2022-12-04 21:17:23
" እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " - ተፈናቃይበምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል።
እንደ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘገባ ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል።
በወረዳው በ19 ቀበሌዎች ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ነቀምቴ እና ጊዳ አያና ወደሚገኙ አካባቢዎች ለመሸሽ ተገደዋል።
ባለፈው ሀሙስ ኪረሙ ላይ ከፍተኛ ውድመት የደረሰ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ፥ " እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " ያሉ ሲሆን ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን ፣ ተፈናቃዮች ሰላምን ፍለጋ በሸሹበት ወቅት እየራባቸው ፤ እየደከማቸው በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልፀዋል።
ከተፈናቃዮች መካከል ፤ አንድ አዛውንትም በመንገድ ላይ ደክሟቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ያጠቆሙት እኚሁ ነዋሪ " ባለፉት ሳምንታት በነበረው ግጭት ኪረሙ ላይ በአንድ ጉድጓድ ሃያ (20) እና አርባ (40) ሰው ስንቀብር ነበር " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት ተናግረዋል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንዳሳወቁት ፤ ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እናቶች ልጆቻቸውን ተሸክመው ጫካ ለጫካ እንዲንከራረቱ፣ እንዲሰቃዩ ሆነዋል።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት በተለያዩ ዞኖች አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በወለጋ ላለፉት ዓመታት የነበረው የፀጥታ ችግር፣ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ሞት ፣ መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሲሆን ችግሩ እልባት ከማግኘት ይልቅ ይበልጥ እየተባባሰ እና እየተወሳሰበ መጥቷል።
የአካባቢው ህዝብ ዘርቶ ማጨድ ፣ ሰርቶ መብላት ፣ እንደልቡ ወጥቶ መግባት፣ ልጆቹን በሰላም ያለስጋት ማሳደግ አልቻለም።
- በተደጋጋሚ ጊዜ ፤ የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች በግልፅ ተለይተው እየታወቁ ችግርም ሲኖር የድረሱልን ጥሪ እየቀረበ በፍጥነት መፍትሄ መስጠት ለምን አልተቻለም ?
ሁሌም ክቡር የሆነው የሰዎች ህይወት ከረገፈ በኃላ የአንድ ሰሞን ትኩረት ተሰጥቶ ፤ ሰሞነኛ ጩኸት ተጩሆ ከዛ ችግሩ ለምን ይቀጥላል ?
- ስንት ሰው ሲያልቅ ነው ዘላቂ መፍትሄ የሚበጀው ? አሁን እየሆነ ላለው እና ለነበረው ነገር ሁሉ ማነው ተጠያቂ ?
- ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ፤ እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ ሰላሙንና ደህንነቱን ማስጠበቅ ያልቻሉ የመንግስት አካላት መቼ ነው በህግ ፊት ተጠያቂ የሚሆኑት ?
- የተሰቃዩ ፣ የተበደሉ ፣ የሚወዱትን የተነጠቁ እንዴት ነው ፍትህ የሚያገኙ ? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጣቸው ይገባል።
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
4.8K views18:17