Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-31 06:55:06
ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑ በትግርኛ ባደረገው ንግግር እንዲህ ሲል ነበር የተናገረው

''ትጥቅ በመፍታትና መሳሪያ በማስረከቡ ዙሪያ ላይ ምንም መደናገር አያስፈልግም።

እነሱ የፈለጉት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆን ነበር መሬት ላይ አሁን የሆነው ግን ሌላ ነው።

በዚህ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም በጣም sensitive ጉዳይ ስለሆነ፣ እርግጥ በትጥቅ ማስፈታት ዙሪያ የሚሰሩ የቴሌቪዢን ፕሮግራሞችን ሲመለከቱ ስጋት የሚገባቸው አንዳንድ የኛ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ።

ግን በዚህ ደረጃ ድህንነታችን ለሌላ አሳልፎ የሰጠ የለም።'' Asfaw Abreha
በማለት የጦር መሳሪያ ማውረዱ (disarmament) ጉዳይ ተፈጻሚ እንዳልተደረገ ፍንጭ ሰጥቷል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 20:38:45 Special News : አሜሪካ ዩጋንዳ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ፤ ኡጋንዳ ትላንት ያፀደቀችውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል የሚያደርገውን ህግ " አሳፋሪ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት " በማለት ተቃወሙ።

ባይደን ፤ " ይህ አሳፋሪ ድርጊት በዩጋንዳ ውስጥ ያለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ሙስና  የቅርብ ጊዜ እድገት አመላካች ነው "  ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ባይደን ፤ የአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነት ም/ ቤት የዩጋንዳው ሕግ አሜሪካ ከአገሪቱ ጋር ባሏት ግንኙነቶች ላይ ምን አንድምታ እንዳለው አጥንቶ እንዲያቀርብ አዘዋል ተብሏል።

ከህጉ ጋር በተያያዘ ፤ አሜሪካ ለኡጋንዳ የምትሰጠውን እርዳታና ኢንቨስትመንት ልታቆም እንደምትችል ባይደን አስጠንቅቀዋል።

የሕጉን ተፅኖ ከግምት በማስገባትም የዩጋንዳ የአጎዋ (AGOA) ተጠቃሚነት እንደሚገመገም አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም ሙስና ውስጥ በተሳተፈ ማንኛውም ሰው ላይ #ማዕቀብ እና ወደ አሜሪካ የመግባት #እገዳን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያጤኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከባይደን በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ፤ ህጉን ተቃውመዋል ፤ መስሪያ ቤታቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ መመሪያ እንዲያወጣ አዘዋል።

የባይደን አስተዳደር የዩጋንዳ ፓርላማ አፈ ጉባኤ " አኒታ አሞንግ " አሁን ያላቸውን የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ መሰረዙ ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት (ተመድን ጨምሮ) ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በዩጋንዳ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንዳያኖሩና እንዳያፀድቁ ማስጠንቀቂያዎችን ቢሰጡም ፕሬዜዳንቱ ትላንት መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገበትን ሕግ በፊርማቸው በማኖር አቅፅድቀውታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.0K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 20:38:36
2.6K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 12:37:30
በአዲሱ ሸገር ከተማ ቤት የማፍረሱ ሂደት 100ሺ አቤቱታዎች ቀርበውበታል ተባለ


        በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ዜጎችን በግዳጅ የማስነሳትና ቤቶችን የማፍረስ ሂደት 100ሺ ቅሬታዎች እንደቀረቡበት ተገለፀ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ መረጃው ያልተጣራና ከአንድ ወገን ብቻ የተገኘ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ “ህገወጥ ግንባታ” በሚል እየተካሄደ ካለው የቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ከአንድ መቶ ሺ በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት ገልጿል፡፡
ተቋሙ በተያዘው በጀት አመት ከ133ሺ በላይ አቤቱታዎችን መቀበሉን ገልፆ፤ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ካለው የቤት ፈረሳ ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች እንደሆኑም አመልክቷል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ “ህገወጥ ግንባታ” ናቸው እያለ ለሚያፈርሳቸው የመኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች ምትክ ቦታ እንደማይሰጥና ለተፈናቃዮችም ጊዜያዊ መጠለያ እንዳልተዘጋጀላቸው የገለፀው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ይህ ሁኔታም ተቋሙን እጅግ እንዳሳሰበውና መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ አመልክቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በከተማው እየፈረሱ ያሉት ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተገነቡና የግንባታ ፈቃድ የሌላቸው ቤቶች መሆኑን ጠቁሞ፤ እርምጃው የህግ የበላይነትን ከማስከበር ጋር የተያያዘ ነው ብሏል፡፡
በህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተገለፀውና 100ሺ ቅሬታዎች ቀረቡበት የተባለው ጉዳይም ከእውነት የራቀ፣ ውይይት ያልተደረገበትና፣በአግባቡ ያልተጣራ እንዲሁም ከአንድ ወገን ብቻ በተገኘ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ሲል አስተዳደሩ አስተባብሏል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
2.8K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 11:27:36 ተጨማሪ 41 የኢዜማ አባላትና አመራሮች መልቀቃቸው ተሰምቷል

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ኢዜማ አባላቱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ ፓርቲው ያዘጋጀው የአምስት አመት የፖለቲካ ሂደትን የሚገመግም ሰነድ ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

ይሁንና ተጨማሪ 41 የፓርቲው የምርጫ ወረዳ አመራርና መደበኛ አባላት ድርጅቱን ለቀው መውጣታቸውን ፓርቲው ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/wektawi1mereja
2.8K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 23:10:27
ሰበር መረጃ

በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አሸነፉ

በቱርክ በድጋሚ በተካሄደ ባለው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ቱርካውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ በዛሬው እለት ድምጽ ሰጥተዋል።

እስካሁን በተካሄደ 98.33 በመቶ የድምጽ ቆጠራ ጊዜያዊ ቆጠራ ላለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.10 በመቶ እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ ደግሞ 47.90 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።

በቱርክ ባለፈው ግንቦት 14 በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እና ዋና ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ አብላጫ ድምጽ ማግኘት  ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ ተካሂዷል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/wektawi1mereja
3.3K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 12:26:11
በሩዋንዳው የዘር ግጭት ከ2 ሺህ በላይ ግጭቱ ሸሽተው በቤተክርስቲያን የተጠለሉ ሰዎችን ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በገፍ አቃጥሎ ሲያበቃ በኋላ በዶዘር ቆፍሮ የቀበራቸው ወንጀለኛ Fulgence Kayishema ከዓመታት ክትትል በኋላ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ስር ውሎ ተይዞ ፍርድቤት ቀርቧል።

ይህ ነብሰ ገዳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስደተኛ ሆኖ ስሙ ቀይሮ ነበር የገባው። የአንድ እርሻ ዘበኛ ሆኖ ነበር ሲሰራ የነበረው። የሩዋንዳና የደቡብ አፍሪካ የጽታና ድህንነት ሰራተኞች ባደረጉት ክትትል በ2018 እሱ መሆኑ ካወቁ በኋላ ለተባበሩት መንግሥታት በማሳወቅ የስደተኝነት ማንነቱ ተፍቆ ዛሬ ፍርድቤት ቀርቧል።

PS: ትላንት በአማራ ህዝብ ላይ በኦሮሞ ክልል በተለይ ወለጋ ውስጥ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ገና አፉ እንደከፈተ ወንጀሎች ሳይቀጡ ከሞት የተረፈው ህዝባችን አሁንም ሜዳ ላይ ተበትኖ ይገኛል። ይህን የመሰለ የዘር ማጥፋት ጭካኔ የፈጸሙ ሰዎች ግን ዛሬ ባለ ጊዜ ሆነው ማለፍ ቢችሉም የነገ ዕጣ ፈንታቸው እንደዚህ ሰውዬ ከመሆን እንደማያልፍ ሊያውቁ ይገባል።

ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ዓለም ነገ የማን ጓደኛ እንደሚሆን አይታወቅምና ወንጀለኞች አንድ በአንድ መዝግበን እንያዝ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.3K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 19:55:02
ባለስልጣኑ በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የጣለውን እግድ አነሳ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ግንቦት 13/2015 ጥሎት የነበረውን ጊዜያዊ እግድ ከዛሬ ግንቦት 18/2015 ጀምሮ ማንሳቱን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ ጊዜያዊ ዕግዱን መነሳቱን አስመልክቶ ለማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.6K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 16:07:53
የሸገር ከተማን መስጂድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ!

በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈጸመ የሚገኘውን መስጂድ የማፍረስ ተግባር በመቃወም ሙስሊሙ ማኀበረሰብ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል።የሰልፉ ዋነኛ ዓላማም በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የመስጂድ ፈረሳዎች በአስቸኳይ እንዲቆም ማሳሰብ መሆኑ ታውቋል።ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንዋር መስጂድ ላይ የተቃውሞ እያደረገ ያለውን ህዝበ ሙስሊም እንዲበተን ማድረጉም ተነግሯል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ግንቦት 15/2015 በሰጠው መግለጫ፤ በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ ያወገዘ ሲሆን፤ ዛሬ ግንቦት 18/2015 በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ኹሉም መስጂዶች የጁምዓ ኹጥባ መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ የሚገኘውን የመስጂድ ፈረሳው የተመለከተ እንዲሆን ማሳሰቡን መዘገባችን ይታወሳል።

ምክር ቤቱ በአዲሱ የሸገር ሲቲ ከተማ አስተዳደር ከረመዳን 1 ጀምሮ የፈረሱ መስጂዶች ቁጥር 19 መድረሳቸውን ያስታወቀ ሲሆን፤ እነዚህ የፈረሱት መስጂዶች በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙት በቡራዩ መልካ ኖኖ፣ በኮዬ ፈጬ፣ በሰበታ፣ በፉሪ፣ በአጃምባና ሌሎችም አካባቢዎች እንደሆነ ገልጾ ነበር፡፡በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፈው ደብዳቤ፤ በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁም ይታወሳል።

[Addis Maleda]
https://t.me/wektawi1mereja
3.5K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 17:51:01
ሰበር ዜና!

የኢዜማ የስራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት
አቶ የሽዋስ አሰፋ ፣ ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ
፣አቶ ሀብታሙ ኪታባ  አቶ የጁአልጋው ጀመረ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ኑሪ ሙደሲር እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከኢዜማ መልቀቃቸውን አሳወቁ!

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
3.5K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ