Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-25 07:58:47 #Update

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ አግኝተው ከተመረጡ በኃላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ርዕሰ መስተዳደር አድርገው እንደሾሟቸው ትላንት የጠ/ሚ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።
667 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 12:33:16 #አማራ_ነን_እንጂ_አማራ_አድርጉን_አላልንም። #ራያ_ራዩማ_አላማጣ
1.6K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 06:55:29
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ ማግኘታቸው ተነገረ።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህም አቶ ጌታቸው ረዳን በትግራይ ክልል ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንታዊ እጩ አድርጎ አብላጫ ድምጽ መስጠቱን ቅርበት ያላቸው የፓርቲው ምንጮች እንደገለፁለት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል ዘግቧል።

የአቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው ካፀደቁት በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ነው ' ቪኦኤ ትግርኛ ' ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ በዘገባው ያመለከተው።

ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ  እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
https://t.me/wektawi1mereja
1.8K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 07:37:02
ታዋቂው የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ታፈኑ!

የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ልጃቸን ከትምህርት ቤት አውጥተው በታክሲ ወደ ቤታቸው እየሄዱ ባለበት ቦሌ ብራስ ዮድ አቢሲኒያ አካባቢ ሲደርሱ ከነልጃቸው ቦርሳና ምሳ እቃ እንደያዙ አፍሰው እንደወሰዷቸው ተሰምቷል።

መምህር ታዬን የወሰዷቸው ሲቪል የለበሱ የታጠቁ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል።

የታክሲ ሾፌራቸው ምንድነው? ብሎ ለመጠየቅ ሲሞክር መሳሪያ አውጥተው እንዳስፈራርቱ እና ልጃቸውን ይዞ ወደ ቤት እንደወሰደ ገልጿል።

ምንጭ ፦ ኢሳት
ለፈጣን መረጃ የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!

https://t.me/wektawi1mereja
2.2K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 12:46:47 ሰሜን ኮሪያ ለሙከራ የተኮሰችው ሚሳኤል ከተመታ ጦርነት እንደምትጀምር አስጠነቀቀች


አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ አዲስ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል።
https://am.al-ain.com/article/north-korea-threatens-us-against-test-missile-interception
1.6K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:44:32
ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

Via EOTC
1.3K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 07:19:00 #Oromia

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው  መደበኛ  ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ውሳኔዎቹ ምድናቸው ?

ውሳኔዎቹ ከከተሞች አደረጃጀት ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ እንዲደራጁ ተወስኗል።

1. ቢሾፍ ከተማ ፦ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ድሬ በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

2. ሻሸመኔ ከተማ፦ የሻሸመኔ ከተማ እና የብሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክ/ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

3. አዳማ ከተማ፦ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክ/ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

4. ሮቤ ከተማ፦ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

5. ማያ ከተማ፦ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

6. ባቱ ከተማ፦ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡

1. መቱ ከተማ
2. አጋሮ ከተማ
3. ቡሌ ሆራ ከተማ
4. ነጆ ከተማ
5. ሰንዳፋ በኬ ከተማ
6. ሸኖ ከተማ
7. ሞያሌ ከተማ
8. ዶዶላ ከተማ
9. ሻክሶ ከተማ

ከዚህ ባለፈ የሚከተሉት ከተሞ ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።

1. አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ

2. የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ

3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።

በሌላ በኩል የምስራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል፡፡

በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-
• ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
• ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
• እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

የመደ ወላቡ ወረዳ ደግሞ በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅና የጭናክሰን ወረዳ የነበረው በሁለት ወረዳ የጭናክሰን ወረዳና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።
1.4K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 07:13:36 የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር።


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444
1.4K views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 08:05:41 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ክልልና የኦሮሚያ ክልል አመሮችን ለስብሰባ ጠሩ::
የአማራ ክልልና የኦሮሚያ ክልል አመራሮችና የብልፅግና ስራ አስፈፃሚዎች ለመጀመርያ ጊዜ በጋራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለስብሰባ ለቀጣይ ማክሰኞ  ሶስት ስዓት ጥዋት ተጠርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ቀውስ አስመልክተው የአማራ ክልል ካቢኔ አባላትንና እና የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ አባላትን ከብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በጋራ ለስብሰባ በፅፈት ቤታቸው መጥራታቸው ተሰምቷል::
2.0K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 23:12:01
የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው

በዛሬው ዕለት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የሌሴቶ ፕሬዚዳንት ሳም ማትኬኔ፣ የኬፕ ቬርዴ ፕሬዚዳንት ሆዜ ማሪያ ፔሬራ፣ የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ንዩሲ፣ የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋውዛኒ እና ሌሎችም መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል። 

መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። 

36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 11 እና 12 “የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ ይካሄዳል።
525 views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ