Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi1mereja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi1mereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.46K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-17 17:11:51
5 ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ካርቱም በተነሳው ግጭት መገደላቸው ተገለፀ

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት ሳቢያ አምስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸው እና ቢያንስ ዘጠኝ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸው ታወቀ።በመሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በጀነራል አብዱልፈታል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ጦር መካከል በካርቱም እያካሄዱት ባለው ውጊያ ሳቢያ ነው የአምስት ኢትዮጵያዊያን ሞት የተሰማው።

የካርቱም ነዋሪ የሆኑት የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለፁት ጦርነቱ እየተስፋፋና በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ መሆኑ ጉዳቱ እንዲጨምር አድርጓል። ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩበት እና "ዴም" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተደረገ ጦርነት ሦስት ኢትዮጵያን መሞታቸውን የገለጹት የመረጃ ምንጩ አደጋው የደረሰው ጠዋት ቢሆንም የሟቾች ቀብር አለመፈጸሙን ገልጸው፣ የሟቾች አስክሬን በአካባቢው አል-ጃውዳ ሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል።

https://t.me/wektawi1mereja
941 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 12:37:12 የፈጥኖ ደራሹን ሀይል የሚደግፉት አገራት የሚከተሉት ናቸው ሲል የሱዳኑ ዋሃድ ጋዜጣ አስነብቧል።
አዲስ አበባ፣አስመራ፣ሞስኮ
ዱባይ እና ቻይና ናቸው ብሏል።
እነዚህ አገራት የፈጥኖ ልዮ ኮማንዶውን ጥቃት ሲያቀነባብሩ ነበር ሲል ነው የሱዳን ዋህድ ጋዜጣ የዘገበው። በዚህ አክሎም 11ሺ ጦር ኤርትራ ውስጥ ሲሰለጥኑ እንደኖሩና አሰልጣኙ ሻዕቢያ መሆኑንም ነው ጋዜጣው የዘገበው። ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የልዮ ፈጥኖ ደራሹ አዛዥ መሀመድ ሀምዳን ጋደሎ ( አህሜቲ) ከአዲስ አበባ መንግስት ጋር 4 ጊዜ የስልክ ልውውጥ አድርጓል ነው የተባለው። የአገሪቱን ጦር የመገናኛ ሬዲዮ የጠለፉት የሩሲያ መንታፊዎች ሲሆኑ ሞሳድ ለማስለቀቅ ቢጥርም  እስካሁን አልተሳካለትም ብሏል ጋዜጣው።


ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
1.3K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 23:48:19
የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ?

የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል።

በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል።

እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።

ይህ ሁኔታ በአጠቃላይ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የገለፀው ያሲር አብዱላህ በዚህ ውስጥ ማንም አሸናፊ የለም ብሏል።

ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሱዳን ጦር እና RSF (ፈጥኖ ደራሽ) መካከል የከፋ የከተማ ውስጥ ውጊያ ጭምር ሲካሄድ ነበር።

ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ድል እየተቀዳጁ መሆኑንና አንዱ የአንዱን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተፈላለጉ መሆኑን በሚያወጧቸው መግለጫዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በጄነራል አል - ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በሄሜቲ የሚመራውን RSF " አማፂ " ቡድን ብሎ በይፋ ጠርቶታል። ዳጋሎም (ሄሜቲ) ተሸሽገው የሚገኙ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ ናቸው በማለትም ማንኛውም ዜጋ ከእሳቸው ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው አሳስቧል።

ጦሩ RSF እስካልፈረሰ ድረስ በምንም ለድርድርም ይሁን ለንግግር እንደማይቀመጥ አስገንዝቧል።

በጄነራል ሄሜቲ የሚመራው RSF በበኩሉ ድል እየተቀዳጀ መሆኑንና " ወንጀለኛ ናቸው " ያላቸውን አል ቡርሃንን #ለማሰር እያሳደዳቸው መሆኑን ገልጿል ያሉበትንም ደርሼበታለሁ ብሏል፤ ቡርሃን ግራውንድ ስር #ተደብቀው የህዝብ ልጆችን እንዲዋጉ እየገፋፉ ነው ብሏል።

https://t.me/wektawi1mereja
518 views20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:28:32
ቪድዮ ፦ ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ ደራሽ) በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ " የተማረኩ " ናቸው ያላቸውን #የግብፅ_ወታደሮችን የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል።

የግብፅ ወታደሮች በ " ሜሮዌ "  ስለነበሩበት ሁኔታ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ባይኖርም የግብፅ እና የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ዉጥረት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አልፎ አልፎ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያካሂዱ ቆይተዋል ተብሏል።

RSF ያጋራው አጭር ቪዲዮ በርካታ ድካም የተጫጫናቸው የግብፅ ሰራዊት አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች መሬት ላይ ቁጭ ብለው የRSF ዩኒፎርም የለበሱ አባላት በግብፅ አረብኛ ዘዬ ወታደሮቹን ሲያናግሩ ያሳያል።

ሮይተርስ ቪድዮውን ወዲያውኑ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል። የግብፅ ባለስልጣናትም በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ወዲያውኑ አልሰጡም።

https://t.me/wektawi1mereja
839 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:23:41
በሱዳን ያለው ውጥረት የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል!
*
በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ አባላት መካከል እየተደረገ ያለው የተኩስ ልውውጥ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በካርቱም ሰማይ ላይ የጦር ጀቶች ሲበሩ ታይተዋል።

ሄምቲ በሚለው ቅጽል ስማቸው በሚታወቁት በጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል፣ ወደ አገሪቱ ጦር ስለሚቀላቀልበት ሁኔታ አንዲሁም ኃይሉን ማን ይመረዋል በሚለው አለመግባባት ተፈጥሮ ባለፉት ቀናት ውጥረት በአገሪቱ ውስጥ ሰፍኖ ነበር።

ዛሬ ቅዳሜ ከረፋድ ጀምሮ የተኩስ እና የፍንዳታ ድምጽ በመዲናዋ ካርቱም እየተሰማ ነው። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የካርቱም ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ተቆጣጥሪያለሁ ብሏል።

የአገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑም ተዘግቧል።
በዚህ መካከል የሱዳን ሠራዊት ናቸው የተባሉ የጦር ጀቶች በካርቱም ሰማይ ላይ ሲበሩ ታይቷል።

የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በሱዳን የተከሰው ውጥረት እና ግጭት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።ብሪታኒያም ሱዳን ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ከቤታቸው እንዳይወጡ አሳስባለች።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
844 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:23:40
825 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 12:42:37 ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳም ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
በያላችሁበት መልካም በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው
1.3K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:14:45 ኢሳት ቴሌቪዥን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለስልጣን ለኢሳት ቴሌቪዥን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል፡፡ጣቢያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሚዛናዊነት የጎደላቸው፤ በተጨባጭ መረጃ ያልተደገፉ፤ የህዝቦች መተማመንና አንድነትን ሊሸረሽሩ ሚችሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ ማቅረቡ ማጠንቀቂያው መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው ዘገባዎች ውስጥ የመገናኛ ብዙሐን አዋጅ 1238/2013 የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ 1185/2012 እና የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባርን በመጣስ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ጣቢያው ሚዛናዊነት የጎደላቸውን ሀሰተኛ ዘገባዎችን በማሰራጨት በህዝቦች አብሮበነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ ይህ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን እናሳስባለን ማለቱን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://t.me/wektawi1mereja
1.3K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 06:54:15 ከአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ህዝብን ትጥቅ በማስፈታት የዘር ፍጅት ለመፈጸም የተደረገው ጅምር ተግባር በተባበረ የከተማ አመጽ እና ህዝባዊ እምቢተኝነት  ልዩ ኃይላችን ከሞላ ጎደል መታደግ ተችሏል።ይህ የምዕራፍ አንድ እንቅስቃሴ ያስገኘው ውጤት እጅግ ማራኪ ነበር። ውጤቶችም ፦

ሀ/ ህዝባችን የደረሰበትን በደል ተረድቶ በአንድነት መቆም መቻሉ እና መንግስታዊ ሰርዓቱን  በቃን ለማለትና ትግሉን ለማቀጣጠል ያለው ቁርጠኝነት አሳይቷል ።

ለ/ ሁሉም የክልሉ ከተሞች መንገድ በመዝጋት በመንግስት  ላይ  ከፍተኛ ተፅዕኖ  መፍጠር ተችሏል  ።

ሐ/ የልዩ ኃይላችን ከመበተንና ትጥቅ ከመፍታት መታደግ መቻሉ

መ/ ለልዩ ኃይላችን ምግብና ውኃ እንዲሁም የትራንስፓርት አገልግሎት ማቅረብ የተደረገው እንቅስቃሴ በጠንካራነት ታይቷል

ሠ/ እንደ ወሎ ፣ሸዋ ወዘተ  ከመከላከያ ሠራዊት ጋር የተደረገው ትንቅንቅ  አሸንፈን  መውጣት ተችሏል ።
እና መሰል ተግባራት በመልካም የተገመገሙ ሲሆን  መንግስታዊው የአማራ ልዩ ሀይልን የማፍረስ ፣ክንድህን የማስጣል  እና በቀጣይ ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ የዘር ማጥፋት  ድርጊቱን ለማሰፈፀም  የጀመረው ድንገት በአንድ ሌሊት በመሆኑ አስተባባሪው በአካል ተገናኝቶ የመምከር እና ውሳኔዎችን ቶሎ ቶሎ አለመስጠት እንደ ችግር ታይተዋል።

በመሆኑም  ምዕራፍ ሁለት  እንቅስቃሴን  ለማስጀመር የህዝባዊ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል። ስለሆነም ህዝባችን በፆምና ፀሎት  ውስጥ ሆኖ   ፤የህልውና ችግር ላይ ፤ የመኖር እና ያለመኖር የዋስትና አደጋ ላይ ሆኖም በጉጉት የሚጠብቃቸውን የፋሲካ እና የኢድ አልፈጥር በዓላትን እንደተለመደው ባይሆንም በሰላም አክብሮ  እንዲያሳልፍ የከተማ ውስጥ አመፁ  እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱ  ከነገ ሚያዚያ 5/2015  ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም ተወስኗል።

በመሆኑም ፦
1/  የአማራ ህዝብ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በእዬ ከተሞች መንገድ የተዘጋባቸው ድንጋይ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በማንሳት ከተሞችን የማጽዳትና ሠላሙን የማስጠበቅ ስራ እንዲሰራ፤

2/ መንግስት የተጠየቀውን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ካልሰጠ በቀጣይ የሚሰጡ ተግባራትን ለመፈጸም እንዲዘጋጅ

3/ የልዩ ኃይል አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ባሉበት ሆነው ለሚሰጠው ተልዕኮ እንዲጠብቁ

4/ የመንግስት አካላት የህዝባዊ አመጹን አስተባብረዋል በሚል የጠረጠራቸውን ወጣቶች ከማንገላታት እንዲታቀብ ይህን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ካሉም እርምጃ እንዲወሰድባቸው

5/ የአገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት አባቶች የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ትሆኑ ዘንድ መልዕክት ተላልፏል። ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነው ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ፣ፍትህ እና እኩልነት ነው ።

    (የአማራ ህዝብ ኮሚቴ )
https://t.me/wektawi1mereja
946 views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 22:27:59
የእስር ዜና!

የቀድሞው የ“አል አይን አማርኛ” ጋዜጠኛ፤ በባህር ዳር ከተማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ገለጹ።

“አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ዛሬ አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ስለ ጋዜጠኛው መያዝ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል። ጋዜጠኛው የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆነበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበርም በተመሳሳይ ስለ ዳዊት መያዝ እስካሁን መረጃ እንደሌለው አስታውቋል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/wektawi1mereja
1.4K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ