2023-04-17 22:08:09
አጫጭር መረጃዎች በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ
በካርቱም የሚገኘው የአል-ሻባብ ሆስፒታል ረዳት ዳይሬክተር አል-ታይብ አብደልራህማን በጦር ሠራዊቱ ማዘዣ ሕንጻ አቅራቢያ ያለው ሆስፒታሉ የጥቃት ሰለባ መሆኑን ተናግረዋል። “ሆስፒታሉ በዛሬው እለት ብቻ አራት ጊዜ በቦምብ ተመቷል በዚህም ሰራተኞችና ህሙማን ቆስለዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
በሱዳን መከላከያ እና የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) በሚል ከተሰየመው ቡድን መካከል ለሶስት ቀናት በቀጠለው ውጊያ የሱዳን ቲቪ (SRTC) እና የሱዳን ራዲዮ ከትላንትና ጀምሮ ከአየር ላይ የወረዱ ሲሆን መንግስታዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ የሀገር ፍቅር ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎች በማጫወት ላይ ይገኛል።
የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ናቢል አብዱላህ የጦሩ ሰራዊት በአርኤስኤፍ ቦታዎች ላይ የአየር ጥቃት መጀመሩን ተናግረዋል።ነገር ግን ጥቃቱ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ እስካሁን አልታወቀም። "ግጭቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስቆም እየሰራን ነው ምክንያቱም ዜጎችን ለአደጋ እንዳይጋለጹ ከፍተኛ ፍላጎት አለን" ብለዋል።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገሪቱ ጦር አዛዥ አል-ቡርሃን የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች(RSF) በመባል የሚታወቀውና በጄኔራል ዳጋሎ የሚመራው ኃይል እንዲፈርስ ትእዛዝ መስጠታቸውን እና በመላው ሀገሪቱ በሚካሄደው ጦርነት አማፂ ቡድን ተብሎ መፈረጁን ይፋ አድርገዋል።
የሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ለስካይ ኒውስ እንደተናገሩት ወታደሮቻቸው የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ልዩ ሀይሉ እንደሚያሸንፉ የተናገሩ ሲሆን ለውይይት ግን ክፍት መሆናቸውን ተናግረዋል። በካርቱም የሚገኙ ነዋሪዎች እንቅልፍ ማጣታቸውንና ምግብና ውሃ እጥረት መኖሩን ገልፀዋል።
ዋይት ሀውስ በሱዳን የሚደረገው ውጊያ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ከወታደራዊ መሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ገልጿል።
በሱዳን ቁልፍ ከተማ የሆነችውን ሜሮዌ ለመያዝ ከአውሮፕላን ማረፊያው በስተምዕራብ በኩል የከተማ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።
https://t.me/wektawi1mereja
254 views19:08