባይኖር ዛሬ ኢትዬጵያ አትኖርም ነበር። ዛሬ አማራነቱን አስከብሮ ግዛቱን ኢትዮጵያ የያስጠበቅ አማራ እሱ ስልብ ብአዴን ነው ። ትግሉን በአማራ ይጀምራል ፍጻሜው የአባቶቹን ግዛት ኢትዮጵያን ክብራን አስመልሶ ያስበበራል።  አማራ መቼም ታሪካዊ ግዛቱን ወያኔ በሰፈረችለት ግዛት ብቻ  ተቀብሎ አይኖርም :: ሌላ የሚሉት ሁሉ በወያኔ ቫይረስ የተከተቡ በአብይ ክርኵሰት የተጠለፉ ናቸው ። ጥንቃቄ አድርጉ ህዝቡን ባልተገባ መንገድ አትምሩት :: ከ 32 አመት ጀምሮ እንጂ ከ 16 ኛው ክ/ዘመን በፊት ኢህአዴግ አልነበም  :: ዛሬ መጥቶ አይወስንለህም ::


ወጥር ጀግናዬ
ትግሉ እስከ ቀራኒዮ ነው
https://t.me/wektawi1mereja
2.8K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 18:50:13
ፑቲን ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር በክሬምሊን እየተወያዩ ይገኛሉ።
President Putin Holds Talks With Eritrean Counterpart At The Kremlin

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.8K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ