Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-03 19:48:43
1.1K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 19:48:40 "መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!"

* በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ  የተሰጠ የጋራ መግለጫ

ባለፉት 30 አመታት የተከተልነው “የጎሳ ፌደራሊዝም” የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሰብዓዊነቱ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ አግዶታል፡፡ የሠላምና የጸጥታ ዕጦት፣ መረን የለቀቀ ሙስና፣ አድሏዊ አሠራር፣ ዘውገኛነትና ጎጠኝነት ሥር ሠዶ የገነገነበት ዘመን ላይ እንድንደርስም አስገድዶናል። በዚህ ላይ ስለሀገሩ ኅላዌ፣ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚገደው ዜጋ ደግሞ ተብከንካኝና ባይተዋር እንዲሆን ተፈርዶበታል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምንገኝበትን የብሶት ደረጃ “አላውቅም” የሚል የገዥው ፓርቲም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣን ካለ ያለበትን የኃላፊነት ሥፍራ የዘነጋና እውነታውን የካደ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ ችግር፣ ምስቅልቅልና ብሶት ዉስጥ ነው።

ማንኛውም ዜጋ በሀገሩ ዉስጥ የህይወት ዋስትና ሊኖረው ሲገባ፣ ዛሬ ዘውግን ወይንም ሃይማኖትን፣ ወይንም ደግም ከገዥዎች ፍላጎት የተለየ ሃሳብ መግለጽን መሠረት ባደረጉ ፍረጃዎች የተነሳ በዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። በሠላም ወጥቶ መግባትም ፈታኝ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም ማንነትን መሰረት ባደረገ የጥላቻ እሣቤ የአማራ ህዝብ ለመፈናቀል፣ ስደትና እንግልት ተዳርጓል፡፡  በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤  ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡

ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ከጨበጠበት ወቅት ጀምሮ አማሮች በጠላትነት ተፈርጀው በተደጋጋሚ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የብልጽግና መንግስትም ይህንኑ ፈለግ ተከትሎ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጦስ የዜጎች ህይወት በሰብአዊነት መንጠፍ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል። ከዚህ አኳያ የሁሉም ዜጎች ህይወት እኩል ዋጋ፣ እኩል ክብርና  ዋስትና ሊያገኝ ይገባል ብለን እናምናለን። የመንግሥት ግንባር ቀደም ሃላፊነትና ሥራ የዜጎችን ህይወት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ባለፉት አምስት አመታት የዜጎች ህይወት በእየለቱ ሲቀጠፍ መንግስት ያሳየው ዳተኝነት አሳፋሪ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጡ ሰሞን የነበረው የለውጥ ፍላጎትና ጠንካራ ትግል የተወሰነ ለውጥ መሣይ ብልጭታ በመፍጠሩ፣ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጥ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይቻላል” የሚል ተስፋም አጭሮ ነበር። ይሁን እንጂ “ላም አለኝ በሰማይ …” በሆነ መልኩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተክዶ በተለመደው መልኩ በጎሳ ስሁት ትርክት ውስጥ የምትታሽ ሀገርና ሥርዓት ውስጥ እንድንኖር ተገደናል፡፡ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎች፣ በተናገሩትና በጻፉት ህግን ጥሰው ከሆነ በፍርድ ቤት እንደሚጠየቁ እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን ግን ምን አመጣው?

በቅርቡ ዳግም ጅምላ እስሩ መፈናቀሉ ግድያውና አፈናው የበረታው በአማራው ህዝብ ላይ መሆኑ ምሬትና ብሥጭት እንዲጨምር አድርጓል። በሀገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሣይቀር ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ማፈናቀልና ማሣደድ  ከፍተኛ  ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡   የብልጽግና መራሹ መንግስት የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይም የዜጎችን በሀገራቸው ዉስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት በሚደፈጥጥ መልኩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተደረጉ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውም ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። የአማራው ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን በደሙና በአጥንቱ  በሠራት አገር ባይተዋርና አገር አልባ ተሳዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በግልጽ ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ በላይ የተገለጡት እውነታዎች፣ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ብሶቶችን እንደፈጠሩ፣ የዚህ ችግር ባለቤት በመሆን የወረራ ስልትና ፈጠራውን ያቀነባበሩ ኃይሎች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዚህ ቀደም ሦስቱም ፓርቲዎች (እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ) ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ጉዳዮች እየገለጡ ችግሮች እንዳይባባሱ መንግስትን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ ጥሏል። የትግራይን፣ የአማራን፣ የአፋርን ህዝብንም የበለጠ   ጎድቶታል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን  የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፡ ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል። የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል። ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም። ታዲያ ገዥው መንግስት ይህንን መራር እውነት ዘንግቶ እንዴት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሊከፍት ቻለ!? ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል፡፡

ነገሮች እንዲህ በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ውስጥ እያሉ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል  ሠራዊት አዝምቶ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት” በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል።  የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም። ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://t.me/wektawi1mereja
1.1K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 22:31:41
ትልልቆቹ የህዝብ/የመንግስት ሚድያዎች "ተሽኮርሙመው" ሳይዘግቡት የቀረ ውጤቱ ግን የሁሉንም በር የሚያንኳኳ ዜና።

ህዝቡ ኑሮ ተወደደብኝ ሲል መልሱ... ውትድርና!

አዋጁ የጣለው ውዴታ እና ግዴታ ምን ይላል?

ውዴታ: "ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመታት በሠራዊቱ ብሔራዊ ግልጋሎት ለመስጠት ፍቃደኛ የሆኑ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ አባላትን ተቋሙ ተቀብሎ ግልጋሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።"

ግዴታ: "ማንኛውም የሰራዊት አባል ልዩ ስልጠና ወይም ትምህርት ተከታትሎ ከጨረሰ በኋላ በስልጠና ወይም በትምህርት የቆየበትን ግዜ እጥፍ የማገልገል ግዴታ አለበት።"

But for the general public... "It's easier to fool people than to convince them they've been fooled."

https://t.me/wektawi1mereja
2.3K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:48:01
የኦሮሞ አፓርታይድ የአብይ አህመድ አገዛዝ ቡድን የአማራ ህዝብ አይን የሆኑ ልጆችን “አገር በማፍረስ ወንጀል” እፈልጋቸዋለሁ ሲል የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቷል። በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ካላቸው ውስጥ

1. ከሀገር ውስጥ

ጎበዜ ሲሳይ
ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
በለጠ ጋሻው እና
ሙሉጌታ አንበርብር

2. ከሐገር ውጪ

ሀብታሙ አያሌው፣
ምንአላቸው ስማቸው፣
ብሩክ ይባስ እና
እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ 
ዘመድኩን በቀለ
ልደቱ አያሌው
መሳይ መኮንን ናቸው

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:33:01 ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ  እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:42:11
የብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ፀፀት ይብቃን

ጀግናውን እንጠብቀው!

እሱ ታርቀናል ብሎ ቢተዋቸውም እነሱ ግን የሚተኙለት አልሆኑም። የጀግናው የምሬ ወዳጆን ድምፅ በDeep Fake በማቀነባበር ከግርማ የሽጥላ ግድያ ጋር እጁ እንዳለበት ለማስመሰል እየጣሩ ነው። ይሄን ማድረጋቸው አንድም በህዝባችን መካከል ቁርሾ ለመትከል፣ ሁለትም ጀግናውን ምክንያት በመፍጠር የጥቃት ኢላማ ውስጥ ለመክተት ነው። እንዳንሳሳት!


ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
1.6K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 12:35:06
አህያ ከእረኛዋ ጠፍታ ከጅብ ጋር ካደረች የመጨረሻ ዕድሏ መበላት ብቻ ነው።
በኦሮማያ ክልል ሸኔ እንደ ቅጠል ሲያረግፍ ለነበሩ የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች እንዲህ አልተሽቋለጠም።
   ለአማራ ክልል ለምን ወሬ ይገናል ?
ሸኔ በኦሮሚያ ክልል የብልፅግና እጆችን ቆራርጦ ብልፅግና ተሽመድምዶ የእርቅን ደጅ ጠና ወጤቱን የምናየው ይሆናል።
#የአዲስ_አበባ_ህዝብ_የጩኸትህ_ሰዓት_ተቃርቧል። እንደ ካርቱም ከመሆንህ በፊት ከወዲሁ ቀድመህ ተደራጅ

https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
2.2K viewsedited  09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:40:11
ሰበር ዜና

አቶ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደብድቦ ተገደለ።

የብአዴኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደብድቦ መሃል ሜዳ ሆስፒታል መግባቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

ጉዳቱ የደረሰው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ስብሰባ አድርገው በመመለስ ላይ ባሉበት ወቅት መሆንም ታውቋል።

ግርማ የሺጥላ በህይወት ስለመትረፉ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም የሚሉት ምንጮቹ የዞኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ አብረውት የነበሩት በሙሉ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይናገራሉ።

ጉሳ በምትባለው አካባቢ ከደቂቃዎች በፊት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በህይወት ላይተርፍ ይችላል የተባለውን ግርማ የሺጥላን ወደ ሌላ ሆስፒታል ለማዛወር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።

ምንጭ Ethio 360

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!

https://t.me/wektawi1mereja
2.6K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 11:49:12
መቀሌ ጎዳና ሽመልስ ከነዳ
ተሳፋሪ ሆኖ ጌታቸው ረዳ
እኛስ  ደስ ይለናል የሞተ ተጎዳ
:
19/08/15

ከወሎ ሰፈር አደባባዩ ጋር ካለው ጎሚስታ ማዶ ጫማዬን እያስቦረሽኩ :: የመጣልኝ ግጥም  

https://t.me/wektawi1mereja
2.7K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 22:14:17
በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መሆኑን ኤምባሲው መግለፁን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ