Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-12-09 19:52:10
ሰበር መረጃ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከስልጣኗ ተነስታለች!

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.9K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 20:38:38 ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ!

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን ተሰምቷል።

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎች መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱን  ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከሁለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡

የኦሮሚ ክልል ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳኔውን  ከመቃወምም አልፈው ወደፊት ችግር ሊፈጥር ይችላል በማለት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
#ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.4K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:33:10 በአዲስአበባ በትምህርት ቤቶች ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩ አካላት በቁጥጥር ስር ዉለዋል -የአዲስአበባ ፖሊስ

በመላው የፀጥታ ሐይላችን የህይወት መስዋዕትነት እና በህዝባችን ቀና ተባባሪነት እየሰከነ የመጣው ሰላማችንን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚንቀሳቀሱ ሐይሎችን ለመቆጣጠር የሚያከናውነውን ህግን የማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት በቅርቡ በከተማችን በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በአንድ በኩል የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብትና ማንነታቸውንና ባህላቸውን መግለፅን እንደ ጫናና በሃይል በሌሎች ላይ እንደተጫነ አድርጎ የመቀስቀስ በሌላ በኩል ደግሞ  የኦሮሞ ህዝብ  እየሞተ ነው የህዝብ ባህልና ማንነት ተዋረደ የሚሉ እርስ በእርሱ የሚቃረን የግጭት ማቀጣጠያ  አጀንዳ በመፍጠር  እንዲሁም የወልቃይትና የአዲስ አበባ ጉዳይ አንድ ነው የሚል መፈክር ይዘው ከመውጣት ባሻገር  የሐገሪቱን ሰንደቅ ዓላማና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ከሰንደቁ ላይ ላይ በማውረድና መሬት ለመሬት በመጎተት ከፍተኛ ድፍረት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል፡፡

ሰሞኑን በተወሰኑ አንደኛና ጥቂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጥፋት አጀንዳቸውን ከተቀበሉ አንዳንድ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን በማደናገርና በማወናበድ ምንም የማያውቁ አብዛኛው ተማሪዎችን ከፊት በማሰለፍ ባስነሱት ረብሻ  በትምህርት ቤቶቹ ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ተረጋግጧል ከከተማዉ ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ከዚህም በሻገር ፅንፈኛ በሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው በመጠቀም የፀጥታ ሐይሉ ህጋዊ ተግባሩን እንዳይወጣ ለማሸማቀቅ ታስቦ ከዚህ በፊት የተቀረፁ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምስሎችን እና እርምጃ ተወስዶ የታረመን ድርጊት አሁን እንደተፈፀመ በማስመሰልና በማሰረጨት ህብረተሰቡ ለአመፅና ብጥብጥ እንዲተባበር እያነሳሱ መሆናቸውን ፖሊስ በመረጃ ያረጋገጠ ሲሆን ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ዘጠና ሰባት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

አያይዞም የፀጥታ ሐይሉ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በሐሠተኛ ሚዲያዎችና የሃሰት ዘገባዎች ሳይሸማቀቅ ከህዝብና ከመንግስት የተሰጠውን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን እና ህግ የማስከበር ግዴታውን እንደሚወጣ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ የወትሮ ሠላሟና  የነዋሪዎቿ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚያንገበግባቸው ግለሰቦችንና ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደቱን ለርካሽ የፖለቲካ አላማቸው ለማዋል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሃይሎችን ፤ በመለየት ህግ የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ፖሊስ ህብረተሰቡም ልጆቹን ከመምከር ባሻገር የሠላሙ ፀር የሆኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን አጋልጦ ለፀጥታ አካላት በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ 

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትና መረጃዎችን ለመስጠት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚቻል  የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.4K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:33:03
3.7K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 10:57:11
የኦነግ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ለ #VOA አሁን የሰጠው ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦

"የኦሮሚያ ልዩሀይል ከአራት ኪሎ ትዕዛዝ ሳይጠብቅ ከእኛ ጋር ተቀናጅቶ ርምጃ እየወሰደ ነው። አሁን የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የአምባገነን ስልጣን መጠበቅ ትቶ ከህዝቡ ጋር ሆኖ  በምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ መልካም ስራ ላይ ነው። እነርሱም ስራ ላይ ናቸው። እኛም ስራ ላይ ነን"

የአማራ ብሄር ተወላጁ በበኩሉ "እየገደለን ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ከሸኔ ጋር ሆኖ ነው! ክልሉን ልቀቁ ነው የሚሉን" በማለት ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ያስረዳሉ።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.9K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 10:53:51 በቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከጋሞ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የጋሞ ዞን በለውጡ ማግስት ሀገር ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ውስጥ በወገኖቻቸው ላይ በተፈጸመ ግድያ የተቆጡ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን ሲገልጹ የጋሞ አባቶች እርጥብ ሣር ይዘው በመንበርከክ ጸብ በማብረድ ሠላም እንዲመጣ በማድረጋቸው  የሠላም አምባሳደር በመሆን ለሌሎች አካባቢዎችም አርዓያ መሆናቸው የአደባባይ  ሀቅ ነው።

ነገር ግን ህዳር 28/2015 ዓ.ም አባ ማቲያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወዕጨጌ ተክለሃይማኖት በሰጡት መግለጫ " በአርባምንጭ እስር ቤትና በአባያ እስር ቤት በእስረኞች ላይ ግድያ ተፈጽሟል " ተብሎ የተሰጠው መግለጫ ፈጽሞ የተሳሳተ እና  አሁን ላይ የጋሞ ዞን እና አርባምንጭ ከተማ ከማንኛውም አካባቢ በተሻለ ሠላምና መረጋጋት የሰፈነበት መሆኑን ባለመረዳት የተሰጠ በመሆኑ እርማት እንዲደረግበት የጋሞ ዞን አስተዳደር ይጠይቃል።

መግለጫው የጋሞ ጎፋ  ሀገረ ስብከት በማያውቀውና በአካባቢው እንዲህ አይነት ግድያ ባልተፈጸመበት እንዲሁም አባያ በመባል የሚታወቅ እስር ቤት በሌለበት አካባቢውን የሞትና የእልቂት አካባቢ በማድረግ  የተሰጠው መግለጫ የዞናችንና ከተማችን አርባምንጭን ገጽታ ያጠለሸ በመሆኑ የዞኑ አስተዳደር "በማህበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል እና በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የተለቀቀው መግለጫ ዞኑንም ሆነ ከተማችን አርባምንጭን የማይገልጽ ከእውነት የራቀ መግለጫ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳልን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ስለሆነም  እንደ ሀገር በሰላም በአብሮነትና በመቻቻል ለሌላው በምሳሌነት የሚገለፅን አካባቢ በዚህ ልክ  የሌለን እና ያልነበረን ወደፊትም እንዲሆን የማይፈልግን ድርጊት በመግለፅ የዞናችንን መልካም ስምና ገፅታ በአሉታ ወይም በሀሰት የተገለፀበትን መንገድ የማንቀበለው በመሆኑ መግለጫውን ያወጡ መገናኛ ብዙሃን  እና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ፈጥነው እርማት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት
#ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.8K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 21:28:14
ብራቮ

“ፋኖ ነፍሰጡር አይነካም፤ ፋኖ ህፃን አይገልም፤ ፋኖ የሀገር መከታ ነው!”

ዲላ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች በዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ!

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.0K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 19:40:38
እንጠብቅሻለን አለብን አደራ”

የአዲስአበባ የአዲስ ከተማ መሰናዶ ተማሪዎች በዛሬው ተቃውሞ ላይ

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.4K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 11:56:20
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን ግጭት ላይ ዋና ተሳታፊዎች “ሸኔ” እና “የአማራ ታጣቂዎች” እንደሆኑ ኢስመኮ ገለጸ

በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን ግጭት ላይ ዋናኛ ተሳታፊዎች “ሸኔ” እና “የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ሲል የመብት ኮሚሽኑ ገለፀ።ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በዜጎች ላይ የተለያዩ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች፣ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ እንደተፈፀመባቸው በተለያዩ መንገዶች እየተገለፀ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የምርምርና ክትትል ሪጅናል ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታ “በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች ውስጥ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎች ዋነኞቹ ተሳታፊዎች ናቸው” ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።ሰዎች በማንነታቸው ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የገለፁት ዳይሬክተሩ ከሰሞኑ የተፈፀሙት ጥቃቶች “መጠን ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል” ስጋታቸውን አጋርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)፣ እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ትላንት በሰጧቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች እየተፈፀመ ያለውን ብሔር ተኮር ጥቃት እንዲቆም መንግስት እርምጃዎች እንዲወስድ፣ የሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ እንዲሰጡበት እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ጥፋተኞች እንዲያዙና አካባቢው በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር ጠይቀዋል።

#ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.2K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ