Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-23 21:43:53 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ምልመላና ምርጫ የሚያከናውን  7 ሊቃነ ጳጳሳት ያሉት አስመራጭ  ኮሚቴ መምረጡ ተገለጸ

የግንቦቱ ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወያይቶ  ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች መካከል የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሢመት አንዱና ዋነኛው ነው።

በመሆነም በጉዳዩ ዙሪያ  ለሦስት ቀናት ከተወያየ በኋላ ለአሁኑ ችግር ባላባቸውና አስፈላጊ በሆነባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ በዚህ ዓመት  2015 ዓ/ም  9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጳሳት እንዲሾሙና በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን እውነትና ቀኖናን እንዲሁም መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ባደረገ  መልኩ እንዲሁ አባቶች በሚያስፈልጉባቸው አህጉረ ስብከት የአዳዲስ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይን እንደሚመለከተው ውሳኔ አስተላልፏል።

ስለሆነም በዚህ ዓመት በሚካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የሚሾሙ አባቶች የሚመደቡባቸው   የ(9)ኙ አህጉረ
ስብከት ስም ዝርዝር

፩. ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፪. ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፫. ሆሮ ጉድሩ  ወለጋ ሀገረ ስብከት
፬. የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
፭ ምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት
፮. ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
፯.ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
፰.ጌዴኦ ቡርጅና አማሮ ሀገረ ስብከት
፱.ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት
መሆናቸው ታውቋል።

ከዚህ  በተጨማሪም ምልዓተ ጉባኤው ይህን ጉዳይ በጥናትና በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት የሚለይና  የሚያከናውን 7 ሊቃነ ጳጳሳት የተካተቱበት  አስመራጭ ኮሚቴ መምረጡም ተገልጿል።

የአስመራጭ ኮሚቴው  አባላትም ስም ዝርዝርም

1) ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
2) ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
3) ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4) ብፀዕ አቡነ ናትናኤል
5) ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
6) ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
7) ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
  በመሆን ኮሚቴው ተዋቅሯል።

አስመራጭ ኮሚቴው ጥናቱንና ምልምላውን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በመናበብ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት በማድረግ ለመጨረሻ ምርጫ  ለምልዓተ ጉባኤ የሚያቀርብ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው  እንደሥርዓቱ  በመምረጥ 9ኙን  መነኮሳት የሚለይ ይሆናል።

በምልዓተ ጉባኤው የተመረጡ 9ኙ መነኮሳት አባቶች  ሥርዓተ ሢመት ሐምሌ 9/2015 ዓ/ም  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ እንደሚፈጸም  ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
4.0K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 21:41:54
3.2K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 19:44:31
የእነ አቡነ ሳውሮስ ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ውሳኔን እንደማይቀበል ገልጿል።

በዐቢይ አህመድ አገዛዝ ድጋፍ የሚሰጠው የእነ አቡነ ሳዊሮስ ቡድን  ባወጣው መግለጫ በሰሞኑ ጉባኤ ተላለፈ የተባለው ውሳኔ ፍትሃዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣ እናወግዛለን ብሏል።

አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ ምእራብ ሸዋ ሀገረስብከት በመምጣት አልግሎታቸውን እንዲጀምሩ ሲልም ቡድኑ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም የእነ አቡነ ሳዊሮስ ቡድን የኦሮሚያ አህጉረስብከት በአስቸኳይ ወደስራ እንዲገባም  ጠይቋል።

የእነ አቡነ ሳዊሮስ ቡድን ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ማጠቃለያ እና የውሳኔ ሀሳብ ተስማምተናል በሚል መፈረማቸው ይታወቃል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.4K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:42:49
ከግል ጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳ ስራ አስፈፃሚውን የገደለ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ዋለ፡፡ በአመራሩ መገደል  የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰማውን ኃዘን ገልጿል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በፖሊስ አባል ተገድለዋል፡፡

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡ ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ  በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉ ታውቋል፡፡ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ፍትህን ለማረጋገጥ የሚያከናውነውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ የፖሊስ አባሉ በፈፀመው ድርጊት ማዘኑን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች ፣ ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
1.0K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 07:52:01 ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ  እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
https://t.me/wektawi1mereja
1.9K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:18:46
“የዶ/ር አብይ አህመድን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። በመሆኑም ወደ ሀገር ቤት እሄዳለሁ!”

-አቶ ልደቱ አያሌው

የአብይ አህመድን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ወደ ሀገር ቤት እሄዳለሁ። ይሄን ውሳኔዬን በአጉል ጀብደኝነት እንዳታዩብኝ። ውድ ህይወቴን እንደሚነጥቁኝ ባውቅም፣ ለለውጥ ዋጋ ከፍዬ ማለፍ እፈልጋለሁ።

ብሄር መርጦ በግፍ ጨፍጭፎ፣ በደውዘር የቀብረው አብይ አህመድ እኔን በአሸባሪነት መፈረጁ የሞራል ዝቅጠቱን ያሳያል። በ31 አመት የፖለቲካ እንቅስቃሴዬ የትጥቅ ትግል እንኳን ደግፌ አላውቅም። ያሳፍራል። አብይ አህመድ በስልጣን እና በገንዘብ የማይደለል የለም ብሎ ያምናል። እኔ እንደዚያ አይደለሁም።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:18:24
“የዶ/ር አብይ አህመድን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። በመሆኑም ወደ ሀገር ቤት እሄዳለሁ!”

-አቶ ልደቱ አያሌው

የአብይ አህመድን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ወደ ሀገር ቤት እሄዳለሁ። ይሄን ውሳኔዬን በአጉል ጀብደኝነት እንዳታዩብኝ። ውድ ህይወቴን እንደሚነጥቁኝ ባውቅም፣ ለለውጥ ዋጋ ከፍዬ ማለፍ እፈልጋለሁ።

ብሄር መርጦ በግፍ ጨፍጭፎ፣ በደውዘር የቀብረው አብይ አህመድ እኔን በአሸባሪነት መፈረጁ የሞራል ዝቅጠቱን ያሳያል። በ31 አመት የፖለቲካ እንቅስቃሴዬ የትጥቅ ትግል እንኳን ደግፌ አላውቅም። ያሳፍራል። አብይ አህመድ በስልጣን እና በገንዘብ የማይደለል የለም ብሎ ያምናል። እኔ እንደዚያ አይደለሁም።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.5K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 06:50:11
በአማራ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ሳይባባስ፤ ፓርላማው የሰላማዊ መፍትሔ አስፈላጊነትን ለመንግስት “በአስቸኳይ እንዲያሳስብ” ኢሰመኮ ጠየቀ

በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው “የጸጥታ እርምጃ” የተፈጠረው ጉዳት ሳይባባስ፤ ፓርላማው የሰላማዊ መፍትሔ አስፈላጊነትን ለመንግስት የስራ አስፈጻሚ አካል “በአስቸኳይ እንዲያሳስብ” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቀረበ። ብሔራዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም፤ በተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት “የተዓማኒነት እና የአካታችነት” ጥያቄም ተነስቶበታል።

ጥያቄው የተነሳው ኢሰመኮ የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን፤ ለፓርላማው የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው። በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አማካኝነት የቀረበው ሪፖርት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበሩ አዎንታዊ እርምጃዎች እና አሳሳቢ ሆነው የቀጠሉ ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነበር።

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን “ወታደራዊ እንቅስቃሴ” በአሳሳቢነት ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ፤ “ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት አንድምታ ስላለው በቅርበት እየተከታተልነው ነው” ብለዋል። መንግስት በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ ባለው “የጸጥታ እርምጃ” “በሲቪል ሰዎች ላይ የሞትም፣ የንብረት ውደመትም፣ የመፈናቀልም ጉዳት ደርሷል” ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ “እስካሁን ባለው መረጃም በመነሳት ከሰብዓዊ መብት አንጻር በጣም የሚያሰጋ” መሆኑን ገልጸዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10853
2.5K views03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 23:39:51
የክሬምሊኑ ጥቃት ሩሲያ ዜለንስኪና ግብረአበሮቹን ከማስወገድ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላት አሳይቷል ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ

በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ክሬምሊን ቤተመንግስት የተቃጣው የድሮን ጥቃት ሞስኮን ክፉኛ አስቆጥቷል።

የሀገሪቱ የደህንነት ምክርቤት ምክትል ሊቀመንሩ ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ፥ ጥቃቱ ሩሲያ ቮልድሚር ዜለንስኪ እና ግብረአበሮቹን ከማስወገድ ውጭ ሌላ አማራጭ አሳጥቷታል ነው ያሉት።

የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት በኬቭ ላይ ሊወሰድ የሚችለው የአጻፋ እርምጃ የበረታ እንደሚሆን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ሩሲያ ዩክሬንን ተጠያቂ ያደረገችበትና ፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመግደል ያለመ ነው ያለችውን የድሮን ጥቃት ማክሸፏን መግለጿ ይታወሳል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ግን ኬቭ ከጥቃቱ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላት ተናግረዋል።

አሜሪካ በበኩሏ የክሬምሊኑን ጥቃት በተመለከተ መረጃው ደርሶኛል፤ ትክክለኛውን ጥቃት አድራሽ እና አላማውን ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም ብላለች።
Via አል ዐይን
https://t.me/wektawi1mereja
145 views20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 21:10:39 "መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!"

* በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ  የተሰጠ የጋራ መግለጫ

ባለፉት 30 አመታት የተከተልነው “የጎሳ ፌደራሊዝም” የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሰብዓዊነቱ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ አግዶታል፡፡ የሠላምና የጸጥታ ዕጦት፣ መረን የለቀቀ ሙስና፣ አድሏዊ አሠራር፣ ዘውገኛነትና ጎጠኝነት ሥር ሠዶ የገነገነበት ዘመን ላይ እንድንደርስም አስገድዶናል። በዚህ ላይ ስለሀገሩ ኅላዌ፣ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚገደው ዜጋ ደግሞ ተብከንካኝና ባይተዋር እንዲሆን ተፈርዶበታል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምንገኝበትን የብሶት ደረጃ “አላውቅም” የሚል የገዥው ፓርቲም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣን ካለ ያለበትን የኃላፊነት ሥፍራ የዘነጋና እውነታውን የካደ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ ችግር፣ ምስቅልቅልና ብሶት ዉስጥ ነው።

ማንኛውም ዜጋ በሀገሩ ዉስጥ የህይወት ዋስትና ሊኖረው ሲገባ፣ ዛሬ ዘውግን ወይንም ሃይማኖትን፣ ወይንም ደግም ከገዥዎች ፍላጎት የተለየ ሃሳብ መግለጽን መሠረት ባደረጉ ፍረጃዎች የተነሳ በዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። በሠላም ወጥቶ መግባትም ፈታኝ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም ማንነትን መሰረት ባደረገ የጥላቻ እሣቤ የአማራ ህዝብ ለመፈናቀል፣ ስደትና እንግልት ተዳርጓል፡፡  በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤  ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡

ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ከጨበጠበት ወቅት ጀምሮ አማሮች በጠላትነት ተፈርጀው በተደጋጋሚ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የብልጽግና መንግስትም ይህንኑ ፈለግ ተከትሎ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጦስ የዜጎች ህይወት በሰብአዊነት መንጠፍ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል። ከዚህ አኳያ የሁሉም ዜጎች ህይወት እኩል ዋጋ፣ እኩል ክብርና  ዋስትና ሊያገኝ ይገባል ብለን እናምናለን። የመንግሥት ግንባር ቀደም ሃላፊነትና ሥራ የዜጎችን ህይወት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ባለፉት አምስት አመታት የዜጎች ህይወት በእየለቱ ሲቀጠፍ መንግስት ያሳየው ዳተኝነት አሳፋሪ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጡ ሰሞን የነበረው የለውጥ ፍላጎትና ጠንካራ ትግል የተወሰነ ለውጥ መሣይ ብልጭታ በመፍጠሩ፣ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጥ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይቻላል” የሚል ተስፋም አጭሮ ነበር። ይሁን እንጂ “ላም አለኝ በሰማይ …” በሆነ መልኩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተክዶ በተለመደው መልኩ በጎሳ ስሁት ትርክት ውስጥ የምትታሽ ሀገርና ሥርዓት ውስጥ እንድንኖር ተገደናል፡፡ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎች፣ በተናገሩትና በጻፉት ህግን ጥሰው ከሆነ በፍርድ ቤት እንደሚጠየቁ እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን ግን ምን አመጣው?

በቅርቡ ዳግም ጅምላ እስሩ መፈናቀሉ ግድያውና አፈናው የበረታው በአማራው ህዝብ ላይ መሆኑ ምሬትና ብሥጭት እንዲጨምር አድርጓል። በሀገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሣይቀር ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ማፈናቀልና ማሣደድ  ከፍተኛ  ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡   የብልጽግና መራሹ መንግስት የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይም የዜጎችን በሀገራቸው ዉስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት በሚደፈጥጥ መልኩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተደረጉ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውም ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። የአማራው ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን በደሙና በአጥንቱ  በሠራት አገር ባይተዋርና አገር አልባ ተሳዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በግልጽ ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ በላይ የተገለጡት እውነታዎች፣ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ብሶቶችን እንደፈጠሩ፣ የዚህ ችግር ባለቤት በመሆን የወረራ ስልትና ፈጠራውን ያቀነባበሩ ኃይሎች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዚህ ቀደም ሦስቱም ፓርቲዎች (እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ) ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ጉዳዮች እየገለጡ ችግሮች እንዳይባባሱ መንግስትን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ ጥሏል። የትግራይን፣ የአማራን፣ የአፋርን ህዝብንም የበለጠ   ጎድቶታል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን  የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፡ ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል። የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል። ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም። ታዲያ ገዥው መንግስት ይህንን መራር እውነት ዘንግቶ እንዴት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሊከፍት ቻለ!? ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል፡፡

ነገሮች እንዲህ በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ውስጥ እያሉ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል  ሠራዊት አዝምቶ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት” በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል።  የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም። ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://t.me/wektawi1mereja
762 views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ