Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-17 10:31:53
ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ በቅርቡ በቤተክርስቲያኗ ላይ የደረሰው ችግር በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት በመፈታቱ እጅግ በጣም ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸውና ውጭ ሀገር የነበሩት እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የመጡበት ወቅት አይነት ስሜት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

" በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ችግር የሌለበት ጊዜ የለም " ያሉት ቅዱስነታቸው " ችግሩን በእውቀት ፣ በማስተዋል መፍታት ያለ ነገር ነው የኛም ድርሻ ነው ፤ አሁንም ቢሆን የተደረገው ይሄው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ቅዱስነታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትላንቱ ቀን እንደሚመጣ ብዙ መልፋታቸውንና መድከማቸውን አንስተዋል " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ለፍተዋል ፣ብዙ ደክመዋል በተለይ ሰሞኑን እንደው አላረፉም ፤ ሁላችንም እንደዚሁ፤ ወንድሞቻችንም ፣ አባቶችም ሲመላለሱ እንደሰናበቱ አውቃለሁና ይሄንን ታላቁን የቤተክርስቲያን ሚስጥር ወደ ቤቱ መመለሱ በጣም በጣም እጅግ የሚያስደስት ነው " ብለዋል።

" እናተም ደስ ሊላችሁ ይገባል አባቶች (የተመለሱ አባቶችን ማለታቸው ነው) ፤ ወደ ሰላም ስንመለስ አብረን ስንሆን ደስ ሊላችሁ ይገባል ፤ እኛ በእውነቱ የቀኖና ቤተክርስቲያን ስለሆነ ዝም ብለን ስንል ሰነበትን እንጂ ሃዘናችን አልቀረም ፤ እናተን ወንድሞቻችንን በማጣታችን እጅግ ልባችን ሳይቆስል አልቀረም፤ ነገር ግን ቀኖና ቤተክርስቲያን ለመጠበቅ ስለሆነ እኛም ኃላፊነት ስላለብን ነው ይሄን ሁሉ ስናደርግ የሰነበትነው እንጂ ደስ ብሎን አይደለም። ይህንን በማየታችን ደስ ብሎናል ፤ እኔም በጣም ተደስቻለሁ፤ ክብሩ ጠ/ሚኒስትር እናመሰግናለን። " ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል
https://t.me/wektawi1mereja
1.3K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:12:29 #እባብ_ለመደ_ተብሎ_በኪስ_አይያዝም
1.2K viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 09:12:01 ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
https://t.me/wektawi1mereja
1.2K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 22:07:33 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ተፈታ

በቤተ ክርስቲያኒቱ የገጠመውን ፈተና ለመፍታት የሁለቱ ወገኖች የሐይማኖት አባቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡

አንድነትን የሚያጸና እናአገልግሎትን የሚያሰፋ መንገድ መከተል ተገቢ መሆኑን በማመን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ቤተ ክርስቲያን የጀመረችውን ሥራ አጠናክራ እንደምትቀጥል ከመግባባት ላይ መደረሱ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም በጀትና የሰው ኃይል ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶት ይሠራል ነው የተባለው፡፡

በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እምነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲጠናከሩ እና ቤተ እምነትን ለትውልድ ለማሻገር መፈታት የሚገባቸውን ችግሮች በጥናት እና በአሠራር መፍታት እንደሚገባ መተማመን ተፈጥሯል፡፡
1.4K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 00:28:28 የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል!

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል። ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር ያሳውቃሉ ተብሏል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
99 views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 06:58:20
974 views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:49:10 በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር
እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ
ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም
ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግ እያወቅን በመከራችን
ደግሞ እንመካለን”

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገ
ወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና
ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን
የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት
በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን
ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ
ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ
ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና
እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና
የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል
ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት

በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም
ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት
፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር
አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት
በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡
በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው
የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን
በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት
ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት
መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ
አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ
የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር
ሽማግልዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ
መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት
ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት
የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ
ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል
ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤
በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና
የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና
በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት

መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡
በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል
ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም
ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ
ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት
ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ
አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤
የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ
አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ
በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤
አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
ስምምነት ላይ  ተደርሷል፡፡
በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ
ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት
ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ
ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ
ወስኗል፡፡
በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ
በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ  ምሕረት ላይ  ባለመቅረት
የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣
የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ
ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር
አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ  ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት
እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን
አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ
ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ
የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ
በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት
እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ
በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም
የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም
በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት
መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር
በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡
በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር
ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን
የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤
አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው
ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን
የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖት

ተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ
አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና
በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት
ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1.3K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:37:49
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበረው ውይይት የቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎቿ እንደተመለሰላትና ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ዝርዝር እና ሰፊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@
660 views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:26:54 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ በአወገዘቻቸው ተጠሪዎች ላይ ከደቂቃዎች በፊት የእግድ ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል።
686 views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:02:16 መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡

መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
1.6K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ